Site icon ETHIO12.COM

ምስራቅ ወለጋ ስድስት ሰዎች ታገቱ፤ አምስቱ ተማሪዎች ናቸው

በምስራቅ ወለጋ በሸኔ የሽብር ቡድን 6 ግለሰቦች መታገታቸውንና ለማስለቀቅ እየሰራ መሆኑን መንግሥት ማስታወቁን የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ አስታወቀ።

ሸኔ አምስት ተማሪዎችንና አንድ በንግድ ሥራ የሚተዳደር ግለሰብን ጨምሮ በድምሩ ስድስት ሰዎችን በኦሮሚያ ክልል ማገቱን የፌደራል የደኅንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል ነው ያስታወቀው።

ግብረ ኃይሉ በላከው መግለጫ ታጋቾቹ ከአዲስ አበባ ወደ አሶሳ ሲጓዙ ምስራቅ ወለጋ ጎቡ ሰዮ ወረዳ ልዩ ስሙ ባፋኖ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ጥር 15 ቀን 2014 ከቀኑ 10 ሰአት አካባቢ በሽብር ቡድኑ ታፍነው መወሰዳቸውን አስታውቋል።

ከሽብርተኛው ትህነግ ጋር በመቀናጀት በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ሽብርና ትርምስ ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱት የሸኔ ቡድን ታጣቂዎች በፌደራል የደኅንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል እና በኦሮሚያ ክልል የፀጥታ አካላት በቅንጅት እየተወሰደባቸው ባለው እርምጃ እየተደመሰሱ መሆናቸውን መግለጫው ጠቁሟል።

የተበታተኑት የቡድኑ አንዳንድ ኃይሎች በየዋሻውና ጥሻው በመደበቅ በንፁሃን ላይ አስነዋሪ አፈናና እገታ መፈፀማቸውን ነው በመግለጫው ያመለከተው፡፡ ታጋቾችን የማስለቀቁ እንቅስቃሴም እየተካሄደ በመሆኑ፤ እርምጃዎችን ተከትሎ የሚገኘውን ውጤት በቀጣይ ለሕዝቡ እንደሚያሳወቅ በመግለጫው ጠቁሟል።

“ሸኔ ነን” በሙቱሉ አካባቢ ሁለት ወድማማቾችን ይዘው ለያንዳዳቸው መቶ ሺህ በድምሩ ሁለት መቶ ሺህ እንዲከፈላቸው ጠይቀው፣ ቤሰቦች አንድ መቶ ሺህ ብር ብቻ ማግነታቸውን ገልጸው ከላኩ በሁዋላ፣ በተላከው ገንዘብ ታላቅ ወደምን ከለቀቁ በሁዋላ ታናሽዬውን መግደላቸውን ችግሩ ለደረሰበት ቤሰብ ቅርብ የሆኑ ገልጸዋል።

በርካታ ተመሳሳይ ዜና እየወጣ ያለበት ኦሮሚያ የስድስት ወር የስራ አፈጻሰሙን ሲገመግም ከጸጥታና ሰላም ጋር በተያያዘ በቀጣይ ምን አቅጣጫ እንደሚከተል አላስታወቀም። በኦሮሚያ በንጽሃን ላይ የሚደርሰውን ስቃይና ግድያ አስመልክቶ ኦነግም ሆነ ኦፌኮ ድርጊቱን ሲኮንኑ አለመሰማቱ ጉዳዩን ይበልጥ አነጋጋሪ እንዳደረገው ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።

Exit mobile version