Site icon ETHIO12.COM

አሚና መሐመድ – አገራዊ ንግግሩን አጎሉ፤ ዕርዕስ ዋጋው ስንት ነው?

“ጋብ ብሎ የነበረው የሚዲያ ዘመቻ እንደገና እያገረሸ ይመስላል። በተለይም በአማርኛ የሚተላለፉት ንብረትነታቸው የውጭ አገራት የሆኑት ሚዲያዎች በበቀል ተነስተዋል። ባለስልጣናቱም ለእነሱ መረጃ እየሰጡ የአፍራሽ ሚናቸው ተባባሪ እየሆኑ ነው” በማለት አቶ ሳህሉ የስጋት ይናገራሉ። አቶ ሳህሉ ይህን ያሉት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሐመድ የሰጡትን መግለጫ ተከትሎ የተዘገበውን ካስተዋሉ በሁዋላ ነው።

በመናበብ የሚፈጸመና አጀንዳ ቀራጭ፣ በጀት መዳቢ፣ አስፈሳሚና የማህበራዊ ሚዲያ አራጋቢዎች ያሉት የእምነት ቤት አመጽ የተጠመቀው ሆን አገሪቱ ወደ ሰላም እንዳታመራ የሚደረገው ዘመቻ አካል እንደሆነ በርካታ መረጃ እንዳለም እነዚሁ ወገኖች ይጠቁማሉ።

ትህነግ ሰሜን ሸዋ ዘልቆ መነኩሴ ሲደፍርና መነኩሴዋ “ቆቤን ጣልኩ፣ አረከሱኝ ” ብለው ሲያለቅሱ ያልተነፈሱ የሃይማኖት አባት፣ ለቀውስ ጠመቃው ግብዓት ይሆን ዘንዳ ” የተግባባንበት ጉዳይ የለም” ሲሉ ቀውስን የሚያባብስ መግለጫ የሚሰጡ የሃይማኖት አባት

አሚና መሐመድ በኮምቦልቻ፣ በአፋርና በትግራይ ጦርነቱ ያደረሰውን ቀውስ ከተጎጂዎች ጋር በመነጋገር ካገኙት ምስክርነት፣ የደረሰም ውድመትና የጅምላ መቃብሮች በአይነ ልቡናቸው ከሳሉ በሁዋላ፣ በተለይም ህጻናት፣ ሴቶችና አዛውንቶች ላይ የደረሰውን በደል ከዚህ ቀደም በስማ በለው ጭምር ሲቀርብላቸው ከነበርው ሪፖርት ጋር ካመዛዘኑ በሁዋላ የሰጡት መግለጫ መሆኑንን አብዛኞች ዘንግተዋል። እንደውም በዚህ ደረጃ ያሉ ከፍተኛ ባለስልጣን ረዘም ላለ ቀን ኢትዮጵያ ቆይተው ክትትልና ግምገማ ያደረጉበት ዋና ምክንያት በዝርዝር ማየትም አልተወደደም። እንደው በጀምላ ጉዳይ የደረሰባቸውን አካባቢዎች ጎበኙ ከመባሉ በቀር።

ነዋሪነታቸው አዲስ አበባ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ ቀበሌ አስር እንደሆነ የሚናገሩት የስነ ልቦና ባለሙያ በጽሁፍ በሰጡት ምላሽ እንዳሉት ለዚህ አሳባቸው መነሻ የሆናቸው የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ “ሕወሓት ሰርዶን አልቆረጠም” ሲል የዘገበው ዜናና ቢቢሲ አንድ ሃረግ መዞ ዜና ያደረገበት አግባብ ነው። የዜናዎቹ ዓላማም ሕዝብ ላይ ያለመረጋጋት ስሜት ለማጉላት የመናበብና ከሌሎች ለጊዜው ስማቸውን ከማይጠቅሷቸው ክፍሎች ጋር በስምምነት የሚሰራ ለመሆኑ ምስክር እንደሆነ ይገልጻሉ።

ትህነግ የጅቡቲ አዲስ አበባን መንገድ ሊቆርጥ እንደሆነ በዘገበ ሰዓታት ውስጥ ” አልተሳካለትም” ሲል ሃሳብንና ፍላጎትን እያስደነሰ ዜና የሰራውን የጀርመን ድምጽ የአማርኛ ክፍለ ጊዜ አቶ ሳህሉ ” የስብዕና ጉድፍ ያነቀዘው” ሲሉ ነቅፈውታል። አያይዘውም “በዚህ ማንነት እንዴትስ ልጆቻቸውን ያሳድጋሉ? እንዴትስ መሽቶ ይነጋላቸዋል” ሲሉ ይጠይቃሉ።

የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ሃይሎች ሰርዶን በመቁረጥ የጅቡቲን መንገድ ለመቁረጥ መቃረባቸውን ጠቅሶ መዘገቡ ይታወቃል። ዜናው ይህን ሲያሰፈር የፓርላማ አባላት፣ የተባበሩት መንግስታት ምክትል ዋና ጸሃፊ፣ በረካታ ባለስልጣናት እስፍራው ላይ በነበሩበት ወቅት ነው። ሰዓታት ቆይቶ ደግሞ “በአፋር ክልል ዳግም ውጊያ የከፈቱት የህወሓት ኃይሎች ወደ ጅቡቲ በሚወስደው አውራ ጎዳና ላይ የሚገኘውን ሰርዶን ለመቁረጥ ያደረጉት ጥረት አልተሳካም” ሲሉ ዜና አስነብቧል።

ምንም እንኳ የጦርነት ውሎ ተለዋዋጭ ቢሆንም የጀርመን ድምጽ ” የአፍሪካ ሕብረት መሪዎች አወሩ ተበተኑ” ሲል ኢትዮጵያ ያገነችውን ታላቅ ዲፕሎማሲያዊ ድል ለማራከስ መሞከሩንም ያነሱት አቶ ሳህሉ፣ ” የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ፈረሰች፣ ተበተነች፣ አለቀላት በሚል የጀርመን ድምጽን ጨምሮ ሲያሟርቱባት በነበረችው ኢትዮጵያ መደረጉ ያስገኘው ድል ከማንም በላይ ለነሱና አለቆቻቸው ግልጽ ነው” ብለዋል። አያይዘውም “ድሉ ስለገባቸው ከተቀጠሩበት ዓላማ አንጻር ጩኸት ማሰማታቸው ባይገርምም እንደ ዜጋ ሕዝብ ልብ ሊላቸው ይገባል። ከዚህ በላይ ባንዳነት የለም። ይህ አገር ላይ የተፈጸመ ክህደት ነው” ብለዋል። ሙያዊ ሽታ የሌለው የመቀለብ ጫናና በዛ ውስጥ የሚፈጠር የመንፈስ መድረቅ ውጤት እንደሆነም አመልክተዋል።

እሳቸው ባላቸው መረጃ የተባበሩት መንግስታት ( የሚዛናዊነቱ ጉዳይ ወደፊት የሚታይ ቢሆንም) ዓላማው ጦርነቱን ማስቆም ነው። ችግሩም በውይይት እንዲፈታ ማስቻል፣ እንዲሁም በአገሪቱ ይደረጋል የተባለውን አገራዊ ውይይት ማገዝ ነው።

አቶ ሳህሉ እንዳሉት “ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም የአገራዊ ውይይቱን ሂደት ቀጣይነት እንዲኖረው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ያደርጋል” ሲሉ ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሐመድ መናገራቸው ተደምጧል። ቢቢሲ አማርኛ “በኢትዮጵያ መንግሥትና በትግራይ አመራሮች መካከል ያለው ውይይት መቀጠሉን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ” የሚል ዕርዕስ የሰጠው ይህን የአሚና መሀመድ ንግግር ነው።

ብዙም ማብራሪያ ወይም እሳቸው በቀጥታ ተጠቅሰው የተናገሩት ፍሬ ጉዳይ ባልታየበትና ዜናው ትህነግና መንግስት እንደሚደራደሩ ለማጉላት የቀረበው የቢቢሲ ዜና “በእርግጥ ከጥቂት ወራት በፊት ከነበረው አንፃር አነስተኛ ግጭቶች ናቸው የሚታዩት” ማለታቸውን ከመግለጫቸው ወስዶ አስፍሯል። ዜናውን የሚወክል ጉልበት ያለው የሃላፊዋ ቃል ግን የለም። ቢቢሲ ለሰተው እርዕ የጻፈው ከታች በጥቅስ ውስጥ ያለውን ነው።

“ምክትል ዋና ፀሐፊዋ በጦርነቱ የተጎዱትን የትግራይ፣ የአማራና የአፋር ክልሎችን ከጎበኙ በኋላ ለሰላም ተስፋ እንዳለ የገለጹ ሲሆን “በእርግጥከጥቂት ወራት በፊት ከነበረው አንፃር አነስተኛ ግጭቶች ናቸው የሚታዩት” ብለዋል። ምክትል ዋና ፀሐፊዋ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “በአሁኑ ወቅት በእርግጠኛነት የተሻለ ቦታ ላይ ነን። ተጨማሪ ውይይቶችም አሉ” በማለት አስረድተዋል። ምክትል ዋና ፀሐፊዋ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “በአሁኑ ወቅት በእርግጠኛነት የተሻለ ቦታ ላይ ነን። ተጨማሪ ውይይቶችም አሉ” በማለት አስረድተዋል። ከትግራይ አመራሮች፣ ከአማራ እንዲሁም ከፌደራል መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ውይይት ያደረጉት አሚና መሐመድ ግጭቱ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል”

የመንግሥታቱ ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሐመድ በትግራይ፣ አማራ፣ አፋርና በሶማሌ ክልሎች የነበራቸውን ጉብኝት አጠናቀዋል። የጉብኝታቸውን መጠናቀቅ አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ በኢትዮጵያ በተፈጠረው ግጭት በርካቶች ላይ ጉዳት ደርሷል፤ ይህን እንዲያበቃና ህብረተሰቡን ለመታደግ ሂደት ላይ ያለውን አገራዊ ውይይት ቀጣይነት እንዲኖረው ማድረግ አጉልተዋል። መንግስትም አኩራፊው ብዙ በሆነበት አገር ይህን ውይይት ለማድረግ ዝግጅት መጀመሩ የአደባባይ ሚስጢር ነው። በርካቶች እንደሚሉት ኢትዮጵያን በቀናነት እንደገና ለመስራት መሰረት የሚጣልበት ይሆናል። ቀናነት!!

“በቀጣይ ኢትዮጵያ ልታከናውን ያሰበችው አገራዊ ምክክር ብሔራዊ መግባባትን የሚፈጥርና በአገሪቱ ላይ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን መፍትሄ እንደሚሆን ዕምነቴ ነው ” ሲሉ በስብሰባው አስፈላጊነት ላይ አጽንተው የተናገሩት አሚና፣ “በህብረተሰቡ ላይ እየደረሰ ያለውን አስከፊ ችግር ለመከላከልም ሁሉን አቀፍ አገራዊ ምክክር ያስፈልጋል። ለውጤቱም ኢትዮጵያውያን አስፈላጊውን ውይይት ያደርጋሉ ብዬ እጠብቃለሁ” ሲሉም ሕዝብ ላይ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

“ይህ የምክክር ሂደት የተሳካ ሆኖ እንዲቀጥልና ሰላም እንዲሰፍን ኢትዮጵያውያን አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርጉ እናምናለን፤ ለዚህ ሂደት መሳካትም አጋርነታችን እየገለጽን ድጋፋችንን እናደርጋለን። ተመድ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ያለውን ጦርነት በሠላም እንዲፈታ ጥረት ያደርጋል” በሚል ቃል በቃል ተናግረዋል። ጥረቱ ምን ምንን እንደሚያካትት አላብራሩም።

ዕርቅ የሚያባንናቸው፣ ይህ ሁሉ ሕዝብ እየሞተና እየተፈናቀለ አሁንም ጦርነትን ቅድሚያ የሚያደርጉ ክፍሎች ” መንግስት በሚስጢር እየተደራደረ ነው” በሚል ዘመቻ መጀመራቸው፣ የዚህ ዘመቻ አካል የሆነው የቤተክርስቲያን ውስጥ ቀውስ ተጋግሎ መቀጠሉን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ይናገራሉ። በመናበብ የሚፈጸመና አጀንዳ ቀራጭ፣ በጀት መዳቢ፣ አስፈሳሚና የማህበራዊ ሚዲያ አራጋቢዎች ያሉት የእምነት ቤት አመጽ የተጠመቀው ሆን አገሪቱ ወደ ሰላም እንዳታመራ የሚደረገው ዘመቻ አካል እንደሆነ በርካታ መረጃ እንዳለም እነዚሁ ወገኖች ይጠቁማሉ።

ትህነግ ሰሜን ሸዋ ዘልቆ መነኩሴ ሲደፍርና መነኩሴዋ “ቆቤን ጣልኩ፣ አረከሱኝ ” ብለው ሲያለቅሱ ያልተነፈሱ የሃይማኖት አባት፣ ለቀውስ ጠመቃው ግብዓት ይሆን ዘንዳ ” የተግባባንበት ጉዳይ የለም” ሲሉ ቀውስን የሚያባብስ መግለጫ የሚሰጡ የሃይማኖት አባት ያሏት ኢትዮጵያ ዜጎቿ በማስተዋል ካልሄዱና አገራዊ ምክክር አድርገው ችግራቸውን ካልፈቱ አገር አልባ ልንሆን እንችላለን ሲሉ አቶ ሳህሉ አመልክተዋል።

የመንግሥታቱ ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሐመድ ኢትዮጵያዊያን ለአገራዊ ውይይቱ ልዩ ትኩረት ሰጥተው ችግሮቻቸውን ሁሉን ባካተተ መልኩ እንዲቀርፉ ደጋገመው ያሳሰቡት ከዚሁ ፍራሃቻ ይሁን ሌላ የታወቀ ነገር የለም።

ምክትል ዋና ፀሐፊዋ “የግጭቱን አሳዛኝ መልክ በጉብኝቴ ወቅት ተመልክቻለሁ፤በተለያዩ ቦታዎች ለሚገኙ ዜጎች አስፈላጊውን የሰብዓዊ ድጋፍ ሊቀርብላቸው እንደሚገባ ከሁኔታቸው ተረድቻለሁም ፤ በጦርነቱ ትልቁ ተጎጂዎች ህጻናትና ሴቶች ናቸው ” ብለዋል።

“ችግር ውስጥ ስላሉ ዜጎችም ከተለያዩ የሰብዓዊ ሰራተኞች ጋር ተወያይቻለሁ የሰብዓዊ ድጋፉም ከዛሬ ጀምሮ መድረስ ያለበትና ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው” በሚል ባዩት አዝነው መግለጫ የሰጡት አሚና፣ ደጋግመው የአገራዊ ውይይቱን ሲያነሱ በምክንያት ነው።

አሚና እንደ ቀድሞ ሪፖርት አይቀርብላቸውም። ራሳቸው መረጃ ታጥቀዋል። ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ የአሚናን ቤት አሰራር በወጉ ስለሚያውቁ አስታጥቀዋቸዋል። ይህ ዜና ነው እንደ ዜና መጉላት ያለበት። ጄል ኦጋዴንን ማየታቸው ነው መጉላት ያለበት። መፍረሷ በቅብብል ሲታወጅባት በነበረች አገር በገላጣ ስፍራ በውሃ ዳንስ እየተዝናኑ እራት፣ በረሃ ለበረሃ እየዞሩ ምልከታ ማድረጋቸው ምንም እንኳን የተብለጨለጨ ነገር ሆኖ በመታየቱ ድሉ የገባቸው ቢያብዱበትም ታላቅ ስኬት መሆኑንን አቶ ሳህሉ ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ” የምንሰራው የሚገባቸው ለተላቶቻችን ነው። መከራውም የበዛው ለዚሁ ነው” ሲሉ መናገራቸውን አቶ ሳህሉ አስታውሰዋል። “የዕርዕስ ዋጋ ስንት ነው?” ሲሉም ጠይቀዋል።

Exit mobile version