Site icon ETHIO12.COM

ካረን ባስ – አቋማቸውን አስተካከሉ፤ ጠ/ሚ አብይን በማንሳት ጉዳይ እንደማይስማሙ ይፋ አድረጉ

ከነገ ጀምሮ መላ ኢትዮጵያዊያንን በሃሰት ዘገባ ለማሽበርና መንግስትን ” በወሬ ዘመቻ” ለማስወገድ እቅድ መያዙና ይፋ በሆነበት ሰዓት ካረን ባስ “ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ከስልጣን አንስቶ የሽግግር መንግሥት ለመመስረት የሚደረገውን ሙከራ እቃወማለሁ” ማለታቸው ተሰማ። ድሉ የኢትዮጵያዊያ የዲፕሎማሲ ዘመቻና የጽናት ትሥር ውጤት እንደሆነ ታምኖበታል።

ወቅታዊ መረጃ በማሰራጨትና የሃሰት ቅስቀሳና ውዥንብርን በመከላከል ረገድ ከፍተኛ አስተዋጾ የሚያደርጉ ኢትዮጵያዊያን “አሜሪካ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የፕሬዝዳንት ባይደን መንግስት በሃገራችን ላይ የያዘውን የተንሸዋረረና ለአሸባሪው ወያኔ ያደላ አቋም ለማስለወጥ ከአደባባይ የተቃውሞ ሰልፍ አንስቶ እንደ ካረን ባስ ያሉ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣንን ፊት ለፊት ቀርቦ በመሞገት ከፍተኛ ትግል አድርገዋል፡፡ ዛሬ ካረን ባስ ያወጡት መግለጫ ቢዘገይም አቋሟቸውን እንድትለወጡ ይፋ ማድረጋቸው የዲፖሎማሲ ድል ነው” ብለዋል።

በፖለቲካዊ ድርድር፣ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም በወታደራዊ ኃይል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ከስልጣን አንስቶ የሽግግር መንግሥት ለመመስረት የሚሰነዘረውን ዛቻ እንደሚቃወሙ የአሜሪካ ኮንግረስ አባልና የኮንግረሱ የውጭ ጉዳይ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ካረን ባስ በግልጽ አስታውቀዋል።

ካረን ባስ በድረ ገጻቸው ዛሬ ባወጡት መግለጫ ይህን በህወሓትና ሸኔ የሽብር ቡድኖችና ሌሎች ተቃዋሚ ኃይሎች የሚሰነዘረውን ማስፈራሪያ እንደማይቀበሉት አመልክተዋል።

“በኢትዮጵያ አስተዳደራዊና የግዛት አንድነት ላይ የተቃጣውና የመላ ቀጣናውን ሰላምና ደህንነት የሚገዳደረው ይህ ግጭት በወታደራዊ መፍትሔ የሚፈታ አይደለም” ሲሉ ካረን ባስ በኃይለ ቃል ጭምር አስረግጠው ተናግረዋል። ካረንባስ በርካታ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን በሚኖሩበት የካሊፎርኒያ ግዛት ከምርጫ መዳረስ ጋር ህዝብ ሊቀጣቸው እንደሚችል የተረዱ ይመስላል።

Exit mobile version