ETHIO12.COM

አፍሪካ ሕብረትና ኢጋድ ሸኔንና ትህነግን በይፋ በአሸባሪነት እንዲፈርጁ ዝግጅት እየተደረገ ነው

በኢንተርናሽናል የአሸባሪዎች ዳታ ቤዝ ላይ አሁን ድረስ ስሙ ተተክሎ የሚገኘው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር / ትህነግ በኢጋድ ቀጥሎም በአፍሪካ ሕዝብረት በአሸባሪነት ሊፈረጅ እንደሆነ ተሰማ። አፍሪካ ህብረት ለምስራቅ አፍሪቃ መልዕክተኛ አድርጎ የሾማቸው የቀድሞ የናይጀሪያ ፕሬዚዳንት ሪፖርት ማቅረባቸው ተሰምቷል።

ከዚህ በላይ የሚገኘው መረጃ በዓለምአቀፉ የአሸባሪዎች ቋት ተመዝግቦ የሚገኝ የህወሃት ወንጀል ዝርዝር ነው።

ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ለአዲስ አበባ ዘገባቢያችን እንዳስታወቁት ትህነግ ወደ ሰላም መድረክ እንዲመጣ የቀረበለትን “የትጥቅ ፍታ” ጥያቄ እንደማይቀበል ባስታወቀ ማግስት የአፋር ክልልን ዳግም መውረሩ ነገሮች እንዲከሩበት አድርጓል።



የወሬው ምንጭ እንዳሉት ቀደም ሲል በአማራ ክልል ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ሳይቀሩ በመሰከሩበት ደረጃ በሽብርተኛነት ሊያስፈርጁ የሚችሉ ተግባራትን መፈጸሙ በማስረጃ ተያዟል። ከዚያም በተጨማሪ ሸኔ በይፋ ከትህነግ ጋር መስራቱ ካወጀበትና ከዛም በፊት ጀምሮ ሰላማዊ ዜጎችን በማሸበር፣ በመግደል፣ በሰላም እንዳይኖሩ በማፈናቀል፣ በመዝረፍ፣ በማፈንና በመሰወር ተናበው እንደሚሰሩ መረጃ ቀርቧል። ምስክሮችም ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ቀደም ሲል ጀምሮ ትህነግ ለምስራቅ አፍሪቃ ስጋት እንደሆነ ሲጠቆም ይሰሙ የነበሩ አገራት አሁን ላይ በኢጋድ ደረጃ ትህነግ በአሸባሪነት እንዲፈረጅ ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። የዜናው ባለቤቶች እንዳሉት የሚጠበቀው የኦባሳንጆ ሪፖርት ግምገማ ብቻ ነው። ትህንግና አጋሩ ሸነኤ በኢጋድ አሸባሪ ተብለው ከተፈረጁ በሁዋላ የአፍሪካ ሕብረት በቀጣይ ውሳኔውን ከፍ አድርጎ ያጸድቀዋል የሚል እምነት አለ።

ትህነግ ሻዕቢያን በመጀመሪያ ቢጋድ፣ ቀጥሎ በአፍሪካ ሕዝብረት አሸባሪ አድርጎ ማስፈረጁና በተባበሩት መንግስታት ማዕቀብ እንዲጣልበት፣ ከዓለም ተገልሎ እንዲቀር ማድረጉ ይታወሳል። ከረዥም ጊዜ በሁዋላ ሻዕቢያ አሸባሪ ስለመሆኑና ከአሸባሪ ጋር ግኝኙነት ያለው ድርጅት ስለመሆኑ ማስረጃ እንደሌለ ተተቅሶ ቅፍደዳው እንደተነሳለት ይታወሳል።

ጅቡቲ አሁን ባለው የትህነግ እንቅስቃሴ ስጋት ላይ የወደቀችና ሃይሏን በተጠንቀቅ ያቆመች አገር መሆኗን የሚያነሱ፣ ኬንያ ሸኔንና በድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ አሸባሪ ድርጅቶችን ለመዋጋት ከኢትዮጵያ ጋር መስማማቷ። የመከላከያ ኤታማዦር ሹም ሱዳን በዝግ መክረው መመለሳቸውና ከሱዳን የላዕላይ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢና የፈጥኖ ደራሽ ሃይል አዛዥ ጋር የተደርገው ሚስጢራዊ ስምምነት በትህነግ ላይ ያጠነጠነ ጉዳይ ስለመኖሩ ማረጋገጫ መሆኑን በርካቶች በደፈናው አስተያየት ሲሰጡበት ነበር።

የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ “ህወሓት” እና “ሸኔ” በሽብርተኝነት ፈርጇል፡፡ ቡድኖቹን በሽብርተኝነት ለመፈረጅ የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ ምክር ቤቱ በ1 ድምፀ ተዓቅቦ እና በ312 የድጋፍ ድምፅ ማጽደቁ አይዘነጋም።

የተጠቀሱት ቡድኖች በንጹሃን ዜጎች ላይ ጭምር ሲፈፅመኑ የቆዩት አሁንም እየፈፀሙ ያሉት ድርጊት የሽብርተኝነት ወንጀል መሆኑን የውሳኔ ሀሳቡ ያስረዳል፡፡ ውሳኔው በምክር ቤቱ ከመፅደቁ በፊት ሽብርተኛ አይደለሁም ብሎ ማስረጃ ይዞ የሚቀርብ አካል ካለ በሚል ምክር ቤቱ ጥሪ ቢያደርግም በጊዜ ገደቡ ማስረጃ ይዞ የቀረበ አካል እንደሌለም የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በወቅቱ ማስገንዘባቸው፣ በምክር ቤቱ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡ ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡት የፌዴራል ዋና ዐቃቤ ሕግ ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቲዎስ ሽብርተኛ ተብለው የተፈረጁትን ቡድኖች በገንዘብ የረዱ፣ በሚዲያ የሚያግዙ፣ አመራርና አባል የሆኑ በህግ ይጠየቃሉ መባላቸው ይታወሳል።

የዜናው ሰዎች እንዳሉት ውሳኔው ከጸናና በአውሮፓ ህብረት ተቀባይነት ካገኘ፣ ለድርጅቶቹ መዋጮ ሲከፍሉ የነበሩ አባሎቻቸው በጎፈንድ ዳታ ቤዝ ዝርዝራቸው ተለቅሞ ለሚኖሩበት አገር ይተላለፋል ብለዋል። ከዚያ በሁዋላ ጉዳዩ ምን እንደሚሆን የሚታይ እንደሆነም አመልክተዋል።

በኢትዮጵያ ከፖለቲካ ጥያቄም ሆን አጀንዳ ጋር ግንኙነት የሌላቸውን ሰላማዊ ዜጎችን ማወክ፣ ማፈን፣ መግደል፣ ማፈናቀል፣ መዝረፍ፣ ይህንኑ እንደ ድል በማህበራዊ ሚዲያ ማሰራጨት፣ ለዚሁ ስራ በቅስቀሳና በአካል ተዋናይ የሆኑትን ድርጅቶች በገሃድ በገንዘብ መደገፍ ላለፉት አራት ዓመታት እጅግ የተለመደና በርካቶችን ያሳዘነ ጉዳይ ሆኗል።

Exit mobile version