ETHIO12.COM

‹‹አሜሪካ በጅል ስህተቷ ምክንያት ስልታዊዋን ኢትዮጵያ አጥታለች›› የፖለቲካ ተንታኙ ቶማስ ማውንቴን

‹‹አሜሪካ በሰራችው የጅል ስህተት ምክንያት በኢራን ላይ ከሰራችው ስህተት በመቀጠል ወሳኟንና ስልታዊዋን ኢትዮጵያም በተመሳሳይ አጥታለች›› ሲሉ የፖለቲካ ተንታኙ ቶማስ ማውንቴን ገለጹ፡፡

ላለፉት 40 ዓመታት በተለይም በአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካ ላይ የተመራመሩትና የጻፉት ቶማስ ስሪላንካ ጋርዲያን በተሰኘ ገጸድር ላይ ሰፋ ያለ ሃተታን አስነብበዋል፡፡

በሃተታቸውም በአሜሪካ መንግሥት የሚደገፈው አሸባሪው ሕወሓት በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠውን የኢትዮጵያ መንግሥት ለማስወገድ ያደረገው ሙከራ መክሸፉን ተከትሎ አሜሪካ ስልታዊ አጋሯን ኢትዮጵያ የማጣት ዕጣ እውነታን ተጋፍጣለች ይላሉ፡፡

Photo የፖለቲካተንታኙቶማስማውንቴን

ይህ ስህተት በአውሮፓዊኑ 1979 አሜሪካ ኢራን ላይ ከፈፀመችው ቀጥሎ ትልቁ ጥፋት ነውም ይላሉ፡፡

የኢትዮጵያ ጥምር ጦር በረጅም ወራት የአሸባሪው ሕወሓት ወረራ የተያዙ ቦታዎችን በ10 ቀናት መልሶ ማጥቃት ነፃ እያወጣ መሆኑን የሚያስቀድመው ትንታኔ ጽሑፉ ኢትዮጵያ ለአሜሪካ የቀይ ባህርና ህንድ ውቅኖስ መግቢያው ባብልመንደብ ዓይነት የአፍሪካ ቀንድ ፖሊሷ እንደነበረች በመጠቆም ወሳኝና ስልታዊነቷን ያስከትላል፡፡

ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ከዚህ በኋላ ከአሜሪካ መራሹ ምዕራባዊያን ጋር የኒዮኮሎኒያሊዝም እሳቤ በተጫነው ግንኙነት መቀጠል እንደማትፈልግ ግልፅ አድርጋለች ያለው ጽሑፉ ከቻይና ጋር ጠንካራ የፖለቲካና የምጣኔሃብት ትስስር እየፈጠረች መምጣቷንም ያነሳል፡፡

የኒዮኮሎኒያሊስቶቹ ኃይል እንደሲኤንኤን ባሉ የፈጠራ ዘገባዎች የሽብር ቡድኑ ሕወሓት አዲስ አበባን ከበባ ውስጥ እንዳስገባት ወሬ በመንዛት በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠውን የኢትዮጵያ መንግሥት ለማሳነስ ጥረት ማድረጋቸውንም ጸሐፊው ያነሳሉ፡፡

ምንም እንኳን ጥረታቸው ባይሳካላቸውም በተመሳሳይ የአሜሪካ ኤምባሲም ዜጎቹ ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ውስጥ ለውስጥ ከሚያባብለው ባሻገር በ10 ቀን ውስጥ ብቻ ከ12 ጊዜ በላይ በማኅበራዊ ትስስር ገጾቹ ቢማጸንም ሰሚ አላገኘም፡፡

የሆነው ሆኖ የትግራይ ሕዝብ ሙሰኛና ገዳይ የሆነው የሕወሓት ሽብር ቡድን ሕዝቡን ምን ያክል ዋጋ እያስከፈለ እንደሆነ የመጀመሪያ ደረጃ ምስክር መሆን እንዳለበት የተንታኙ ጽሑፍ ይጠቅሳል፡፡ ይህን ደግሞ መንግሥት የተናጠል ተኩስ አቁም ወስኖ ከክልሉ ሲወጣ አሸባሪው ቡድን ጦርነቱን ወደአጎራባች ክልሎች በማስፋት አስመስክሯል ይላል፡፡ via walta

Exit mobile version