Site icon ETHIO12.COM

መከላከያ የጦርነት ጨዋታውን ቀየረ – እሾህን በሾህ

“ቀደም ሲል አስርና አስራ አምስት የሚሆኑ የትህነግ ጭሮች ሊጠቃ ወዳታሰበ ከተማ ሰርገው ይገባሉ። ከዛ በፊት ደግሞ ከተማዋ ውስጥ በተለያዩ ምክንያት ሲቪል መስለው የገቡ ከተቀጣሪ የአካባቢ ነዋሪዎች ጋር በመሆን ወሬ እንዲያስወሩ ይደረጋል። ይህ ካለቀ በሁዋላ ከግንባር ጦርነት ይከፍታሉ። የመከላከያ ሃይል እየለቀመ ሲያሳድድ ሰርጎ የገባው ክፍል ከተደበቀበት ሆኖ ተኩስ ይከፍታል። ወሬ ሲያራግብ የነበረው ሃይል ህዝቡን እየነዳ ጥላቹህ ጥፉ ይላል። መከለከያ እየተዋጋ ከሁዋላው ከተማ ተይዟል ይባላል። ዛሬ ይሄ አይሰራም። አሾህን በሾህ እንደሚባለው መከላከያን ጨምሮ ሁሉም ደፈጣ ገብቷል። የሚቆረጥ ሳይሆን የሚቆርጥ አካል ሆኗል” ሲሉ መኮንኑ ይናግራሉ።

አሁን ላይ ከግንባር የሚወጡ ዜናዎች መልካቸው እየተቀየረ ሲሆን “ለምን ?” የሚልም ጥያቄ እየተነሳ ነው። ” መከተ” የሚለው ዜናስ እስከመቼ ይቀጥላል የሚል አስተያይተም በማህበራዊ ገጾች ሲሰማ ሰንብቶ ነበር። ” ሸዋ ላይ ደረሰዋል፣ አዲስ አበባ ዙሪያ ናቸው” የሚል ዜና እየወጣ ” ተቀጥጠው ተመለሱ” የሚለው ግብረ ዜና መስማት ያንገፈገፋቸውም ጥቂት አይደሉም።

ለሁሉም ጉዳይ ምላሹ የሚጀመረው ” በግልጽ እንነጋገር” በሚል እንደሆነ ስማቸውን የማይጠቅሱ ውስጥ አዋቂ ይናገራሉ። በግልጽ ሲሉም ” በቁጥር እጅግ እጀግ እንበለጥ ነበር” ቀጥለው ደግሞ በፕሮፓጋንዳ ደግሞ ከእጅግም በላይ የበላይበት ተይዞ ነበር። ከዛ በላይ ደግሞ ዘመቻው በዓለም ቁንጮ አገራት፣ ተቋማትና ሚዲያዎች የታገዘ ነበር። በተጨማሪ ደግሞ ያለፈው ሊበጣጠስ ያልቻለ የትህነግ መዋቅር አልሞተም።

ለውጡ እውን ከሆነ በሁዋላ መንግስት አስፈላጊውን የለውጥ ስራ በሙሉ ሃይሉ ሰርቶ ውስጡን እንዳያጠራ በርካታ ችግሮች ዙሪያውን ተለኮሱበት። በየአቅጣጫው በተለኮሰበት እሳት እየተለበለበ ቆይቶ የአገር መከላከያ ተመታበት። በተለበለበ ጎኑ ተንደርድሮ ወደ ጦርንርት ሳይፈልግ ገባ። የሆነውን ሁሉ ሕዝብ ያየው ነው። ከዛም ትግራይ መቆየት በተለያዩ ምክንያቶች ትክክል ሆኖ ባለመገኘቱ መከላከያ ከትግራይ እንዲወጣ ተደረገ። አወጣጡ ላይ ሚስጢር ያሾለኩ የሁለት ሻሞላ ተጫዋቾች ሚና ዋጋ ማስከፈሉ ግን አይካድም። እንደ አስተያየት ሰጪው፤

ቀድም ሲል ጀመሮ ሃይል ሲያደራጅ የነበረው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር፣ እንደ ስሙ ከትግራይ ክልል ውጪ የሚፈልገውን በውል ባያሳውቅም አንዴ ዲፋክቶ፣ ሌላ ጊዜ የፌደራል ሃይሎች እያለ ጦር ሲያከማች ቆይቶ ነበርና አጋጣሚውን ተጠቅሞ አገገመ። በሰርጎ መግባትና ከሁዋላ የሰው ማዕበል በማሰለፍ ስልት በቀናት ውስጥ እንደ ሰደድ አማራ ክልልን ወረረ። አማራ ክልልን ሲወር ያሰለፈው ሃይል እጅግ በርካታ ስለነበር ድንጋጤን ፈጥሮ ነበር። ወዲያው ግን “ከተት” በመባሉ በአብዛኛው ቦታዎች ነጻ ወጡ።

በጎንደር በኩል፣በወልቃይትና ጠገዴ አቅጣጫ ያለውን ሃይል መስበር ያቃተው የትህነግ ጭፍራ አቅጣጫውን ቀይሮ በወሎ ግንባር ተመመ። ሰፊ ቁጥር ያለው ሃይል ተሰልፎ ስለነበር በወሎ ግንባር ትህነግ ብዙም ድል ይቀናዋል ተብሎ ባይታሰብም ደሴን ያዘ። የሆነውን የአብን ከፍተኛ አመራር አቶ የሱፍ ኢብራሂም ሲያስረዱ ” ደሴ የገባው የትህነግ ታጣቂ ሃይል 100 አይሞላም” ነበር ያሉት።

ሰርጎ የገባው የትህነግ ሃይል ከተማው ውስጥ በሚኖሩ ቁጥራቸው በዛ ያሉ የክልሉ ተወላጆች ጋር በመሆን ከከተማ ውስጥ ተኩስ ከፍተው ጦሩ ከፊት እየተዋጋ ከተማዋ መያዝዋን አቶ ዩሱፍ በአካል ያዩትን መስክረዋል። በወቅቱ አቶ ጌታቸው ” ወጠጤዎች” ሲሉ ማስፈራሪያ የላኩላቸው የአብን አመራሮች ሰሞኑንን ከግንባር ሆነው በአማራ ቴሌቪዥን ቀርበው እንዳስረዱት ከሆነ በኮምቦልቻም የሆነው ተመሳሳይ ነው።

ኮምቦልቻ የጠላት ሃይል ሳይገባ ከኢንደስትሪ መነደርና ከኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ የአገር መከላከያና የፌደራል ፖሊስ ልብስ የለበሱ የትህነግ ታጣቂዎች አውቀው መታኮስ ጀመሩ። ይህን ጊዜ ነገሩ ያልገባው ሕዝብ ” የመንግስት ሃይል እርስ በርሱ ተጫረሰ” ብሎ ውሉን ሳተ። ማጅራት መቺና ዱርዬው ኪሱን መሙላት ተያያዘ። ግርግር ለሌባ እንዲሉ ኪስ ለመሙላት አስተኳሽና አስቀንዳቢ …. በዚህ መልኩ ኮምቦላቻ መያዟን አዲስ አበባ ያረፉ አጫውተውናል።

አሁን ምን እየሆነ ነው?

አቶ የሱፍ ኢብራሂም እንዳሉት ሁሉም መስመር ይዟል። ትናንት በቲውተር ገጻቸው እንዳሉት ደግሞ በሁሉም ግንባር ማጥቃት ተከፍቷል። መንግስትም በአስቸኳይ ኮማንድ በኩል ማጥቃት መጁእመሩን አረጋግጧል።

ያነጋገርናቸው ውስጥ አዋቂ መኮንን ” አሁን የጦርነቱ ጨዋታ ተቀይሯል” ብለዋል። ሚሊሻ፣ ልዩ ሃይል፣ ፋኖ፣ ክተተ ያለው ሃይል መከላከያ በሚያወጣውና በተናበበ መልኩ ልክ እንደ ትህነግ ሰርጎ ገብ ሆኗል። ተበትኖ በሁሉም አቅጣጫ ድንበሩን አስፍቶ እያጠቃ ነው። ” እውነት ለመናገር ነገሮች አሁን ተቀይረዋል” ሲሉ በቅርቡ ታላላቅ ድሎች ይፋ እንደሚሆኑ አመልክተዋል። ይፋ እየተደረገም ነው።

“የካራ ቆሪ አርጡማ መገንጠያን ተከትሎ ወደ ሰንበቴ የመጣ ጠላት ሃይል አዋይቱ ፍልውሃ ላይ አብዛኛው ተደምስሶ በርካቶች ተማርከዋል። የካራ ቆሪ አርጡማ መገንጠያን ተከትሎ ወደ ሰንበቴ የመጣው የጠላት ሃይል ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበታል። ከ80 በላይ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ተማርከዋል። ሠራዊታችን ቀሪውን ወራሪ ሃይል እያሳደደው እንደሚገኝም ተገልጿል” በሚል የኢትዮጵያ ዜና አግለግሎት እንዳስታወቀው በመንገድ ላይ የነበረውን የትህነግ ጭፍራ አድብቶ ወይም አድፍጦ የመታው የወገን ሃይል ሰሞኑንን በየአውደ ውጊያው ለተልዕኮ በቡድን ብ እቡድን ሆኖ የሚንቀሳቀሰውን ሃይል እየበጣጠሰ እየመታውና ሰላም እያሳጣው መሆኑ ተሰምቷል። አዋጊዎችን ጭምር በየጥሻው በመሸጉበት መያዝ ተችሏል።

በዚሁ አካሄድ የታላላቅ ድል ምልክቶች መኖራቸውን ያመለከቱት ውስጥ አዋቂ ” አሜሪካና ትህነግ መጮህ የጀመሩት ለዚህ ነው” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። አሜሪካ የኤርትራ መኮንኖች ላይ ማዕቀብ መጣሏ፣ የትህነግ አመሮች ኢትዮጵያን የሚረዱ ላይ እርምጃ እንደሚወስድ መዛቱ፣ የድርድር ሩጫና የሚማረኩት የትህነግ ምልምሎች መብዛት፣ እንዲሁም ደጋፊዎቻቸው አቋርጠውት የነበረውን የሰልፍ ዘመቻ ቀለም እየተቀቡ ደም በማስመሰል መጀመራቸው የዚሁ ማሳያ መሆኑን አመልክተዋል። ከምንም በላይ አሜሪካ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት እንደ መጨረሻ አማራጭ እንደምታይ ማስታወቋ የዚህ ምልክት እንደሆነ ተመልክቷል። አሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ወታደር ይዛ ከገባችና ኢትዮጵያን ለመውጋት ከሞከረች ነገሮች መላካቸውን ሙሉ በሙሉ ሊቀይሩና ወደ ባሰ ምስቅልቅል ሊያመራ እንደሚችል ስጋት ያላቸው እየገለጹ ነው።

ከየግንባሩ የሚሰማው ዜና ቃል በቃል ባይሆንም መከላከያ፣ ፋኖና ሚሊሻው በቅንጅት ድል እያገኙ እንደሆነ መንግስትም ምልክት የሚሰጡ ዜናዎች እያእማ ሲሆን የአማራ ማስ ሚዲያ በበኩሉ በዋግ፣ በዳንሻና በተለያዩ ግንባሮች ድል መገነቱንናብስሯል። በአፋር ግንባርም በተመሳሳይ ተደጋጋሚ ሙከራ ቢደረግም ሊሳካ እንዳልቻለ፣ ዛሬ ግን በአፋር በኩል ያለው ሃይል ወደፊት እንደሄደ ተሰምቷል። “እሾህን በእሾህ” እንዲሉ ትህነግ በጀመረው መንገድ በብዛትና በሰርጎ መግባት ቀና ውጤት መገነቱ ከየአቅጣጫው እየተሰማ ነው

ስለ ኢትዮጵያ የሚናገሩ የማህበራዊ ምስመሮች ሙሉ በሙሉ መዘጋታቸው አድልዎው የት ድረስ እንደሆነ የሚያሳይ እንደሆነ የሚጠቁሙ ክፍሎች ምስኪኑ የትግራይ ህዝብም ሆነ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወደ ሰላም መሸጋገር የሚቻልበት ሁኔታ እንዲፈጠር የበኩላቸውን እንዲያደርጉ መጣር እንዳለባቸውና የሰላም ውይይትን መቃወም ጥንቃቄ እንደሚያሻው አመልክተዋል።

አቶ የሱፍ ኢብራሂም ዝርዝር ባያቀርቡም የጦር ሜዳው ጉዳይ መለወጡን በፊስ ቡካቸው ጽፈዋል። የስነልቦና አሸናፊነትን ተሸናፊነት ከሚያውጁ ሸፈጠኞች መቀማትና ከዚህ ስሜት መላቀቅ አግባብ መሆኑንን በመረዳት በግንባር ያላቸውን ምስክርነትና አይቀሬ ነው ያሉትን ድል አመላክተዋል። ብዙ መጨፈር እንደማያስፈልግ አጣቅሰው ባሳሰቡበት ትኩስ የፌስ ቡክ አውዳቸው ያሰፈሩት ሃሳብ የሚከተለው ነው።

ወራሪው ሀይል ይሄን ያክል የወበራው ሀሳብ ስላለው፣ አቅም ስላለውና ጀግና ስለሆነ አይደለም! በኛ በኩል ስራዎች ስላልተሰሩና በርካታ ክፍተቶች ስለነበሩ ነው።

ከድል በኋላ ሁሉም ነገር ኦዲት ይደረጋል ብለናል። ነገር ግን የትግል ቅደም ተከተል የሚባል ነገር አለ። አቋም የምንወስደው በድንገት ተነስተን ሳይሆን የግራቀኙን አቅም ከገመገምን በኋላ ሊሆን ይገባል።
ህዝባችን ላልተገባ ጉዳትና ምስቅልቅል ሰላባ መሆኑ አይካድም።

ነገር ግን ታግለን እናሸንፋለን፣ ይሄን መጠራጠር መብት ቢሆንም ማስቀረት አይቻልም። ይሄን የምንለው ደግሞ እየሰራን፣ እየታገልን እንጂ ታዳሚ ሆነን አይደለም። አቅሙና ችሎታው አለን። በህዝባችን እንተማመናለን—አቅሙን ባግባቡ በመጠቀም ወራሪውን ሀይል እንደክረምት አግቢ በወጣበት ማስቀረት ቀላል ጉዳይ ነው። ህዝባችን የጎደለውን ለይተን በንቃት እናስተባብራለን።

አሁን መሬት ላይ ያለው እውነታ በትክክል እየተለወጠ ነው። ሁሉንም ፍሬ ነገር የምናምነውና የምናረጋግጠው ምድር ወገብ ላይ ቆመን ባይናችን ወዲያና ወዲህ ካየን ብቻ ነው ለሚሉት አንጨነቅም። ከፊሉ የጠላት ሴራ ደጋፊ ሲሆን ከፊሉ በቋሚነት የስነልቦና ተሸናፊ ነው።

ወራሪው ሀይል የሆነ ቦታ ስለደረሰ ምን ይደረግ? ተጨባጭ የሆኑ ስራዎች መሰራት አለባቸው ማለት አንድ ነገር ሆኖ “ትላንት የተባለው አልተሳካም፣ ስለዚህ አሁንም አይሳካም፣ ሽንፈትን አምነን እንቀበል” ማለት ግን የለየለት ሸፍጥ ነው!

ጠላት ብቻችንን እንኳ ብንቀር እንደማይተወን ይታወቃል፣ ስለሆነም ብቻችንን እንኳ ብንሆን እንፋለመዋለን! በዚህ ደረጃ ቁርጠኛ ሆነን እንታገላለን፣ እየታገልን መስዋእትነት ብንከፍል ክብሩ ለራሳችን ነው።

ይሄን የምንለው የትግሉን አላማ ግዝፈት ለመግለፅ ያክል እንጂ ጠላት ማሸነፉ እንደማይቀር ከወሬኞች ውጭ ያለውና በግንባር የሚፋለመው የወገን ሀይልም ይሁን በሲቃ ውስጥ ያለው የጠላት ሀይል ጭምር በሚገባ ያውቁታል!

እለታዊ መረጃዎቻችን የሚያረጋግጡት ወራሪው ሀይል በከበባ ውስጥ ሆኖ በተገኘበት እየተመታ መሆኑን ነው። መስራት ያለብንን እና መሻሻል ያለባቸውን ጉዳዬች ለሀሜትና ለትዝብት ግብአት ይዘን አናቆይም። ተገቢ ርምጃዎች በወቅቱ እንዲወሰዱ ጥረት እናደርጋለን። ይህ አሰራር ወሳኝ ለውጦችን እንዳመጣ በሚገባ ተረድተናል።

አንድ ጦርነት በርካታ የውጊያ ግንባሮች እንዳሉት እናውቃለን። እስካሁን የነበሩትና የታዩት ችግሮች የራሳቸው ምክንያቶች አሏቸው። ችግሮቻችንን በመቅረፍ ጦርነቱን ማሸነፍ ብቸኛ አማራጭ ነው!

በተሸናፊነት ስነልቦና መሻሻል፣ ማሸነፍ ወይም ድል ማድረግ አይቻልም።
አጉል ፈንጠዝያ ጠቃሚ ያልሆነውን ያክል አጉል ፍርሀትም ጎጅ ነው!

ስራችንን እየሰራንና እየታገልን ድል እናበስራለን!

Exit mobile version