Site icon ETHIO12.COM

የአሜሪካ አፍሪቃ ቀንድ መልዕክተኛ ወደ አዲስ አበባ አቅንተዋል፤ የሰላም ተስፋ እየታየ ነው

 አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማንን ተክተው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድና ምክትላቸው ፓይተን ኖፍ ለምክክር አዲስ አበባ ወደ እንዳቀኑ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። የሰላም ተስፋው እየጭመረ ነው።

ልዩ መልዕክተኛውና ምክትላቸው ከመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ከሰብአዊ ድርጅቶች ተወካዮች፣ እንዲሁም ከዲፕሎማቲክ አጋሮች ጋር ይነጋገራሉ እንደሚመክሩ ሚኒስቴሩ ይፋ አድርጓል።

የአምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድና የምክትላቸው ፓይተን ኖፍ የኢትዮጵያ ጉብኝት ግጭት ለማቆም፣ ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲኖር፣ ተፈጽመዋል የተባሉ የመብት ጥሰቶች ግልጽ ምርመራ እንዲደረግና፣በድርድር መፍትሄ ለመስጠት አሜሪካ የምታደርገው ጥረት አካል መሆኑ በመግለጫው ተመልክቷል።

በመጀመሪያ የአዲስ አበባ ቆይታቸው ማግስት መንግስት ግጭትና ትንኮሳ ማቆሙን፣ የሰብአዊ እርዳታ እንዲገባ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ ማስታወቁ ይታወሳል።

የመንግስትን አቋም ተከትሎ በግጭት ማቆሙ ስምምነት እንዳለው ያመለከተው የትግራይ ነጻ አውጪ ከአምባሳደሩ አዲስ አበባ መግባት በፊት ከአፋር አንድ ወረዳ መልቀቁን ማስታወቁ፣ ይህንንም ያደረገው ለሰላም ንግግርና እርዳታ ያለገደብ እንዲገባ ለማስቻል መሆኑንን አስታውቋል።

ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ወገኖች እንዳሉት ከሆነ ትህነግ ከአፋርና ከአማራ ክልል በወረራ ከያዛቸው አካባቢዎች ለመልቀቅ የቀረበለትን ማሳሰቢያ ተቀብሎ ነበር። ይሁን እንጂ እስካሁን ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ተግባራዊ አላደረገም።

የአምባሳደሩን ወደ አዲስ አበባ መምጣት አስቀድሞ የዓለም ባንክ 300 ሚሊዮን ዶላር በግጭቱ ለተጎዱ ክልሎች መፈቀዱ የሰላም አካሄዱ በስልትና በዕቅድ የተያዘ ስለመሆኑ አምለካች እንደሆነ አመላካች ነው ተብሏል።

Exit mobile version