Site icon ETHIO12.COM

ኦሮሚያ ክልል “የግብርና ሽግግር ምክር ቤት” መሰረትኩ አለ፤ የስድስት ወር ክንወን ተመረመረ

ክልሉን በስንዴ፣በገብስ፣ በጤፍ፣በጥራጥሬ፣በቡና፣በአትክልትና ፍራፍሬን ጨምሮ በሰባት ክላስተሮች በማደራጀት በግብርና ዘርፍ እየተመዘገበ ያለውን ሽግግር ለማሳካት ምክር ቤቱ መቋቋሙ ተመልክቷል።

በኦሮሚያ ክልል በግብርና ዘርፍ እየተመዘገበ ያለውን ለውጥ ተቋማዊ የሚያደርግ የሽግግር ምክር ቤት ተመሰረተ። በክልሉ ግብርናን ለማዘመንና በተቋማዊ አደረጃጀት ለመምራት አላማ ያደረገ መድረክ በአዳማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳና የግብርና ሚኒስትር አቶ ዑመር ሁሴንን ጨምሮ የምርምር ተቋማት፣ ዩኒቨርሲቲዎችና የተለያዩ ድርጅቶች ተወካዮች እየተሳተፉ ነው። በመድረኩ የክልሉ ግብርና ሽግግር ምክር ቤት በይፋ ተመስርቷል።

ምክር ቤቱ የፌዴራልና የክልሉ የግብርና ምርምር ማዕከላት፣ዩኒቨርሲቲዎችና የምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዞች፣በየደረጃው ያሉ የግብርና ሴክተሮችን በአባልነት ያቀፈ ነው።

ክልሉን በስንዴ፣በገብስ፣ በጤፍ፣በጥራጥሬ፣በቡና፣በአትክልትና ፍራፍሬን ጨምሮ በሰባት ክላስተሮች በማደራጀት በግብርና ዘርፍ እየተመዘገበ ያለውን ሽግግር ለማሳካት ምክር ቤቱ መቋቋሙ ተመልክቷል።

የምክር ቤቱ መቋቋም የቴክኖሎጂ አቅርቦት፣መካናይዜሽን፤መስኖ፣ የተሟላ የኤክስቴንሽን አገልግሎት፣የገጠር ፋይናንስ አቅርቦት፣ገበያ ተኮር ምርቶች፣በምግብ ራስን መቻልና ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን ለማሳደግ አቅም እንደሚፈጥርም ተገልጿል።

ከውጭ የሚገቡ የግብርና ምርቶችን በአገር ውስጥ መተካትና የተፈጥሮ ሀብት ልማትና አካባቢ ጥበቃ ሥራዎች በምክር ቤቱ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሥራዎች መሆናቸውን አስታውቀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

በተመሳሳይ ዜና ክልሉ በአዳማ ሲካሄድ የቆየው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ማጠናቀቁን አመልክቷል። በግመገማው የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ፥ የክልሉን መንግስትና የፖለቲካና ግንባታ ሥራዎችን ተንትኖ ጠንካራ ጎኖቹን እና ክፍተቶቹ መለየቱ ተነግሯል። ኦቢኤን ከስፍራው እንዳለው በልማትና በፖለቲካው ዘርፍ ባለፉት ሦስት ወራት ህዝቡን በማሳተፍ በርካታ ስኬታማ ሥራዎች ተከናውነዋል።

ይህንን መላካም ውጤት ማስጠበቅና ማጠናከር እንደተጠበቀ ሆኖ የውስጥ ድክመቱን መለየቱን ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አስታውቀዋል። አያይዘውም የዞንና የወረዳ እንዲሁም የቀበሌ አመራና አደረጃጀት ላይ መዛነፍ ያሉባቸውን ቦታዎች በመለየት በዘመቻ ማጥራት እንደሚካሄድ ተሰምቷል።

Exit mobile version