ETHIO12.COM

ትህነግ “ለሕዝብ ስል አቅጣጫ ቀየርኩ” አለ – «እየተደመሰሱና እየተማረኩ ነው» መንግስት

No photo description available.

ላለፉት አስር ቀናት ” እጃችሁን ስጡ፣ ያለቀ ጦርነት ነው ” በሚል መግለጫና ማሳሰቢያ ሲያሰራጭ የከረመው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ዛሬ በማህበራዊ ገጹ “ሰበር የድል ዜና” በሚል ባሰራጨው ጽሁፍ የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት “የአብይ አሕመድ ሰራዊት” በሚል ጠርቶ በከፍተኛ እንደደመሰሰ አስታውቋል። ቀጥሎም ደሴ ከተማን መቆጣጠር እንደጀመረ አመልክቷል። አያይዞም አቅጣጫ መቀየሩን አመልክቷል።

«የአሸባሪው ህወሓትቡድን አባላት ኩታበር ቦሩንና ተዉለደሬ ከነመሣሪያዎቻቸው እየተማረኩነው።» ሲል መንግስት፣ የአካባቢው አስተዳደርና ወደ ስፍራው ያመሩ የክተተ አባላት መረጃ አጋርተዋል።

በምስሉ የሚታየው «ይህን ብዛት ያለው መሳሪያ ቦሩሜዳ ላይ ከወደቁ የትህነግ ሃይላት ክንድ ላይ የተለቀመ ነው። በርካታ ምስሎችን ማሰራጨት ይቻላል።ግን መከላከያ አይፈቅድም » ሲል ሙክታሮቪች በስፍራው ካሉ የክተቱ አባላት ያገኘውን መረጃ አሰራጭቷል። እሱ ብቻ ሳይሆኑ በርካታ አካባቢው ላይ ያሉ ፋኖዎች ይፋ አድርገዋል። ሌላም አለ።

1 / 7

ደሴ ዙሪያዋም ሆነ መካከሏ፣ ቦሩ ሚዳና ዙሪያው በሙሉ በመከላከያ እጅ እንደሆነች፣ በቪዲዮ የተደገፈ መረጃ በየሰዓቱ እየተላለፈ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ የትህነግ ሰበር የድል ዜና እየተቆጣጠራቸው ያለውን ቦታዎች አልጠቀሰም። ይልቁኑም “ለሕዝብ ሲባል” የትህነግ ሃይል አቅጣጫ ቀይሮ ወደፊት እየገሰገሰ መሆኑንን አመልክቷል። ወዴት አቅጣጫ እንደሆነ ግን አላመላከተም።

የአገር መከላከያ ሃይል ከተማ ውስጥ መድፍ ጠምዶ እየተኮሰ በመሆኑ፣ “ሕዝብ/ የአማራው ሕዝብ ለማለት ነው/ ላለመጉዳት ሲባል ተመጣጣኝ እርምጃ መቆጠቡን የትህነግ መረጃ ይገልጻል። በዚህ ምክንያት አቅጣጫ ቀይሮ ወደፊት በመገስገስ ላይ እንደሆነ ጠቁሟል። በምን ይህል ቀን ግስጋሴው ደሴን እንዳለው እንደሚቆጣጠር ፍንጭ አልሰጠም።

ቀደም ሲል በተደጋጋሚ ጎንደርን፣ ደብረታቦርን፣ ባህር ዳርን እንደሚቆጣጠር አስቀድሞ ለደጋፊዎቹ ቃል የሚገባው ትህነግ እንዳለው ባይሳካለትም፣ ቃል መግባቱን ቀጥሎ ደሴን እንደሚቆጣጠር ቃል ሲገባ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው።

ቀደም ሲል ” ለደሴ ሕዝብ ካለን ፍቅር የተነሳ ኦፕሬሽኑንን ቀይረነዋል” ሲሉ አቶ ጌታቸው ግጥም አክለው አስታወቀው ነበር። ለጊዜው እሳቸው ዛሬ አቅጣጫ ስለመቀየሩ ምንም ባይሉም ዜናው ለሰሚው ግራ አጋብቷል።

መንግስት ዛሬ ማምጫውን፣ የአብን አመራሮች፣ አስተአየት የተጠየቁ ነዋሪዎችና የመንግስት ሚዲያዎች እንዳሉት ከቀናት በፊት ቦሩ ሜዳን ለመቆጣጠር የገባው ሃይል ሲመታ ተቆርጦ የቀረ ሃይል ጥሻ ውስጥ ተደብቆ ቆይቶ ርሃባና ወሃ ጥማት ሲብስበት ተኩስ ከፍቶ ለመውጣት ሲሞክር ወዲያው ተከቦ መመታቱን ነው። ወሎ ይኒቨርስቲን አልፈው ከመከላከያ ጋር በመሆን ስራ እየሰሩ እንደሆኑ የጠቀሱም በተመሳሳይ ብለዋል። ከተማዋ ውስጥ ሰርገው የገቡና ደሴን እንደያዙ ለማስመሰል የሞከሩ ወዲያ እርምጃ እንደተወሰደባቸው መንግስት አስታውቋል።

የትህነግ ሰራዊት መንገድ ቀይሮ ወደየት አቅጣጫ እንዳመራና በየት ዞሮ ደሴን ለመቆጣጠር እንዳቀደ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም። መንግስት ግን ” ከጉድጓዷ የራቀች አይጥ…” እንዲሉ ሲል ነው መረጃውን የቋጨው።


Exit mobile version