Site icon ETHIO12.COM

የአፍሪካና የአውሮፓ ህብረት ሀገራት አሸባሪው ትህነግ ላይ እርምጃ እንዲወስዱ ተጠየቀ -“ስልጣን ከያዘ ጀምሮ የፈጸመው ወንጀል ይጣራ”

brhane tplf

የአፍሪካ ህብረትና የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት አሸባሪው ህወሃት ለፈፀመው ግፍ እርምጃ እንዲወሰድበት ማድረግ አለባቸው ሲሉ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበራት አስታወቁ። በአፍሪካ ሕብረትና በኢጋድ በኩል ትህነግንና ሸኔን በሽብርተኛነት እንዲፈረጁ እየተሰራ መሆኑ መሰማቱ ይታወሳል።

በአውሮፓ የሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበራት ዛሬ ባወጡት መግለጫ የአፍሪካ ህብረትና የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት አሸባሪው ህወሃት በአፋርና በአማራ ክልሎች ለፈፀማቸው ግፎች እርምጃ እንዲወሰድበት እንዲያደርጉ ጠየቁ።

ሁለቱ ህብረቶች የሰው ልጆች መብቶችን በሚጥሱ ኃይሎች ላይ እርምጃ በመውሰድ የግንኙነታቸውን መርሆ ማክበር እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የህወሃት አመራሮች ኢትዮጵያን ለ30 ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ በአገዛዝ ስር እንዳቆዩዋት በኋላም በህዝብ ታቃውሞ ከስልጣን ሲባረሩ ወደ ትግራይ በመሸሽ ህዝቡን መሸሸጊያ እንዳደረጉት መግለጫው አትቷል።

ይህ ቡድን የሰዎችን በነጻነት የመንቀሳቀስ፣ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ እና የሀሳብ ብዝሃነትን ጨምሮ መሰረታዊ የሰው ልጆች መብቶችን ሲረግጥ እንደቆየም ጠቅሷል።

የሽብር ቡድኑ በቅርብ ጊዜ እንኳን መንግስት ያደረገውን የተኩስ አቁም በመጣስ በአፋርና በአማራ ክልሎች ወረራ ማካሄዱን ያስታወሰው መግለጫው በወረራውም አሰቃቂ ግፎችን መፈፀማቸውን አብራርቷል።

በሰላማዊ ዜጎች ላይ ግድያ፣ በሴቶችና ህጻናት ላይ አስገድዶ መድፈር፣ በማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትና መሰረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ውድመት አድርሷል ብሏል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ፤ የሽብር ቡድኑ ለእንስሳት እንኳን የሚራራ ልብ እንዳልነበረው በመጥቀስ እንስሳትን ከአካባቢው አርሶ አደር ከመዝረፉም ባለፈ በጥይት እየተኮሰ መግደሉን አብራርቷል።

የዳያስፖራ ማህበራቱ መግለጫ አሰቃቂ ግፎችን የፈፀመው አሸባሪው ህወሃት ተጠያቂ መሆን እንዳለበት በመጥቀስም የሽብር ቡድኑ የፈፀማቸውን ማስረጃዎች እንደሚከተለው አቅርቧል፦

አሸባሪ ቡድኑ ወደ አገዛዝ ከመጣበት 1983 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ለፈጸማቸው ግፎችም ገለልተኛ ምርመራ በማካሄድ የማያዳግም ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድበት ጠይቋል።

ኢፕድ

Exit mobile version