Site icon ETHIO12.COM

አብይ “አልቋል … እጅ ስጡ”አሉ

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ትህነግ በተሳሳተ መረጃ የበተናቸው ሃይሎች በሙሉ እጃቸውን በያሉበት እንዲሰጡ ጥሪ ቀረበላቸው። “ለአሸባሪው ሕወሓት የተሰለፉ ሁሉ እጃቸውን በሰላም ስጡ” ሲሉ ከዳሸና ግንባር አፋፍ ላይ ቆመው ጥሪ ያሰሙት የኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዝዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ናቸው።

“አገር መውደድን፣ ለስልጣን ሳይሆን ለሀገር መሞትን ከአብይ አሕመድ ተማሩ” በሚል በአረቡ ዓለም ከፍተኛ ታዋቂነት ያተረፈው ቱኒዚያዊው አንጋፋ ጋዜጠኛ ሳሊህ አልአዝረቕ በአደባባይ በርካታ ማስረጃ በማጣቀስ የመሰከረላቸው አብይ አሕመድ ” ለማይረባና መድረሻ ለሌለው ዓላማ የትግራይ ወታቶችን እየማገደ ያለው አሸባሪ ተሸንፏል” ብለው ነው ወጣቶች ዋጋ ለሌው ጉዳይ እንዳይሞቱ ጥሪ ያቀረቡት።

“ወራሪ” ያሉት ሃይል ዘራፊ፣ ለራሱም ለሴቶች ክብር የሌለውና የሚደፍር፣ ንብረትን የሚያወድም … እንደሆነ አመልክተው ” እኛ ክብራችንን እናስጠብቃለን” ሲሉ ያሰለፈው ሰራዊት ተደናብሮ እንደገባ ተደናብሮ ሊወጣ እንደማይችል፣ ይህም ተግባራዊ እንዲሆን በቂ ዘግጅት መደረጉን አብይ አሕመድ አመልክተዋል። ዳሸና ጠላት አለበት ያሉትን ተራራ በጣታቸው እያመላከቱ ” ነገ እንቆጣጠረዋለን፤ በምስራቅ ያገኘነውን ድል በጋሸና እንደግመዋለን” ባሉት መሰረት ጋሸና በወገን እጅ መውደቋ ይፋ ሆኗል።

በግንባር ተገኝተው በአንደኛው የጦር ግንባር የመጨረሻ ዕቅድ ላይ የመከሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአጠረ ጊዜና በአነስተኛ መሥዋዕትነት የኢትዮጵያ ድል የሚረጋገጥበትን መመሪያ እንደተሰጠ ባስታወቁበት የግንባር መልዕክታቸው “ሁሉም ዝግጁ ናቸው” ሲሉ ለሕዝብ ወቅታዊውን የአገር መከላከያና ድፍን የጸጥታ ሃይል ወቅታዊ ቁመና አስታውቀዋል። ሠራዊቱ በከፍተኛ ሞራል ላይ እንደሚገኝና ጠላትም እየተሸነፈ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለፁ ሲሆን፤ በተደናበረ ዕቅድ የገባው ጠላት ተደናብሮ የማይችልበት ምክንያትም ይህ እንደሆነ በተዘዋዋሪ ገልጸዋል።

ለአሸባሪው ዓላማ የተሰለፉ ሁሉ እጃቸውን በመስጠት ራሳቸውን እንዲያተርፉ፣ የትግራይ ወላጆችም “ልጆቻችን የት ደረሱ” ብለው እንዲጠይቁ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል። “የኢትዮጵያ ፍላጎት ሰላምና ልማት ነው፤ ወደዚህ ጦርነት የገባነው ተገድደን ነው ፤ ማሸነፋችን ግን አይቀሬ ነው” ሲሉ የኢትዮጵያን ድል አድራጊነት በተደጋጋሚ እንደሚናገሩት ደግመውታል። ከስር ሱሌማን አብደላ ታዋቂው የቱኒዚያ ጋዜጠኛ የተናገረውን ተርጉሞ እንዳቀረበው።

አገር መውደድን ለስልጣን ሳይሆን ለሀገር መሞትን ከአብይ አሕመድ ተማሩ። በአረቡ አለም ከፍተኛ ታዋቂነት ያለው አንጋፋው ጋዜጠኛ ቱኒሳዊ ሳሊህ አልአዝረቕ !

በዚህ የቴሌቪዥን ስክሬን ላይ የምታዩት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አሕመድ ነው። ይህ ሰው ስልጣኑን ለምትክሉ ሰቶ የወታደር ልብስ ለብሶ አማፂዎችን ፊትለፊት እየተዋጋ ነው።

ምናልባት ይህ ክስተት ለኛ አዲስ ሊሆን ይችላል። በተለይም በኛ በአረቦች ዘንድ አዲስ ክስተት ነው። በኢትዮጵያውያን ግን ይህ ተግባር የተለመደ ነው። ጀግንነት የራሳቸው ነው። ማንኛው የአረብ የፓርላማ አባል፣ ወይም መንግስት ባለሀብት ነው ስልጣኑን ጥሎ ለገአሩ ሊዋጋ ጫካ የወረደው ? ማንም የለም። እኛ ጋር ያለው እንደውም ከዚህ በተቃራኒው ነው። የቱኒዚያ መንግስት ስልጣን ለመውጣት ብሎ ያንን ሁሉ ህዝብ ጨፈጨፈ። የግብፁ ፕሬዚዳንት መንግስትን በሀይል ገልብጦ ሺዎችን ጨፍጭፎ ነው ደወ ስልጣን የመጣው። የየመኑ ፕሬዚዳንት አብዱረቦ መንሱ፣ የአገሩ ህዝቦችና ወታደሮች ከሁቲ አማፂዎች ጋር እየተጋጉ እሱ አገሩን ለቆ ፈርጥጦ እነሱ ታግለው እስኪያሸንፉ ሳኡዲ አረቢያ ሆቴል ውስጥ ተቀምጦ እየጠበቀ ነው።

አብይ አሕመድ ግን፣ ስልጣኑን አሽቀንጥሮ ለምትክሉ በመስጠት አማፂዎችን እየተዋጋ ነው። ምናልባት ውጊያ ላይ ሊሞት ሊቆስል ይችላል። ይህ ሰው ግን አገሩን ምን ያህል እንደሚወዳት ብቻ ሳይሆን የአገር ፍቅርን አገር ከስልጣን በላይ፣ ስልጣን ከአገር በታች መሆኑን ለመላው አለም ህዝብ አስተዋውቋል። የምዕራባውያን ተላላኪ ስርአት አገሬ ላይ ከሚሰፍን እዋጋለሁ ብሎ ለማንም የማይላላክ፣ መንግስት መሆኑን አሳይቶናል። ማነው የአብይ አሕመድን መንገድ የሚከተል..?.«.እርስ በርስ እያባሏችሁ ቁጭ ብለው ፀሀይ የሚሞቋችሁ መሪዎች ከዚህ መሪ ምን ትማሩ ይሆን.» ! አገር መውደድን፣
ለስልጣን ሳይሆን ፣ለአገር መሞተን ከአብይ አሕመድ ተማሩ !

ሱሌማን አብደላ

Exit mobile version