ETHIO12.COM

“የምንሰራው የሚገባቸው ጠላቶቻችን ናቸው”አብይ አሕመድ፤ የሩሲያ ባህር ኃይል ልዑክ የኢትዮጵያ የባህር ሃይልን ጎበኘ

የሩሲያ ፌዴሬሽን ባህር ኃይል ልዑክ መሪ በኢትዮጵያ የሩሲያ ፌዴሬሽን ተልዕኮ ሀላፊ ሜጀር ጀነራል ኦስትሪ ኮቭ በበኩላቸው ፣ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል በመዋቅራዊ አደረጃጀቱ ይበልጥ እየዘመነ እንዲመጣና ኢትዮጵያውያን በጋራ የሚኮሩበት ጠንካራ ተቋም ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን መገንዘባቸውን ተናግረዋል ፡፡
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ጠንካራ ባህር ኃይልና የመከላከል አቅሟን ይበልጥ ለመገንባት በምታደርገው ሁሉ አቀፍ እንቅስቃሴ ውስጥ በተለያዩ የሥልጠና መስኮች ላይ ሚናዋን መጫወት ትችላለች ተብሏል ፡፡

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ወደ ስልጣን እንደመጡ ያልተለመደ ንግግር ብቻ ሳይሆን ለመረዳት የሚያስቸግር ስራም ጀምረዋል። አንዱና ዋና የሩሲያ ፌዴሬሽን ባህር ኃይል ልዑክ የጎበኘው የኢትዮጵያን የባህር ኃይል ዳግም ግንባታ ነው። ግርምቱ ደግሞ ትህነግ ወደብ አልባ ያደረጋት አገር፣ ትህነግ የባህር ሃይሏን ያፈረሰባት አገር ለምን የባህር ሃይል አስፈለጋት? የሚለው ጉዳይ ነው።

ቃል በቃል መንግስት ባይናገርም የበሻሻው አብይ መንበር እንደጨበጡ አየር ሃይልን ማዝመን፣ ባህር ሃይልን መልሶ መገንባት፣ የፈርሰውን የአየር ወለድ ዳግም ማዋለድ ነበር። እኚህ መሪ እንደሚሆኑ አውቀው በዝግጅት የኖሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ህልማቸው ዕውን በሆነ ማግስት “አምላክ ኢትዮጵያና ሕዝቧን ይባርክ” በማለት ስራ በጀመሩ ወር እድሜ ነበር ዘመናዊ የጦር ጀቶች፣ የባህር ላይ የጦር መርከብ ግዢ ስምምነት ማከናወናቸውና ፣ መለስ ዜናዊ አወላልቀው የጣሉትን ባህር ሃይል መልሶ ለማቋቋም እየሰሩ መሆናቸው በደማቅ ዜና የተሰማው።


Landlocked Ethiopia to Rebuild its Navy The French-Ethiopian military agreement (March 2019)On March 13, 2019, Ethiopia and France reached their first military cooperation agreement, a deal which includes helping Ethiopia build a navy.


ኢስራኤል ደፈንስ የተሰኘ ገጽ “ Landlocked Ethiopia to Rebuild its Navy” በ14.03.2019 ኢትዮጵያና ፈረንሳይ ጥልቅ ስምምነት ማካሄዳቸውን ሲያስነብብ ” Ethiopia established its navy in 1958. In the 1970s, the Imperial Ethiopian Navy was Africa’s leading naval force. When Eritrea gained independence in 1991, Ethiopia suddenly found itself landlocked without a coastline and so it disbanded its navy.” ከ1958 ዓም ጀምሮ ኢትዮጵያ የገነባችው ባህር ሃይል በ1970 ዎቹ በአፍሪካ ግንባር ቀደሙ እንደነበር ያወሳል። አያይዞም ኤርትራ ነጻ አገር ስትሆን ኢትዮጵያ የባህር በር አልባ አገር እንደተደረገች አመልክቶ የባህር ሃይሏም መንኮታኮቱን ይነገረናል።

አብይ ኢትዮጵያን እንደተረከቡ በእልህ የገነቡት ትህንግ አፈር ያለበሰውን ይህን እውቁን የባህር ሃይል ነበር። ለዚህም ፈረንሳይ ከስልተና መሳሪያ አቅርቦትና ቴክኒክ ድጋፍ የዘለለ ድጋፍ፣ እንዲሁም ግብይት ልተፈጽም ስምምነት ተደርሶ ባህር ሃይል ነፍሱ ተመለሰ። ይህ ሁሉ ሲሆን “የትኛው ባህር ላይ” የሚለው ጥያቄ ቁርጥ ያለ ምላሽ ባያገኝም ጅቡቲ፣ ቀይ ባህርም ሶማሊያና ኬንያን እንደ አማራጭ አቅርቦ ጽሁፉ አትቷል።

“እረፍት አልባ” የሚባሉት አብይ አህመድ ለውጡ ያሰቡትን እንዳይተገብሩ ገና ከጅምሩ በርካታ መሰናክል ቢያሸክማቸውም፣ ከለየላቸው ጠላቶች ይልቅ ሳይገባቸው ለሚበጠብጧቸው ” የምንሰራውን የሚረዱት ጠላቶቻችን ናቸው” ሲሉ በተደጋጋሚ ሳይገባቸው የሚበጠብጡ አደብ እንዲገዙ በተደጋጋሚ ወትውተው ነበር። ዓለም ከአንድ የወንበዴ ስብስብ ጋር ተጣምሮ በመናበብ አብሮ የዘመተባቸው እሳቸው እንዳሉት ምን እየሆነ፣ ምን እየተሰራ እንደሆነ ስለገባቸው ይሆን? ዳግም የኢትዮጵያን መከላከያ፣ አየር ሃይልና የባህር ሃይል ለማፍረስ ከዚሁ የሽፍታ ስብስብ ጋር የሚዶለተው ስለምን ተብሎ ነው? ይህን ጥያቄ ለመመለስ እሳቸው እንዳሉት ያልገባቸው ረጋ ብለው ሊመረምሩ ይገባል።

በአፍሪካ የአውሮፓ አገራት የጋራ ስብሰባ ላይ የፈርንሳዩን መሪ አግኝተው የመከሩት አብይ አሕመድ፣ ፈረንሳይ አድማውን ተቀላቅላ ከኢትዮጵያ ጋር የገባችውን ውል ስለማቋረጧ አንስተው መነጋገራቸውን ከግምት በላይ የሚናገሩ፣ ፈረንሳይ በሩን ስለቆለፈችበት የዚሁ የባህር ሃይል ዳግም ግንባታ ጉዳይ አቋሟን ስለመቀየሯ አድሮ የሚሰማ ይሆናል።

“ከሌሎች ሀገሮች የባህር ሃይሎች አደረጃጀትና ቀደም ሲል ከነበረ የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ልምድ በመውሰድ የተሰጠንን ሀገራዊ ተልዕኮ በአግባቡ ለመፈፀም የሚያስችል የተሟላ አደረጃጀት ፈጥረን ወደስራ ገብተናል”

በባህር ሃይል መልሶ ግንባታ ከሩሲያ የጦር መርከበ እንደገዛች የሚነገርላት ኢትዮጵያ ከሶማሌና ኤርትራ ጋር ከገነባችው ነገር ግን አሜሪካና አውሮፓውያኑንን ካንጫጫው ህብረት ጋር በተያያዘ ነገሮች ወደ ጫፍ እየሄዱ መሆኑን አመላክች መረጃዎች እየወጡ ነው። የትህነግ ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ” ዋጋ የለህም፣ እጅህን ለጀግናው የትግራይ ሃይል ስጥ፣ ማለጫ የለህም …” ሲሉት የነበረው የኢትዮጵያ መከላከያ ሁሉንም ተረት አድርጎ ጡንቻውን አፈርጥሞ የባህር ሃይሉን ወደ ስራ ሊያስገባ ከዳር ማድድረሱን ሰሞኑንን ሲያስታውቅ ነበር።

ለዚህም ይመስላል የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ዋና አዛዥ ተወካይ ኮሞዶር ዋላፃ ዋቻ ፣ የኢትዮጵያ ባህር ሃይል የዛሬ ሶስት አመት በአዋጅ መቋቋሙን ገልፀው ፣ ክፍሉን በተማረ የሰው ሃይል ለማደራጀት ሥራዎች እየተሰሩ ያሉ መሆኑን ዛሬ ለስራ ጉብኘት አዲስ አበባ ለገቡትን ለሩሲያ ልዑካን ቡድን ማስታወቃቸውን የመንግስት ሚዲያዎች ያመልከቱት።

የሩሲያ ፌዴሬሽን ባህር ኃይል ልዑክ መሪ በኢትዮጵያ የሩሲያ ፌዴሬሽን ተልዕኮ ሀላፊ ሜጀር ጀነራል ኦስትሪ ኮቭ በበኩላቸው ፣ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል በመዋቅራዊ አደረጃጀቱ ይበልጥ እየዘመነ እንዲመጣና ኢትዮጵያውያን በጋራ የሚኮሩበት ጠንካራ ተቋም ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን መገንዘባቸውን ተናግረዋል ፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ጠንካራ ባህር ኃይልና የመከላከል አቅሟን ይበልጥ ለመገንባት በምታደርገው ሁሉ አቀፍ እንቅስቃሴ ውስጥ በተለያዩ የሥልጠና መስኮች ላይ ሚናዋን መጫወት ትችላለች ተብሏል ፡፡

የሩሲያ መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ለረጅም አመታት የዘለቀ መልካም ዲፕሎማሲያዊ ትብብር ያለው ሲሆን፣ የዚህም ጉብኝት ዓላማ የዚሁ ትብብር አንድ አካል መሆኑም ተመልክቷል፡፡

“ከሌሎች ሀገሮች የባህር ሃይሎች አደረጃጀትና ቀደም ሲል ከነበረ የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ልምድ በመውሰድ የተሰጠንን ሀገራዊ ተልዕኮ በአግባቡ ለመፈፀም የሚያስችል የተሟላ አደረጃጀት ፈጥረን ወደስራ ገብተናል” ያሉት ኮሞዶሩ አያይዘውም ኢትዮጵያ ከባህር ኃይሏ ማግኘት የሚትችለውን ጥቅምና ግልጋሎት እንድታገኝ ከሩሲያ ፌደረሽን ባህር ሃይል በተለያዩ የስልጠና ዘርፎች በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰናል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የማህበራዊ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡

Exit mobile version