Site icon ETHIO12.COM

አብይ አሕመድ ሚሳይል አመከኑ፤ ላይሊበላ፣ጋሸናና ሸዋሮቢት በሰዓታት ኦፕሬሽን ነጻ ወጡ፤ ዘመቻው ቀጥላሏል

በተለያዩ መገናናዎችና የመረጃ መረቦች አሜሪካ የምትመራዉ የሚዲያ ሚሳይል ኢትዮጵያ ላይ ከመተኮሱ በፊት በጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አሕመድ ድንገተኛ ውሳኔ መምከኑ ተሰማ። በአጭር ሰዓት ኦፕሬሽን ላይሊበላ፣ ጋሸናና ሸዋሮቢት በመከላከያ እጅ ገብተው ቃርሚያ እየተከናወናና ዘመቻው ወደፊት እንደቀጠለ ተሰማ።

አርቲስት ታማኝ ” ረክሶ የነበረው ቅዱስ ስፍራ ነጻ ወጥቷል። ድሉ ተጀምሯል” ሲል በቲውተር ገጹ ስሜቱን ገልጿል። የማጥቃት ዘመቻው በተጀመረ ሰዓታት ውስጥ ላይሊበላ፣ ሸዋሮቢትና ጋሸና መጽዳታቸው የሚያስፈነጥዝ እንዳልሆነ ተመልክቷል።

የአፋር መግናኛ ሰዎች እንዳሉት “ለጊዜው ስም አንተቅስም ከሌሎች የወገን ሃይሎች ጋር የምገናኝበት ስፍራ አለ” ሲሉ በጥምር ጥቃት እየተፈጸመ እንደሆነ አመልክተዋል። መውጪያ የሚባል ነገር እንደማይኖርም አመልክተዋል። ” ኢትዮጵያ ንጻ ሳትወጣ የሚቆም ነገር የለም” ሲሉ አመልክተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ደቡብ አፍሪካ ቤት ገዝተው እንደጨረሱና ወደዚያው ሊያመሩ መውሰናቸውን፣ የአገሪቱ ባለስልጣናት አገር ጥለው ለመውጣት በሩጫ ላይ መሆናቸውንና የኢትዮጵያ መከላከያም ሆነ ሌሎች ተዋጊዎች መሳሪያ እንዲያስቀምጡ ለማዘዝ የሚዲያው ሃይል ሱዳን እያሴረ ባለበት ” ከአገሬ በላይ” በለው ተቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ጦር ሜዳ እንደሚያቀኑ ይፋ ማድረጋቸው ኢትዮጵያ ላይ ሊዘንብ የነበረውን የፕሮፓጋንዳ ሚሳይል ማምከኑ ተጠቁሟል።

እዛቸው ብቻ ሳይሆኑ ጠቅላላ የብልጽግና ስራ አስፈሳሚ፣ እንዲሁም ሃይሌና ፈይሳን ጨምሮ መምህራን፣ የኪነት ባለሙያዎችና የቢሮ ሰራተኞች ” መሪያችንን እንከተላለን ማለታቸው፣ በግንባር ያለው ሰራዊት የአለቃው ወደ ግንባር መግባት ልዩ ስሜት እንደፈጠረባቸው መናገራቸው የታሰበው ሳይሆን ዜናው ያልታሰበ እንዲሆን አድርጎታል።

በዜና ፕሮፓጋንዳ ልትታመስ ዕቅድ ተይዞላት የነበረችው አዲስ አበባ፣ በፕሮፓጋንዳ ተይዛ ይህን ጊዜ እንደ ኮምቦልቻ ዝርፊያ እንዲፈጸምባት ተራ የወጣላት ደብረብረሃን በሸዋ ሮቢት ነጻ መውጣት ዜና፣ በላሊበላና ጋሸና ግንባር ድል ሃይላቸውን እያደሱ መሆኑ ተሰምቷል።

የአብን አመራር አቶ ዩሱስፍ ኢብራሂም ደሴና ኮምቦልቻን መልሰን እጃችን የምናስገባበት ቀናት በጣታቸው እየቆተሩ መሆኑንንባስታወቁ ቀናት ውስጥ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ግንባር ባመሩ ሰዓታት ውስጥ፣ ምክትል ኤታማዦር ሹሙ ” ውርድ ከራስ ” ሲሉ ጥብቅ መመሪያ ባስተላለፉ ቅጽበት የተገኘው ድል የዓለም ሚዲያ ሳይፈልግ ሟርቱን እንዲገታ አድርጎታል።

በውጭ አገር የህዝብ ጎርፍ በሃያ ሰባት ከተሞች ” ትህነግን አንፈልግም፤ እጃችሁን አንሱልን” ሲሉ ያሰሙትን ድምጽ ለመዘገብ ያነቃቸው ሚዲያዎች የላሊበላን ነጻ መውጣት ለመዘገብ አሁንም አልፈቀዱም።

ከተለያዩ ወገኖች እንደሚሰማው ከሆነ በሁሉም አቅጣጫ ማጥቃቱ ቀጥሏል።አቶ ጌታቸው ረዳ ላይሊበላ፣ ጋሸናና ሸዋ ሮቢትን በሰዓታት ውስጥ ስለመነጠቃቸው ያሉት ነገር የለም።

Exit mobile version