Site icon ETHIO12.COM

የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚጥሰው HR6600/S3199 ሕግ ተቋረጠ

ኢትዮጵያዊያን በባንዳነት የሚጠሯቸውና በዋናነት ፍላጎታቸው ምን እንደሆነ ለመረዳት በሚያዳግት መልኩ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩትን ሁሉ በጉጉት ሲጠባበቁት የነበረው HR6600/S3199 ሕግ ሆኖ እንዲፀድቅ የቀረበው የውሳኔ ኃሳብ እንዲቋረጥ በአሜሪካን ኮንግረንንስና ሴኔት ውሳኔ ሳይጸድቅ ለጊዜው ወደ መዝገብ ቤት መመራቱ ታውቋል።

በኢትዮጵያ መንግስት በተወሰዱ አበረታች እርምጃዎች የተነሳ እና በተባባሪ ለጋሽ አካላት ቅንጅት የሰብዓዊ አቅርቦት እየተሻሻለ በመምጣቱ በኢትዮጵያ ላይ ተገቢ ያልሆነ ጫና ለማሳረፍ በአሜሪካ በ2ቱ ምክር ቤቶች የውጭ ጉዳይ ኮሚቴዎች ደረጃ ሲታዩ የነበሩ ረቂቅ ህጎች “ለጊዜው ባሉበት እንዲቆዩ” የሚለው ኃሳብ በውስጣቸው መንሸራሸሩ መልካም ቢሆንም ውሳኔ ያላገኘ በመሆኑ፣ የማዕቀብ እና የጫና ደመና ሙሉ ለሙሉ እስኪወገድ ድረስ በሰላማዊ መንገድ የተጀመረው ትግል ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል:: ኢትዮጵያን ለመታደግ ሰላማዊ ትግልና ድጋፍ ለምታደርጉ ሁሉ እጅግ እናመሰግናለን::

አምባሳደር ፍጹም አረጋ

የዩናይትድስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ያረቀቀው HR6600 እና S3199 ረቂቅ ሕጎች ሕግ ሆነው ከመውጣት እንዲዘገዩ የአሜሪካ ኮንግረስና ሴኔት ውሳኔ ላይ መደረሳቸውን ቀድሞ ያስታወቀው የኢትዮጵያ አሜሪካ ሲቪክ ካውንስል ነው። ካውንስሉ በቲውተር ገጹ እንዳለው ህጉ ከመጽደቅ ይልቅ ተቋርጧል።

ህጉ ጸድቆ ለተግባራዊነቱ ለፕሬዚዳንቱ እንደሚቀርብ አስቀድመው ሲተነትኑ የነበሩና ይህ ህግ እንዲረቀቅ ከፍተኛ የውስወሳ ስራን ከፍተኛ በጀት መድበው ሲያካሂዱ ለነበሩ ወገኖች ሃዘን፣ ኢትዮጵያን የሚጎዳና እንደ አገር ጥቅማችንን የሚነካ ህግ ነው ሲሉ የነበሩ ወገኖችን ያስደሰተው ይህ ውሳኔ ለጊዜው መዝገብ ቤት እንዲቀመጥ ተደርጓል።

“መንግስት የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ነኝ” የሚለውን ሃይል ምክንያት እያሳጣ መሆኑ ወደ ዲፕሎማሲያዊ ድል እንዳዛወረው ያመለከቱ ወገኖች ” ትህነግ አሁን አፋርን የሚወርበት ወይም ቀደም ሲል በካርታው ውስጥ የሌሉ፣ እንዲሁም ውዝግብ ያልነበረባቸውን የአማራ ክልል የሚቆይበት ምክንያት ስለሌለው በቀጣይ የዲፕሎማሲው ውሳኔ እየጠበቀበት ይሄዳል” ሲሉ ግምታቸውን አኑረዋል። ሌሎች ደግሞ “መንግስት አድርግ የተባለውን ስላደረገ ህጉን ማጽደቅ ለጊዜው አላስፈለገም” ሲሉ ይከራከራሉ። እንደውም አሜሪካ ተጨማሪ ነገር ካስፈለጋት ሕጉን ከመዝገብ ቤት በመጎተት እንደምትጠቀምበት ገልጸዋል።

ምንም ሆነ ምን ሕጉ እንዳይጸድቅ መደረጉ ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያን ለሚወዱ ድል መሆኑንን በርካቶች አስምረውበታል። ነገር ግን መንግስትም ሆነ ዜጎች በቀጣይ ትግላቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተመልክቷል። ትህነግም በከፍተኛ ደረጃ ለመደራደሪያ በጉጉት ከፍተኛ በጀት ከስክሶ ተግባራዊነቱን ሲጠባበቅ ስለነበር ውሳኔው የተገላቢጦሽ መሆኑ ትልቅ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ እንደሚከተው እየተገለጸ ነው። ደጋፊዎቹም ቢሆኑ ቅሬታቸውን እያሰሙ ነው።

ረቂቅ ህጉ እንዲቋረጥ ለጊዜው ከስምምነት የተደረሰበት ውሳኔ በቀጣይም ህግ ሆነው እንዳይፀድቁ ኢትዮጵያውያን እያደረጉት ያለው የዲፕሎማሲ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ዜናውን ያበሰረው የኢትዮጵያ አሜሪካ ሲቪክ ካውንስል ነው አሳስቧል።

የኢትዮጵያ አሜሪካ ሲቪክ ካውንስል በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን ጣልቃ ገብነትና ጫና በመቃወምና ዳያስፖራ ማህበረሰቡን ጭምር በማስተባበር ከፍተኛ የህዝብ ዲፕሎማሲ ስራ በመስራት ላይ ያለ መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገ ተቋም መሆኑ ይታወቃል።

Exit mobile version