Site icon ETHIO12.COM

«ፑቲን ስልጣን ላይ መቆየት አይችሉም አሉ» ጆ ባይደን ክሬምሊን አይመከታችሁም ብሏል

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፤ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ስልጣን ላይ መቆየት አይችሉም አሉ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ “ይህ በባይደን የሚወሰን አይደለም፤ የሩስያ ፕሬዝዳንት የሚመረጡት በሩሲያውያን ነው” ብሏል። ነገሩ የትርጉም ጉዳይ ነው ሲል ዋይት ሃውስ አስተባብሏል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፤ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ስልጣን ላይ መቆየት አይችሉም ማለታቸው ተስመቷል።

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ይህንን የተናገሩት በፖላንድ በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉት ስደተኞች በጎበኙበት ወቅት መሆኑም ታውቋል።

ባይደን በከፍኛ ችግር ውስጥ የወደቁ ስደተኞችን ከጎበኙ በኋላ በዋርሶው የሮያል ካስትል ፊት ለፊት በሚገኘው ስፋራ ባድረጉት ስሜት የተቀላቀለበት ንግግር “ፑቲን በስልጣን ላይ መቆየት የማይችል ጨካኝ መሪ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም “ቭላድሚር ፑቲን ከዚህ በኋላ አንድ ኢንች የኔቶ ግዛቶችን መውረር አይችልም”፤ መቼም ቢሆን ሩሲያ ድል መቀዳጀት አትችልም” ሲሉም ተናግረዋል።

በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ከሶስት አስርት ዓመታት በፊት ዩክሬናውያን ለነጻነታቸው ሲያደርጉት ከነበረው የፀረ-ሶቪየት ጦርነት ጋር ያነጻጸሩት ፕሬዝዳንቱ፤ ለዩክሬናውያን “ከእናንተ ጋር ቆመናል” የሚል የአጋርነት መልእክትም አስተላልፈዋል።

ባይደን “በዚህ ጦርነት ውስጥ ግልጽ መሆን አለብን፤ ይህ ጦርነት በቀናት ወይም በወራት ውስጥም ቢሆን የሚያልቅ አይደለም፤ ስለዚህም በዚህ ትግል ውስጥ ለረጅም ጊዜ ለመሳተፍ አሁን መወሰን አለብን” ሲሉም ለአጋሮቻቸው ጥሪ አቅርበዋል።

የባይደን ንግግር ታድያ የሩሲያ ባለስልጣናትን ጨምሮ በርካቶች በሩሲያ በቀጠይ ሊኖር ስለሚችል የስርዓት ለውጥ ጋር በመያያዝ እየተቀባበሉት ይገኛሉ።

የክሬምሊን ሰዎች በጉዳዩ ላይ በሰጡት ምላሽ “ባይደን ይህን የማለት ምንም ስልጣን የላቸውም” ሲሉ ተድምጠዋል። የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ “ይህ በባይደን የሚወሰን አይደለም፤ የሩስያ ፕሬዝዳንት የሚመረጡት በሩሲያውያን ነው” በማለት የባይደን አስተያየት ውድቅ ማድረጋቸውንም ነው የሮይተርስ ዘገባ የሚያመለከተው፡፡

ዋይት ሃውስ በበኩሉ ለትርጉም የተጋለጠውን የጆ ባይደን ንግግር ከስርዓት ለውጥ ጋር የሚያገናኘው አንዳች ነገር የለም ሲል አስተባብሏል።

የፕሬዝዳንቱ አስተያየት በሩሲያ የስርዓት ለውጥ እንዲመጣ የተላለፈ ጥሪ ሳይሆን “በዴሞክራሲ የሚያምነው ዓለም ለተራዘመ ጦርነት ራሱን እንዲያዘጋጅ” ለመጠቆም የተላለፈ ነበር ብለዋል።

Via Jemal Abdulazia

Exit mobile version