Site icon ETHIO12.COM

ከትህነግ የዲያስፖራ ክንፍ – በውስጥ የተሰራጨ መልዕክት ” እንረጋጋ”

ፈተናው እንደከበደ መገመት አይከብድም።ፋሽስቱ ኣብይ ኣህመድ ህዝቡን አስተባብሮ ሰራዊቱን ይዞ መግጠሙ ከባድ እንደሚሆን አይጠፋንም። የድሮን ድብደባውም ከባድ ፈተና ነው። ብዙ ጉዳት ሳያደርስ አልቀረም::ኢሳያስም በተለይ በምእራብ ትግራይ ከባድ ጥፋት እያጠፋ ነው። ዙሪያችን ተከበናል። ይህንን ለአለም እየጮህን ነው ። አሁን ብንበለጥም አፈር ልሰን ተነስተን ልንደራጅና ልንመክት የምንችል እኛ ብቻ ነን።አዎ እኛ ተጋሩ።
እንደ ህዝብ አንድ ሆነን የምናስብ ከወደቅንበት ጠንክረን የምንነሳበት ስነልቦና ወኔ ያስፈልገናል።

የጁንታው የዲያስፖራ ክንፍ ቀንደኛ የፕሮፖጋንዳ መሪ የሆነው ካሳ ሃይለማርያም (የሊላይ ሃይለማርያም ወንድም) ይህንን መልዕክት በውስጥ ግሩፓቸው ለትህነግ ደጋፊዎች ብቻ ያስተላለፈው መልዕክት ነው። ፅሁፉ በትግርኛ ሲሆን ወደ አማርኛ ተተርጉሞ እንዲህ ቀርቧል።

“…. በስነ ልቦና ጦርነት እየተበለጥን ነው። እንረጋጋ እናስተውል።
በተደጋጋሚ ብንወያይበትም አልፈታነውም።ጠላቶቻችን እኛን የረዱ በመምሠል በየቀኑ እየፈለፈሉ በራሣችን ሠዎች በኩል እንዲነገረን ያደርጋሉ።
ከዚያም አንዳንዶቻችን የዋኆች ቅብል አድርገን የራሣችንን መንፈሥ መታወክ እንዳይበቃን በሙሉዓለም ያለን ትግራዋይ በበሬ ወለደ የጠላት ወሬ እንድንርበደበድ ወደ ማኅበራዊ ሚድያ እናወጣዋለን። ከዚያማ ወደ ሕዝባችንና ሠራዊታችን ይደርሳሉ። ይሄ ሽንፈት ነው። በውሸት ፕሮፖጋንዳ ለጠላት መንበርከክ ነው።ይሔን እነርሡ የገመዱልንን ተቀብለን ከህዝባችንና ከሠራዊታችን በተቃራኒው እየፈፀምነው ነው። እነርሡ እኮ ሢተርቱ “ጦር ያልፈታውን ወሬ ይፈታዋል “ይላሉ።
እንደ አባቶቻችን ረጋ እንበል ፣ እናሥተውል፣ ለ ደስታችንም ይሑን ለሀዘናችን ለፍርሀታችንም ጭምር ገደብ ይኑረው። ይሔ ገደብ የለሽ መንጫጫት ለጠላቶቻችን እንተውላቸው። ጠላቶቻችን ዋሽተው በዐለም ሕዝብ ፊት ወሸታም ሊያደርጉን እየሞከሩ ነው። እየተሳካላቸውም ነው።
በቀደም” መቃብር እየቆፈሩ ነው” በማለት በአለም ህብረተሰብ ፊት ወሸታሞችአደርጉን። ሣተላይት እንኳን የማያየው መቃብር የት እንደሆነ እንጃ።
ሰሞኑን በራሳችን ሰዎች በኩል የተነገረን ደግሞ “ሁሉም የቲ.ዲ.ኤፍ አባላት ያሉበት አካባቢ በካርታ እየተደገፈ ከነገ ጀምሮ ተከታታይ የአየር ድብደባ ይደረጋል የሚል ነበር።የማይደበደቡ ቦታዎችም ዝርዝር በመስጠት:-የመረጃው ምንጭ ከሚታመን
ከውስጥ ሠው ነው አሉን።ዝም አልን።
ዛሬ ያንን ሙሉ ዓለም የሰማውን መረጃ ይዘን ሰማይ ሰማይ እያማተርንና እየጠበቅን እያለ ሌላ ወሬ “ከማምነው ጓደኛዬ” በተገኘ መረጃ በሚል የጠላት ሀይል ሲቪል እየለበሰ የትግራይን ሰራዊት አሳልፎ ወደ ውስጥ በማስገባት በሗላ አንድበአንድ ሊለቅማቸው ነው ተብሎ በዚህ ክረምት እንደ በጋ እሣት ተቀጣጥሎ በየሰከንዱ ምድር ሰማይ መልዕክት በ መልዕክት ሆነች።
ይሀው አሁን ደሞ
ቲዲኤፍ ወደ መቀሌ መውጫ አጥቶ ተዘግቶበታል እያሉን ነው። በርካታ የትግራይ ወጣት አልቋልም እየተባልን ነው። ይሄ እየተባለው ያለው ግን በራሳችን ሰዎች መሆኑ ያበሳጫል። ቢሆን እንኳ ዝም ማለት ነው ያለብን። እንደ አሸናፊ ሆነን ነው መቅረብ ያለብን:: ምክንያቱም ፋሽስቱን አብይ ለድርድር ማምጣት የምንችለው አቅም እንዳለን በማሳየት ነው። የሰማነውን ሁሉ ብንናገርማ ነጮቹም አያግዙንም።የትግራይ ህዝብም ልጁን አይሰጠንም ነበር። ለዛነው ብዙ ነገሮችን ውጠን ማለፍ ያለብን። ጠላቶቻችን አቅም ቢያገኙና ኒኩሊየር ቦምብ ቢኖራቸው ከመተኮሥ ወደ ኋላ አይሉም።
የስለላ ሀይል ያለ አቅሙ ያለ ችሎታው ሽልማት እየሠጠን ብርቱ አደርገን “ሲቪል ለብሰው ተመሳስለው ሊጨርሱን ነው” የሚል ሽብር መስማት እንደገና መሸነፍ ነው። ቲዲኤፍ መውጫ አጥቷል ቢባልም እስቲ መጨረሻውን እንይ ማለት የኛ ፈንታ ነው።ፈተናው እንደከበደ መገመት አይከብድም።ፋሽስቱ ኣብይ ኣህመድ ህዝቡን አስተባብሮ ሰራዊቱን ይዞ መግጠሙ ከባድ እንደሚሆን አይጠፋንም። የድሮን ድብደባውም ከባድ ፈተና ነው። ብዙ ጉዳት ሳያደርስ አልቀረም::ኢሳያስም በተለይ በምእራብ ትግራይ ከባድ ጥፋት እያጠፋ ነው። ዙሪያችን ተከበናል። ይህንን ለአለም እየጮህን ነው ። አሁን ብንበለጥም አፈር ልሰን ተነስተን ልንደራጅና ልንመክት የምንችል እኛ ብቻ ነን።አዎ እኛ ተጋሩ። እንደ ህዝብ አንድ ሆነን የምናስብ ከወደቅንበት ጠንክረን የምንነሳበት ስነልቦና ወኔ ያስፈልገናል።
የዚህን የላቀ ክብርና ማንነት ትግራዋይ አናዋርደው።በጠላት ወሬ አንንጎድ። ሽንፈታችንን ለማንም አናጋራ። ፍርሀታችንን እንያዘው።እያሸነፍን መሆኑን ብቻ እንግለፅ።ህዝባችን ፅናት እንዲኖረው እናድርግ።ስለማሸነፍ ስለፅናት ብቻ እንውራ።
ጠላት በስነልቦና ጦርነቱ በልጦናል። ንነረጋጋ። ለሀዘናችን ለፍርሀታችንም ገደብ ይኑረን። በዛ ላይ ጠላት ባለ በለለ ሃይሉ እኛን ለማዳከምና ቲዲኤፍን ለመስበር መነሳቱን ግምት ውስጥ አስገብተን አቅማችን በፈቀደውና በምንችለው ሁሉ እንደጋገፍ እንተጋገዝ ። ይህን አጥብቀን ይዘን በአንድነታችን እንፅና።” ይላል ካሳ ሃይለማርያም!

ከደጀኔ አሰፋ የተወሰደ


Exit mobile version