Site icon ETHIO12.COM

ሰሜን ሸዋ ፣ደቡብና ሰሜን ወሎ፣ ኦሮሞ ዞን ” የተዘረፈ እንዳይወጣ መንገድ ዝጋና …”፤ የትህነግ ሃይል እጅ እየሰጡ ነው

“ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ የተላለፈ ማሳሰቢያ” በሚል የተላለፈው ትዕዛዝ “በግንባርና በተወረሩ አካባቢዎች የምትገኙ መላው ሕዝባችን፣ ተደራጅታችሁ የዘረፈውን ንብረት በማስቀረት፤ መኪናዎቹ እንዳያልፉ መንገዱን በሙሉ በድንጋይና በግንድ በመዝጋት የአሸባሪውን ታጣቂዎች በቁጥጥር ሥር አውሏቸው፤ በየገደሉ፣ በየሸጡ፣ በየጫካው እየተደራጃችሁ ጠላት መግቢያ መውጫ እንዲያጣ በማድረግ፣ በምንም መልኩ ጠላት ወደኋላ እንዳይመለስ ባለበት እንድታስቀሩ ጥሪ ቀርቦላችኋል። አንድም ጠላት ወደ ኋላ ሸሽቶ ማምለጥ የለበትም። ወይ እጁን መስጠት አለበት ወይም ርምጃ ሊወሰድበት ይገባል” የሚለውን ያሰደመ ነው። ሙሉ ትዕዛዙ የሚከተለው ነው።

በሰሜን ሸዋ፣ በደቡብ ወሎ፣ በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞንና በሰሜን ወሎ አካባቢዎች ለምትገኙ ሁሉ፤ሀ/ ለሽብር ቡድኑ ታጣቂዎችጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችንና ሌሎች የጸጥታ ኃይሎች ባደረጉት ከፍተኛ ማጥቃት ጠላት ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ሆኖበታል። የቻለውን ዘርፎ፣ ያልቻለውን አውድሞ ለመሸሽ ጠላት እየሞከረ ነው። አሸባሪው ኃይል በምንም መልኩ ከገባበት አካባቢ ተገቢውን ቅጣት ሳያገኝ መውጣት የለበትም። ወይ ይማረካል፤ ወይ ርምጃ ይወሰድበታል።በመሆኑም፦

1. በተወረሩ አካባቢዎች የገባችሁ የአሸባሪው የሕወሐት አባላት፣ የመከላከያ ኃይላችን በከፍተኛ ሁኔታ የሕወሐትን ጦር እየደመሰሰ መሆኑን ዐውቃችሁ ሕይወታችሁን ለማትረፍ ስትሉ፣ በአስቸኳይ መሣሪያ አውርዳችሁ እጃችሁን እንድትሰጡ እናሳስባለን፡፡ ይህ ሳይሆን ከቀረ ግን ለሚደርስባችሁ ቅጣት ኃላፊነቱ የራሳችሁ ነው።

2. እጅ የሚሰጡ የአሸባሪው የሕወሐት አባላትን ሕዝቡ በክብካቤ ይዞ ለጸጥታ አካላት እንዲያስረክብ፤ የጸጥታ አካላትም በሕግና በሥርዓት እንዲይዟቸው ትእዛዝ ተሰጥቷል።ለ/ በተወረሩ አካባቢዎች ለምትገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች

ህ. በግንባርና በተወረሩ አካባቢዎች የምትገኙ መላው ሕዝባችን፣ ተደራጅታችሁ የዘረፈውን ንብረት በማስቀረት፤ መኪናዎቹ እንዳያልፉ መንገዱን በሙሉ በድንጋይና በግንድ በመዝጋት የአሸባሪውን ታጣቂዎች በቁጥጥር ሥር አውሏቸው፤ በየገደሉ፣ በየሸጡ፣ በየጫካው እየተደራጃችሁ ጠላት መግቢያ መውጫ እንዲያጣ በማድረግ፣ በምንም መልኩ ጠላት ወደኋላ እንዳይመለስ ባለበት እንድታስቀሩ ጥሪ ቀርቦላችኋል። አንድም ጠላት ወደ ኋላ ሸሽቶ ማምለጥ የለበትም። ወይ እጁን መስጠት አለበት ወይም ርምጃ ሊወሰድበት ይገባል።

ለ. ጠላት የጦር መሣሪያዎችን ይዞ ማምለጥ የለበትም። በየግንባሩ ያላችሁ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጠላት ይዞ የሚሸሸውን ማንኛውም የነፍስ ወከፍ መሣሪያ ጠላትን ማርካችሁ ወይም ደምስሳችሁ እንድትታጠቁ፤ የቡድንና ሌሎች መሣሪያዎችን ደግሞ ማርካችሁ ለመከላከያ እንድታስረክቡ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ዕዙ ያሳስባል፤ በምትኩ ሌላ የነፍስ ወከፍ መሣሪያ ይሰጣችኋል፤ ነጻነታችንን የምናውጀው በተባበረ ክንዳችን ነው፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

በመጨረሻም መከላከያ በማህበራዊ ገጹ ይፋ እንዳደረገው በርካታ የትህነግ ተዋጊዎች በቀረበላቸው ጥሪ መሰረት እጅ እየሰጡ መሆናቸውን አመልክቷል።

Exit mobile version