Site icon ETHIO12.COM

“መከላከያ በማህበራዊ ሚዲያ እየተመራ ወደእርምጃ አይገባም” ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

ጉልበታም መሆን አለብንና አየርኃይላችን በሚቀጥሉት 7 ዓመታት የአፍሪካ የብቃት መዕከል እንዲሆን እየሰራን ነው

የሀገር መከላከያ ሠራዊት በማህበራዊ ሚዲያ እየተመራ ወደ እርምጃ አይገባም። የእራሱ የተጠና አካሄድን ይከተላል ሲሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አስታወቁ።

የኢፌዲሪ አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ የላቀ የግዳጅ አፈፃፀም ላስመዘገቡ እና የቆይታ ጊዜያቸውን ላጠናቀቁ የሠራዊት አባላትና አመራሮቹ የሜዳሊያ የማዕረግ ማልበስና ሽልማት መርሃ ግብር አካሂዷል።

በዚህ መርሀ ግብር ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ “መቀሌ ለምን አትገቡም የሚለውን ብቻ አንሰማም። የትግራይ ሕዝብ አጥፊዎቹ ልጆቻችን ናቸው እያለ ባለበት መግባቱ መጠፋፋት ነው። ነገር ግን የትግራይ ሕዝብ ተቃውሞ ማሰማት መጀመሩም መረሳት የለበትም። ይህን ተቃውሞው ተጠናክሮ ሲቀጥል እኛም በተጠናከረ መልኩ ዕርምጃችንን እናካሂዳለን” ሲሉ ተናግረዋል።

አሁን ዕድል የሰጠነው ይህ አጥፊ ቡድን መለስ ብሎ እንዲያስብ ነው ካልሆነ ግን በኃይልም እርምጃ ብንወስድ የሚከለክለን የለም ብለዋል።

ሕወሓትም ተጠናክሮ ይመጣል የሚለው እሳቤ አሁን አይሰራም። መከላከያም በተጠናከረ ሁኔታ እራሱን አደራጅቶና ስትራቴጂካዊ ቦታዎችን ተቆጣጥሮ አየጠበቀ ነው ብለዋል።
በጌትነት ተስፋማርያም

ጉልበታም መሆን አለብንና አየርኃይላችን በሚቀጥሉት 7 ዓመታት የአፍሪካ የብቃት መዕከል እንዲሆን እየሰራን ነው – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

ጉልበታም ሆነን መገኘት ስላለብን አየር ኃይላችን በሚቀጥሉት 7 ዓመታት የአፍሪካ የብቃት ማዕከል እንዲሆንና በአፍሪካ አይደፈሬ ማዕከል እንዲሆን እየሰራን ነው ሲሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ።

የኢፌዲሪ አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ የላቀ የግዳጅ አፈፃፀም ላስመዘገቡ እና የቆይታ ጊዜያቸውን ላጠናቀቁ የሠራዊት አባላትና አመራሮቹ የሜዳሊያ የማዕረግ ማልበስና ሽልማት መርሃ ግብር አካሂዷል።

በወቅቱ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፤ ጉልበት ከሌለህ ማንም ተነስቶ ሊፈነጭብህ ይነሳል። በመሆኑም ጉልበታችንን ገንብተን መቆም አለብን ብለዋል።

ለዚህም አየር ኃይሉ መዘመን እንዳለበት እናምናለን። አየር ኃይላችን በሚቀጥሉት 7 ዓመታት የአፍሪካ የብቃት መዕከል እንዲሆንና በአፍሪካ አይደፈሬ ማዕከል እንዲሆን እየሰራን ነው ብለዋል።

አየር ኃይል በንጉሱ ጊዜ በአፍሪካ ግንባር ቀደም ነበር በደርግም እንደዛው ጠንካራ ነበር የሕወሓት ስርዓት ግን አየር ኃይሉ ማሰልጠን የማይችል የተንጋደደ አድርጎት ነበር። ይህ ኢትዮጵያን የማዳከም ሴራ ነበር።

አሁን አየር ኃይሉ ተጠናክሮ ኢትዮጵያን በሚመጥን መልኩ እንዲገነባ ተደርጓል። የሌሎች አገራትን ባለሙያዎች ተቀብለን ማሰልጠን እንችላለን የአውሮፕላኖቻችን ቁጥርም እንዲጨምር ተደርጓል ሲሉ ተናግረዋል።

(ኢ.ፕ.ድ)

Exit mobile version