Site icon ETHIO12.COM

መንግሥት መር የሽግግር ጊዜ እንጂ የሽግግር መንግሥት አያስፈልግም፤

አቶ የሱፍ ኢብራሒም የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ምክትል ሊቀመንበር ይናገራሉ …‼️

👉 ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነጻነት ቀንዲልና መሰባሰቢያ ማዕከል መሆኗ ይቀጥላል፤ ሀገር ለማፍረስ የተሰለፉት ተስፈኞቹም ይሸነፋሉ፣

👉 ሀገር ለማፍረስ ህዝብን ለመበተን ዘወትር ዝግጁ የሆኑ ለዚህም ጠብመንጃውንም በጀቱንም ያዘጋጁ ኃይሎች በአንድ በኩል፤ በሌላ በኩል ማዕከላዊ መንግሥቱ እንዲጸና ኢትዮጵያ እንድትቀጥል የሚፈልግ በውስጡ ሰርጎ ገቦችና ኃላፊነታቸውን የማይወጡ ሰዎች ያሉበት ኃይል አለ፣

👉 ከመንግሥት ጋር የምንተባበረውና ስንተባበርም የቆየነው በሌላ ጎን ያለውን ኃይል ፍላጎትና አቅም ስለምናውቅ ነው፣

👉 መንግሥት መር የሽግግር ጊዜ እንጂ የሽግግር መንግሥት አያስፈልግም፤

👉 አሁን ከቀን ወደ ቀን የአሸባሪው ህወሓት ጀንበር እየጠለቀች ነው፤ ለቀጣሪዎቹ የገባውን ቃልኪዳን ማስጠበቅ የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሶ አጠቃላይ ግብዓተ መሬቱን እየጠበቀ ነው፣

👉 አሸባሪው ህወሓት ከውሸት የተወለደ ኢትዮጵያዊ እሴት የሌለው፤ የሐሰት ፕሮፓጋንዳ በመንዛት፣ ጽንፈኞችን በመፈልፈል ላይ የተመሰረተ ስምሪት ያለው፤ በህዝቦች መካከል በጎ ድንበር ተሸጋሪ ግንኙነቶች እንዳይኖሩ ለማድረግና የነበሩትንም ለማፍረስ ሰርቷል አሁንም ቢሆን የህንኑ ተግባር ነው እደገመው ያለው፣

👉 የአማራን ህዝብ ጠላቱ ያደረገው ተፈጥሯዊ በሆነው በመልክዓ ምድር አቀማመጡ ወደ ማዕከል በመምጣት ስርዓቱን ለማፍረስ ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ በቀላሉ አልፎት መሄድ የማይችለው ጎረቤት ክልል ስለሆነበት ነው፣

👉 እንደ አለመታደል ሆኖ እምነታቸውን በመብላት ከመሃል የደበቁትን ጠመንጃ በማውጣት መሐል ከተማ ላይ ሽብር በመንዛት ደሴና ኮምቦልቻ በሚፈርሱበት ጊዜ ታጣቂው ኃይል ከተማዎቹ ጫፍ እንኳን አልደረሰም፤ ሰርጎ ገቦቹ የልዩ ኃይሉንና የመከላከያ ዩኒፎርምን አስገብተውላቸው ያንን እየለበሱ እያምታቱ ሠርተዋል፣

👉 ከመከላከያ ጀርባ ገብተው በስንቅ አቀባይነትና በደጋፊነት አብረው ከሕዝቡ ጋር ተሰማርተው ‹‹በቦሩና በኩታበር ያለው መከላከያ እየፈረሰ ነው ፤ እናንተ ለምንድነው የምትለፉት!›› እያሉ ሽብር ሲነዙ ነበር፣

👉 እኔ አርፍበት የነበረውን ሆቴል የክፍል ቁጥሩን ሁሉ በመለየት በከባድ መሣሪያ አፍርሰውታል፣ እንቅስቃሴያችን ተጽእኖ አሳድሮባቸው ስለነበር በዘወትር ቃል አቀባያቸው በጌታቸው ረዳ ስማችንን እየጠቀሱ ዛቻና የማስፈራራት ስራን ሠርተዋል፣

👉 ያደረሰው ጥፋት ከድል በኋላ ሲመረመር ኢትዮጵያውያንና የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ሊያስደነግጥ ይችላል፤ ድሉ ግን የኢትዮጵያውያን የመሆኑ ጉዳይ ሳይታለም የተፈታ ነው፣

👉 የሁለቱ አሸባሪዎች የጥምረት ምንም አስደናቂ ነገር የለውም፤ ሁለቱም ኢትዮጵያን ማፍረስ የሚል ሀሳብ ይጋራሉ፣

👉 የኦሮሞ ማህበረሰብ ራሱ አትወክለንም ለአገራችንም ለሕዝባችንም የማትሆን ድርጅት ስለሆንክ በእኛ እግር ስር ልትሆን አትችልም በሚል ከመከላከያ ፣ ከልዩ ኃይሉና ከፋኖ ጋር በመሆን እርምጃ ወስዶበታል፣

👉 ኢትዮጵያ በአፍሪካ የነጻነት አርማ ፣ የጥቁር ሕዝቦች ተምሳሌት፣ ለቅኝ ግዛት ያልተንበረከከችና ያልገበረች አገር ስለሆነች ምዕራባውያኑ ታሪካችን አይመቻቸውም፣

👉 የኢትዮጵያ መንግሥት ኢትዮጵያዊነትን መሠረት ሲያደርግና ነጻነቷንና ታሪኳን በቅጡ እውቅና እየሰጠ ሲሄድ ተረብሸዋል፣

👉 በሕወሓት ስርዓት ወቅት ከፍተኛ መጎሳቆልና መጉደፍ የደረሰበት ኢትዮጵያዊነት ወደ ቦታው መመለሱ፤ አርበኝነት ቦታውን መያዙ ፤ የነጻነት ፍላጎትና ጣልቃ ገብነትን መከላከል እምቢተኝነት መደራጀቱ፤ የኢትዮጵያ ሉአላዊነት መሠረቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ የማንም ፍላጎትና ጣልቃ ገብነት ሊሆን እንደማይችል እየታየ ነው፣

👉 ሕወሓት ቀድሞም ተንበርካኪ ስለነበር በትጥቅ ፣ በመረጃና በገንዘብ የተወሰነ ድጋፍ ቢደረገለት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ይችላል በሚል ነው አብረውት እየተሰለፉ ያሉት፣

👉 የሽብር ቡድኑ ቀደም ሲል በፈጸማቸው ሰቆቃዎች ፣ ጅምላ ፍጅቶች ፣ አፈናዎች፣ እስራቶች፣ ግርፋቶችና ግድያዎች ከእነዚህ የውጭ ኃይላት ጉልህ ድምጽ ተሰምቶ አያውቅም፣

👉 ኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለው ርብርብ ተንበርካኪ አገር ለመመስረት ባላቸው ፍላጎት ነው፣

👉 ኢትዮጵያ በጂኦ ፖለቲካዊ ይዞታዋ በጣም አስፈላጊ አገር ስለሆነች በራሷ እግር መቆም ከጀመረች ስጋት ትሆንብናለች፤ ብለው ለቡድንና ለግለሰብ ጥቅም የሚንቀሳቀስ ኃይል ወደ ማዕከል ማምጣት ይፈልጋሉ፣

👉 አሁን ግንባር ቀደም ጉዳያችን የአገርንና የሕዝብን ህልውና አደጋ ላይ የጣለውን የሽብር ጥምረቱ በፈለገውና እየተንቀሳቀሰበት ባለው መንገድ በጠመንጃ ማንበርከክና ማሸነፍ ነው፤

👉 ከዚያ በኋላ ሕዝቡ እንደየፍላጎቱ ይወክሉኛል የሚላቸውን አደረጃጀቶች በማዋቀር አመራሮችን በመወከል ሰፊ አካታች ብሔራዊ ውይይትና ድርድር ይኖራል፣

አቶ የሱፍ ኢብራሒም የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ምክትል ሊቀመንበር ከዘመን መጽሔት ት ጋር በነበራቸው ቆይታ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችንና አሸባሪውን የህወሓት ቡድንን አሰመልክቶ ዝርዝር መረጃዎችንና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የዚህን ጽሁፍ ሙሉ መረጃ ለማግኘት ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ
👇
https://press.et/zemen/?p=174

Exit mobile version