Site icon ETHIO12.COM

ኦባንሳንጆን የገፉት ጌታቸው ረዳ ” ተከበናል” እያሉ ነው፤ ጥምር ሃይሉ በጥንቃቄ እየተራመደ ነው

“አውቀን፣ ወደንና ለሰላም ዕድል ለመስጠት ስንል ሃላችንን ከማራና አፋር ክልል አስወጣን” ሲሉ ያስታውቁትና ሃይላቸው ከነ ሙሉ አቅሙ ወደ ትግራይ መግባቱን ጠቅሰው ዶክተር ደብረጽዮን የላኩትን ደብዳቤ ተከትሎ አቶ ጌታቸው ረዳ ተከታታይ መረጃ እያሰራጩ ነው። በቲውተር ገጻቸው እንዳሉት ከሆነ አሁን ከበባ ላይ መሆናቸውን አምነዋል።

ጣምራው ጦር አላማታን ይዞ ወደፊት እየገፋ እንደሆነ በተጠቆመበት በአሁኑ ሰዓት አቶ ጌታቸው ” የኢትዮጵያ መከላከያ፣ የአማራ ተውዋጊዎችና የኤርትራ ወታደሮች የትግራይን ድንበር አቅራቢያ ተከማችተዋል። ለዳግም ጂኖሳይድ ነው” ሲሉ ማስታወቃቸውን የቢቢሲ አፍሪቃ ኤዲተር ዊል ሮስ አመልክቷል።

በቃለ ምልልሱ አቶ ጌታቸው የትግራይ ሃይሎች በጥምር ሃይሉ ጫና ውስጥ መውደቃቸውን እንዳመኑ ዊልል ሮስ አስታውቋል። ትህነግ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ መጠይቁን አቶ ጌታቸውን ጠቅሶ ዊል ሮስ በቲውተር ገጹ ጽፏል። አቶ ጌታቸውና ድርጅታቸው ኦባሳንጆ የጀመሩትን የሰላም ድርድርና የተኩስ አቁም ” አንቀበልም” በሚል ማጣታላቸው ይታወሳል።

አቶ ጌታቸው ዳግም ጄኖሳይድ እንደሚፈጸና መከበባቸው ጠቅሰው ለተናገሩት ” ተከበው ሊሆን ይችላል። ይህ ወታደራዊ ጉዳይ ነው። ነገር ግን ማንኛውም ኦፕሬሽን ከትህነግ ባህሪ አንጻር ክፍተት እንዳይሰጥና ህዝብ እውነቱን እንዲረዳ እጅግ ጥንቃቄ የተሞላበት ስራ እንደሚሰራ ጥርጥር የለውም” ሲሉ አንድ ሃላፊ ነግረውናል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሃይል በትግራይ ሕዝብ የሚወደ፣ ከትግራይ ሕዝብ ጋር ሰላማዊና ቤተሰባዊ ግንኙነት የነበረው፣ የተዋለደና አብሮ የኖረ እንደሆነ ያመለከቱት ሃላፊው ” የትግራይ ሕዝብ የሚነገረውን የሚሆነው እጅግ የተለየ እንደሆነ እንዲረዳ ሰፊ ስራ ተሰርቷል” ብለዋል።

የትግራይ ተቃዋሚ ሃይሎችና ትግራይ ብልጽግና እንደ ፓርቲ የራሳቸውን የቤት ስራ ካለፈው በመማር ማስራታቸውን በተደጋጋሚ ሲያስታውቁ መቆየታቸው ይታወሳል። በትግራይ ሕዝብ ለማነሳሳት ሃውዜን ላይ ትህነግ ህዝብ እንዲያልቅ አቀነባብሮ እንደነበር የድርጅቱ መሪ ዶክተር አረጋዊ በርሄና ነዋሪነታቸው አውስትራሊያ የሆነው የድርጅቱ የቀድሞ ከፍተና አመራር በተደጋጋሚ ማጋለጣቸውን የሚያስታወሱ የጥምር ሃይሉ እጅግ ጥንቃቄ የተሞላበትና ሕዝብን የሚከላከል ዘመቻ እንዲያካሄዱ በረካቶች እየመከሩ ነው።

ትህነግ በአፋርና በአማራ ክልል የፈጸማቸው ማናቸውም ተግባራት ከህዝብ ጋር ስለማይገናኙ ዘመቻው በህዝባዊነት እንዲሆን ቀና ዜጎች እየተመኙ ነው። የጥመር ሃይሉ ይህ ዜና ሲሰራ ከአላማጣ ወደፊት እያመራ መሆኑ ታውቋል። መንግስት ግን ማረጋገጫ አልሰጠም። አቶ ጌታቸው መከበባቸውን ሲገልጹ መቀለ አካባቢ ስለመሆኑ ያሉት ነገር የለም። የአፋር ሃይሎች ግን ከመቀለ 50 ኪሎሜትር ላይ ውጊያ እንደነበር ትናንት ገልጸው ነበር። እንሱኑ ጠቅሰን ዘግበን ነበር።


Exit mobile version