Site icon ETHIO12.COM

ጉተሬዝ – የሰላም ድርድሩ ውጤት እየታየበት ነው፤ በቅርቡ የተኩስ አቁም በይፋ ይታወጃል

በኢትዮጵያ ከዳር እስከዳር ሰላም የናፈቃቸው፣ የሞት፣ መፈናቀልና የውድመት ዜና እጅግ ያወካቸው ዜጎች “የሰላም ያለህ” ማለት የጀመሩት ገና ትህነግ ወደ መቀለ በሄደ በማግስቱ ነበር። አንድና ሁለት ሰዎችን በህግ ጥላ ስር ላለማዋልና ለህግ አሳልፎ ከመስጠት ይልቅ ጦርነት ቅድሚያ ወስዶ ሁሉም ነገር እንዳይሆን ሆኗል። ዛሬ እንደተሰማው ከዚህ ሁሉ ጥፋት በሁውላ ትህነግ የረገጠውን የሰላም አሳብ እየተቀበለ ሲሆን፣ የተኩስ አቁም ስምምነት እንደሚታወጅና አንዳንድ የንግግር አሳቦች ይፋ እንደሚሆኑ እየተጠቆመ ነው።

ህጻናት፣ እናቶች፣ አረጋዊያን እገሌ ከገሌ ሳይባል፣ በንብረትና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ በደረሰ ውድመትና ዘረፋ፣ በተፈጸመ የጅምላ ጭፍጨፋ፣ አስነዋሪ ተግባራት ሁሉም ዜጋ በሚባል ደረጃ ተቆጥቷል። አኩርፏል። ታሟል። አዝኗል። ወረራው ከተቀለበሰ በሁዋላ የሚወቱ መረጃዎች ሰብአዊነትን የሚፈታተኑ ቢሆንም፣ ሰላም ለራቃትና በቂም ፖለቲካ ተለውሳ መከራዋን ስታይ ለኖረች አገር አንድ መፍትሄ መምጣት ነበረበት። ይህ የሁሉም ሰላም ወዳድና ጤነኛ አሳቢዎች ጸሎትም ነው።

በትግራይ የመረጃ መስመሩ መዘጋቱ እንጂ ከፖለቲካው ፍልጎት እየተቀዳ ከሚፈሰው ፕሮፓጋንዳ በዘለለ፣ ከጥላቻና ቂም በራቀ ቢታሰብ በትግራይ ንጹሃን ዜጎች ላይ የደረሰባቸውና እየደረሰባቸው ያለው የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር እንቅልፍ የሚነሳ ነው።

ትናንት የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ከአፍሪቃ ሕብረት የቀጠናው ሹም ኦሊሴንጎ ኦባአሳንጆ ጋር የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀው የሰላም ተስፋው እጅግ ከፈተኛ መሆኑንን ገልጸዋል።

ለቀውስ ጠማቂዎችና፣ ከቀውስ ውስጥ ለማትረፍ ከሚሯሯጡ በስተቀር ዜናው በሁሉም ወገን ተስፋ የሚያሰንቅ ሆኗል። የደረሰው በደለ ማህበራዊ ፍትህና፣ ህጋዊ ፍርድ የሚሻው እንደሆነ ከሚነገረው ጎን ለጎን በኢትዮጵያ በመላው አገር ደረጃ በሚባል ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ከተያዘው ዕቅድ አንጻር ዜናው የሁሉንም ዜጋ ቀልብ የሳበ ሆኗል።

በፖለቲካው ዙሪያ የሚልከሰከሱ ይህን የሰላም ጅማሮ ለማኮላሸትና አገሪቱ ወደ ማያባራ ተጨማሪ ቀውስ እንድታመራ አማራና ኦሮሞ ደም እንዲፋሰሱ የሃሰት ዜና ማምረታቸውን ቀጥለዋል።

ትግራይ ደርሰው የመጡት ኦባሳንጆ “ የተሳካ የሚባል ውይይት አድርገው ተመልሰዋል። ደስተኞች ነን” የሚል ዜና ከትግራይ የወጣ ሲሆን ይህንኑ የሚያጠናክር ዜና ነው ዋና ጸሃፊው ይፋ ያደረጉት።

በሰሜን ዕዝ ላይ “ መብረቃው ጥቃት” እንደወሰዱና በደቂቃዎች ውስጥ ይህንኑ ጥቃት በድል እንዳጠቃለሉ በአደባባይ የተናገሩት የትህነግ ሃላፊዎች፣ ወደ ተንቤን ያወረዳቸውና አንጋፋ መሪዎቻቸውን ያጡበት ግጭት ለትግራይ ንጹሃን ከፍተኛ መርዶ ነበር። ከመርዶውም በላይ እጅግ ሰፊ ሰቆቃ ይዞባቸው እንደመጣ ከዛን ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን የሚወጡ መረጃዎች ምስክር ናቸው። ጥያቄ የሆነው “እንዴት ይህ ሰቆቃ ያቁም?” የሚለው ሆኖ ሳለ ትህነግ አማራና አፋርን ወሮ ሁሉንም የሰላም መንገድ በግፍና በጭካኔ ተግባሩ ዘግቶት ስለነበር ይህ የሰላም አሳብ ከቶውንም ይደመታል የሚል ግምት አልነበረም።

ከትህነግ ክንድ መዛልና ያቀዱት በስህተት የታጨቀ ዕቅድ ከፈነዳ በሁዋላ ከእርቅ ሌላ አማራጭ እንደሌላቸው የተሰማው “ አፈገፈግን” ሲሉ ሽንፈትን ለማስተባበል በይፋ የተኩስ ማቆም ውሳኔ እንዲወሰን የዓለምን ደጅ መቧጠጥ ሲጀመሩ ነበር።

በሕይወት ተርፎ ከተንቤን ተነስቶ ወደ መቀለ የተመለሰው የትህነግ አመራር “ ሂሳብ አወራርዳለሁ” በሚል ስሌቱ አስቀድሞ ያደራጀውንና አዲስ የመለመለውን ሃይል አሰልፎ በሳሳው የመከላከያ ሃይል ቁመና ላይ ዘመተ። ምስክሮች እንዳሉት፣ መረጃዎች ይፋ እንዳደረጉት፣ ሊስተባበል የማይችል የምስል መዛግብት እንደመሰከሩትና ገና እንደሚመሰክሩት ደብረሲና የደረሰው የትህነግ ሃይል እጅግ ሰፊ በደል፣ ውድመትን፣ ዘረፋና አጸያፊ ተግባራትን  ስለመፈጸሙ ክርክር የለም።

“በደልን በሌላ በደል፣ ቁስልን በሌላ ቁስል እያከኩ መኖር ዋጋው ረብ ነው” በሚል ይመስላል፣ አንድ ድሮን ለጥቃት በተሰማራ ቁጥር ሰባ አምስት ሺህ ዶላር የሚደፋው መንግስት በዚህ መልኩ መቀጠል ስለማይችል፣ የዓለም ዓቀፍ ጫናው መክፋትና ኢኮኖሚው ቆሌ እየራቀው መሄዱ መንግስት ሃሳቡን በሙሉ ወደ ሰላም ማተኮሩ አድሮም ቢሆን ተቀባይ እየሆነ መጥቷል።

አሁን ላይ በሶማሌ ክልል፣ በኦሮሚያ ቦረና፣ ድርቅ ክፉኛ ጉዳት እያደረሰ ነው። ተፈናቃይ ወገኖች በአፋርና አማራ ክልል እጅግ ሰፊ ድጋፍ ያሻቸዋል። ወደ ቀዬያቸው ሲሄዱም የሚያገኙት ባዶ መንደር ነውና መልሶ ማቋቋሙ እጅግ አስቸጋሪ፣ ፈታኝ፣ በቀላሉ ሊቀረፍ የማይችል እንደሆነ እየተገለሰ ነው። መሰረተ ልማትና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ የደረሰው ጥፋት በአሃዝ ሲቀርብ የሚፈጥረው የድንጋጤ ስሜት የሚያሳየው መልሶ ግንባታው ምን ያህል ውስብስብ እንደሚሆን ነው።

በዚህና በሌሎች ሰፊ ምክንያቶች፣ በኦሮሚያ እጅግ ውስን አካባቢ በአማራ ተወላጆች ላይ የሚደርሰው በደል ግፍና መፈናቀል፣ ግድያና ዘረፋ ሌላ መላ የሚያሻው ጉዳይ በመሆኑ በመላው አገሪቱ በተሳሳተ ትርክትና በተጋነነ ወግ የጎደፈውን ፖለቲካ ለማርቅ የእርቀ ሰላም ሂደት ማካሄዱ ለነገ እንደማይባል መንግስት አስታውቋል።

የዚህ በረከት ለትግራይ ወገኖችም አስፈላጊና ምን አልባትም ከማንም በላይ የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ መንግስት የሚከፈለውን ዋጋ ለመክፈል ለትግራይ ሕዝብ ቃለ በገባው መሰረት የሰላም ሂደት ተጀምሯል።

ውስጥ ውስጡን ሲሰማ የነበረው የሰላም ሂደት እያደር ይፋ መሆኑንን ተከትሎ የተለያዩ የስሜት መደበላለቆች ቢፈጠሩም፣ ሂደቱ ቀጥሏል። ችግርና ቀውስ እያመረቱ ሳንቲም የሚለቅሙ የደም ደላሎች አሁንም “ እንዴት ተደርጎ” በሚል ቢጮሁም መንግስት ሕዝብን እያሳመነና ባገኘው አገባብ ሁሉ እያስረዳ “ በጎ ሆኖ ያልቃል። እመኑን። በኢትዮጵያ ትቅም ላይ ድርድር የለም…” የሚለውን አቋማቸውን እያሰረጹ ናቸው።

ካሁን በሁዋላ ጦርነት መሸከም የማትችለው ኢትዮጵያ የሚከፈለውን ከፍላ በሆደ ሰፊነት እርቅ ታወርድ ዘንድ የርቅ ኮሚሽን እየመሰረተች መሆኗ፣ እሰረኞችን መፍታቷ፣ ለሰላም መቀየር፣ መስተካከልና መሻሻል የሚገባቸውን ጉዳዮች በሙሉ አንጥሮ በመለየት የአገሪቱን ሰው ሰራሽ የቀውስ መንስኤ ጉዳዮችን ሙሉ በሙሉ ለማስወገድ ቁረጠኛነት መኖሩን ያመላክታል። ይህ መከራና ሞት፣ ስደትና መፈናቀል ለሰለቸው ሕዝብ ታላቅ ተስፋ እየሆነ ነው።

ኦባሳንጆ ባለፈው ሳምንት ወደ አዲስ አበባና መቀለ በመጓዝ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣንትና ከትህነግ መሪዎች ጋር ውይይት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው። አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ከኦባሳንጆ ጋር የስልክ ውይይት ሲያደርጉ የተገነዘቡትን ሲናገሩ ሁለቱ ወገኖች ሰላም ለማውረድ የሚያስችል ጎዳና ላይ ናቸው።

የሰሜኑ ጦርነት አብቅቶ ሰላም ለማውረድ የሚረዳ ጥረት እየተደረገ መሆኑ መስማታቸው የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ሲያስታውቁ በኦባሳንጆ ዜና መደሰታቸውን  በመግለጽ ነው።

ዜናውን ልዩ የሚያደርገው የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪቃ ጉዳይ ረዳት የዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ሞሊይ ፊ አዲስ ከተሰየሙት በአፍሪቃ ቀንድ የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ሳተርፊልድ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ለመነጋገር አዲስ አበባ ከሚገቡበት አንድ ቀን ቀደም ብሎ መሆኑ ነው።

አሜሪካ “ ግጭቱ እንዲቆም አጥብቄ እሰራለሁ” በሚል በተደጋጋሚ ባስታወቀችው መሰረት፣ ከችግር ጠማቂነትና ከተጭበረበረ ዜና ማዝመት ተግባሯ ሙሉ በሙሉ ባትላቀቅም አይነህን ላፈር ሲሉዋቸው ለነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ፈልገው መደወላቸው የጦርነቱን መክሰም አመላክችና ማስረገቻ ቁልፍ ተደርጎ ተወስዷል። ከዚህ በተጨማሪ ትህነግ ትጥቅ እንደሚፈታና ወታደሩን እንደሚበትን ከስምምነት መደረሱ ለትህነግ እሬት እሬት እያለው የሚውጠው ሃቅ ቢሆንም የማይቀር መሆኑ መሰማቱ የሰላሙን ሂደት አይቀሬነት አጉልቶታል።

ጉተሬዝ ጦርነቱን ለማስቆም የኢትዮጵያ መንግሥትናና የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባርን በማስማማት ለግጭቱ ተጨባጭ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ ለማፈላለግ ተስፋ መኖሩን ኦባሳንጆ እንደገለጹላቸው በመግለጫቸው አስታውቀዋል።

ዋና ጸሃፊው  በአገሪቱ አንዳን አካባቢዎች እየተካሄደ ያለው የነፍጥ ግጭት ሰላም ለመውረድ ለሚደረገው ጥረት እንቅፋት እንደሆነ አመልክተዋል። አይይዘውም “በግጭቱ ተሳታፊ ወገኖች መካከል መተማመን ለመገንባት የሚወሰዱ እርምጃዎችን ያበላሻል” ሲሉም ደስታቸውን በገለጹበት ልክ ስጋታቸውን አስቀምጠዋል።

ድርጅታቸው ኢትዮጵያ በሁሉም አቅጣጫ ሰላም ለማስፈን እያደረገች ልታደርግ ያሰበችውን አካታች ውይይትና የሰላም ዕርቅ ሂደት እንደሚደግፍ ማረጋገጫ ሰጥተዋል። አያይዘውም ሁሉም ወገኖች ወደ ሰላም እንዲመጡ የሚያስችላቸውን ጎዳና ለመያዝ ግጭት እንዲያቆሙ ተማጽነዋል።

“በአፍሪካ ሕብረት የሚመራውን የሰላም ሂደት በታላቅ ተስፋ እየተከታተልን ባለበት ወቅት፣ በጦርነቱ በተጎዱ የተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ያለው የሰብአዊ ቀውስ ሁኔታ ያሳስበናል” በማለት፣ ሁሉም ወገኖች እርዳታ ለማቅረብ የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ጥረቶችን እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል። ዕርዳታ ይሰራጭ ዘነድ የዓለም አቀፍ ህግን ባከበረ መልኩ ሁሉም ወገኖች የበሉካቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።

በአባላ በኩል ትህነግ ጦርነት መክፈቱና ከባድ መሳሪያ እየተኮሰ የዕርዳታ ስርችቱን ሆን ብሎ ማስተጓጎሉ በተደጋጋሚ የሚገለጽ ሲሆን፣ ትህነግ በበኩሉ ያስተባብላል። አንዳንድ ውስጥ አዋቂዎች እንደሚሉት የተኩስ አቁም ስምምነት በቅርቡ ይፋ ይሆናል። አንድንድ የንግግር አጀንዳዎችና የሰላም አሳቦችም ይፋ ይሆናሉ።

Exit mobile version