Site icon ETHIO12.COM

“ራሳቸውን ልዩ የኢትዮጵያ ጠበቃ ያደረጉ መርጦ-አልቃሽ ሚዲያዎች የአንድነት ጠንቅ ናቸው” ኦሮሚያ

የኦሮሚያ ክልል ብስም ሳይዘረዝር “መርጦ-አልቃሽ ሚዲያዎች” ሲል በክልሉ ላይ በማይገባው ደራጃ ሆን ተብሎ የተከፈተበትን ዘመቻ አራከሰ። “ራሳቸውን ልዩ የኢትዮጵያ ጠበቃ ያደረጉ መርጦ-አልቃሽ ሚዲያዎች የአንድነት ጠንቅ ናቸው” ብሏል።

“ኃላቀርና ዘመኑን ያልዋጀ አስተሳሰብ በማራመድ ህዝብን ጭራቅ አስመስለው በመሳል በህዝቦች መካከል ግጭትና ጥላቻን ለመፍጠር እየታተሩ ይገኛሉ” ሲሉ ስም ሳይጠሩ ” መርጦ አልቃሽ” ያሉዋቸውን ሚዲያዎች ተችተዋል። “ጥላቻን የሚያራግቡ ጽንፈኞች፣ ጥላቻን የሚያሰራጩ፣ መርጠው የሚያለቅሱና የሚያስለቅሱ አንዳንድ ሚዲያያዎች ውሸት ማሰራጨትን ተግባራቸው ያደረጉ ይመስላል” ሲሉ ሆን ተብሎ በኦሮሞና በኦሮሚያ ላይ እየተካሄደ ነው ያሉትን የስም ማጥፋት ዘመቻ በምሬት አውግዘዋል። ክልሉ በዚህ ደረጃ አምርሮ ሲቃወም ይህ የመጀመሪያው ነው።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ኮሙነኪኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ በአጠቃላይ ክንውኖች ላይ መግለጫ ሲሰጡ እንዳሉት የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ከአጎራባች ክልሎች ጋር ያለውን ግንኙነት የወንድማማችነት ዕሴት ጠንካራ መሠረት ላይ ለመገንባትና ለማስረጽ እየሰራ ነው። ከሸኔ ጋርም የመጨረሻ የተባለ ዘመቻ በቅንጅት እየተከናወነ ይገኛል። ይሁን እንጂ ይህ ሃይል በተስፋ መቁረጥ ንጽሃን ላይ የሚወስደውን የግፍ እርምጃ ከልሉ ጋር እየተገናኘ የሚቀርበበት አግባብ ልክ እንዳልሆነ አመልክተዋል።

አቶ ሃይሉ አዱኛ “አንድ አንድ መርጦ አልቃሽ ሚዲያዎች በኦሮሚያ ክልሉ ህዝብና መንግሥት ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ እያካሄዱ ይገኛሉ” አያይዘውም ” ራሳቸውን የ’ኢትዮጵያዊነት ጠበቃ’ አድርገው የሚስሉ እነዚህ ሚዲያዎች ለኢትዮጵያ አንድነት የሚበጁ ሳይሆኑ በተቃራኒው የአንድነት ጠንቆች መሆናቸውን በተጨባጭ አሳይተዋል” ሲሉ አካሄዱ አገርን በሚጠቅም ደረጃ ልመዘን እንደሚገባ አመልክተዋል።

“ኃላቀርና ዘመኑን ያልዋጀ አስተሳሰብ በማራመድ ህዝብን ጭራቅ አስመስለው በመሳል በህዝቦች መካከል ግጭትና ጥላቻን ለመፍጠር እየታተሩ ይገኛሉ” ሲሉ ስም ሳይጠሩ ” መርጦ አልቃሽ” ያሉዋቸውን ሚዲያዎች ተችተዋል።

“ጥላቻን የሚያራግቡ ጽንፈኞች፣ ጥላቻን የሚያሰራጩ፣ መርጠው የሚያለቅሱና የሚያስለቅሱ አንዳንድ ሚዲያያዎች ውሸት ማሰራጨትን ተግባራቸው ያደረጉ ይመስላል” ሲሉ ሆን ተብሎ በኦሮሞና በኦሮሚያ ላይ እየተካሄደ ነው ያሉትን የስም ማጥፋት ዘመቻ በምሬት አውግዘዋል። ክልሉ በዚህ ደረጃ አምርሮ ሲቃወም ይህ የመጀመሪያው ነው።

ሰሞኑን በቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ አንድ ብሔር ብቻ ‹‹በጁምላ ተገድሏል›› በማለት ራሱ መንግስት ይፋ ያደረገውን ዜና ሃቅና መሰረቱን የለቀቀ ቅጥፈት የተቀላቀለበት እንደሆነ ገልጸው “አሸባሪው ሸኔ የህዝብ ጠላት እንደመሆኑ እየገደለ ያለው ህዝብን ነው። የሚገድለውም ብሔርን ሳይለይ ነው” ሲሉ ተናግረዋል። ሸኔ ግድያውን መፈጸሙ ይፋ የሆነው ሲቆጣጠረው የነበረውን አካባቢ እንዲለቅ ከተደረገ በሁዋላ መሆኑ ይታወሳል። ዜናውንም “የጅማላ መቃብር ተገኘ” ሲል አሃዝ ጠቅሶ ያሰራጨው ክልሉ እንደሆነ የሚታወስ ነው።

አስከፊው ድርጊት የተፈጸመበትን አግባብ ሚዛናዊነት በማሳት፣ ይባስ ተብሎ ውሸት በመቀላቀል የሚቀርበውን ዜና ” ህዝብን ጭራቅ አስመስለው በመሳል በህዝቦች መካከል ግጭትና ጥላቻን ለመፍጠር ነው” ብለዋል። ሸኔን ለመታገል ንጹሃን ዜጎች ሕይወታቸውን በየቀኑ እየገበሩ፣ የመንግሥት የአስተዳደርና ጸጥታ መዋቅር ውስጥ ያሉት ሰዎች መሥዋዕት እየሆኑና ቤተሰቦቻቸው ሳይቀር እየተገደሉ ባለበት ሰዓት እንዲህ ያለ ሚዛን የሳተ ጥላቻ ማራገብ ሸኔን ለመታገል እየተዋደቁ ያሉትን አካላት ከማንኳሰስ ተለይቶ እንደማይታይ ሃላፊው ገልጸዋል። “እነዚህ ሚዲያዎች ከተግባራቸው እንዲታቀቡ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ያሳስባል” ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

“የህዝብ ጠላት የሆነውን ሸኔ አሸባሪ-ቡድን ለማጥፋት፣ መንግሥት ከህዝብ ጋር ተቀናጅቶ እርምጃ ሲወስድ ቆይቷል፡፡ በዚህም ምክንያት ተጨባጭ ውጤቶች ተግኝተዋል። የክልሉ መንግሥት አሁንም ሸኔ የክልሉ ህዝብ ሰላም ስጋት እንዳይሆን አስፈላጊውን እርምጃ መውሰዱን ቀጥሏል” ሲሉ አቶ ሃይሉ አዱኛ አመልክተዋል። “በንጽሃን ሞት ኦሮሞ እንደሚደሰት፣ ክልሉ ልዩ ስሜት እንደሚሰማው አድርጎ ማቅረብ እንደ ሕዝብ ኦሮሞን መናቅ፣ ስብዕናውን መካድ፣ አብሮ የመኖር እምነቱን መሻር እንዲሁም በክልሉ ሰክኖ ወደ ላማት የገባውን ሃይል የመጎትጎት ያህል በመሆኑ ጥንቃቄ ያስፈልጋል” ሲሉ የክልሉ ካቢኔ አባል ቀደም ባሉት ቀናት መናገራቸው ይታወሳል። “እኚሁ ሰው አንድን ጉዳይ ሌሎችን ለጸብ ሳያነሳሳ መዘገብና ማስታወቅ እየተቻለ ለምን ግጭትንና ጥላቻን የሚያባብስ መንገድ እንደሚመረጥ አይገባኝም። መንስ እንዲሆን እንደምንመኝ አይረዳኝም” ብለዋል።

በቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ 168 ንፁሀን ዜጎች በኦነግ ሸኔ ግድያ እንደተፈጸመባቸው፣ከእነዚህ ውስጥም 87 ሰዎች በጅምላ ተገድለው አስክሬናቸው መገኘቱንና 81 ሰዎችም በተለያዩ የወረዳው አካባቢዎች መገደላቸውን መንግስት ማስታወቁ አይዘነጋም። ዜናው በርካታ ዜጎችን ያስቆጣና ያሳዘነ እንደነበርም ይታወሳል። ትህነግ ተመቶ ወደ መቀለ ካፈገፈገ በሁዋላ ሸኔ በርካታ ዜጎችን መግደሉና የሕዝብ መገልገያ ተቋማትን ማውደማና መዝረፉ፣ በተለይም የአማራ ተወላጆች ላይ ያተኮረ ጥቃት መፈጸሙን ምስክሮች ማንገራቸው ይታወሳል። ክልሉ ይህን ባይክድም ሆን ተብሎ እሱ እራሱ እንደሚያደርገው ተደርጎ መቅረቡ፣ ይህንን ሃይል በተበተነበት ሁሉ እየተከተሉ ማጥፋት አስቸጋሪ መሆኑንን መረዳት አለመቻሉና ዋጋ እየከፈሉ ያሉ አካላትን በጅምላ መፈረጁ ጥቅም የለውም፣ አግባብም አይድለም ባይ ነው።

የኦሮሚያ ብሮድካስቲን ኔት ዎርክ አቶ ኃይሉ አዱኛ የህዝቦችን እና ክልሎችን መልካም ግንኙነት ወንድማማችነትና ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑንን አመልክተዋል።የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ከአጎራባች ክልሎች ጋር ያለውን ግንኙነት የወንድማማችነት ዕሴት ጠንካራ መሠረት ላይ ለመገንባትና ለማስረጽ እየሰራ እንደሚገኝ ሲያስረዱ መንገድ እና ውሃ የመሳሰሉ መሠረተ ልማቶችን በመዘርጋት፤ በባህል፣ ቋንቋ እና ሚዲያ ላይ በመስራት፤ ኦ ቢ ኤን በተለያዩ የብሔር ብሔረሰቦች ቋንቋ የሥርጭት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ በትምህርት ዘርፍ በጋራ በመስራት፤ የ‹‹ኢፋ ቦሩ›› ትምህርት ቤቶችን በሶማሌ፣ አፋር፣ ጋምቤላ፣ ቤንሻንጉልና የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች ህዝቦችና ክልሎች ውስጥ እንዲስፋፋ በጋራ እየተሰራ ነው። በአስተዳርና ደህንነት ጉዳዮች ላይ በጋራ በመስራት ላይ ናቸው፡፡

በዚህም መሠረት በህዝቦች መካከል ወንድማማችነትን ለማጠንከር በአፋር ብሔራዊ ክልል በግጭት ምክንያት ለተጎዱ ዜጎች የሚደርስ 50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡ በሶማሌ ብሔራዊ ክልል በድርቅ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የ50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ መደረጉን ፣እንዲሁም በትህነግ አሸባሪ ቡድን በአማራ ክልል ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የሚሆን 100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ መደረጉን አስታውሰዋል።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የህዝቦችን ሠላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ብዙ ሥራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝያመልከቱት አቶ ሃይሉ፣ ከሠላምና መረጋጋት ሥራ በስተጓዳኝ እመርታ ያሳዩ የልማት ሥራዎችን በማከናወን ላይ መሆንንና ክልሉ በአንድ እጅ ልማት ላይ በመሰማራት በሌላ እጅ ደግሞ አሸባሪዎችንና ጽንፈኞችን እየተፋለመ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። በሸኔ ላይ ከመከላከያና ከክልል ዩ ሃይሎች ጋር በመሆን ሰፊ የማጽዳት ስራ እየተሰራ መሆኑንን መከላከያ ማስታወቁ አይዘነጋም።

የኃይማኖች ጽንፈኝነት በተመከተ ከኃይማኖት ጀርባ በመደበቅ ሥውር ፖሊቲካ የሚያራምዱ ቡድኖች የኃይማኖት ግጭቶችን ለማምጣት እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ አቶ ሃይሉ ይፋ አድርገዋል።

የብሔር ጽንፈኝነት – አሸባሪው የሸኔ ቡድን በህዝቦች ላይ እያደረሰ ያለውን አሰቃቂ የሽብር ተግባር፣ ጽንፈኞች በመንግሥት የተቀነባበረና በአንድ ብሔር ላይ ብቻ ያተኮረ አስመስለው የጥላቻ ፖለቲካ በማራገብ የህዝቦችን ወንድማማችነት ላይ የተመሠረተ ግንኙነት ለመናድ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያ ህዝብ ለጽንፈኞች የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ ጆሮ ሳይሰጥ የወንድማማችነት ዕሴቱን ይበልጥ ሊያጠናክር ይገባል፡፡

Exit mobile version