Site icon ETHIO12.COM

“በትግራይ መሰረታዊ አገልግሎቶች መጀመር ሰላምን ያፋጥናል” አሜሪካ

– ትህነግ ሴራውንና ማተራመሱን እንዲያቆም ሕዝብ ጫና ማድረግ ይገባዋል

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን፤ የህወሓት ኃይሎች ከቀሪ የአፋር ክልል አካባዎች ለቀው እንዲወጡና በትግራይ የተቁረጠው መሰረታዊ አገልግሎት በአፋጣኝ እንዲጀመር ጠየቁ። ለሰማ ማስፈኑ ስራ አገልግሎቶች መጀመራቸው አግባብ እንደሆነ አመለከቱ። ከሁለቱም ወገን ይህን አስመልክቶ የተባለ ነገር የለም። ይሁን እንጂ ሰላምን የሚናፍቁ ትህነግ ሴራውንና ሌሎችን እያደራጀ የሚያካሂደውን ማተራመስ እንዲያቆም ሕዝቡ ጫና ሊያሳድር እንደሚገባው ተመልክቷል።

ብሊንከን በመግለጫቸው የትህነግ ኃይሎች በሃይል ከወረሩት ከአፋር ኤሬብቲ መውጣታቸውን አድነቀው። “ከሌሎችም የአፋር አካባቢዎችቢወጡ ጠቀሜታው የጎላ ነው” ሲሉ ምክረ ሃሳብ ቢጤ ሰንዝረዋል። ይሁን እንጂ በአፋር ንጹሃን ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍና ስቃይ በሚቃወም መልኩ ያሉት ነገር የለም። ከዚያ ይልቅ በትግራይ ክልል አፋጣኝ የመሠረታዊ አገልግሎቶችን መልሶ መጀመር ለዘለቂ ሰላም ወሳኝ እንደሆነ ነው ያመለከቱት።

እርዳታ የጫኑ 50 ተሸከርካሪዎች ወደ መቀሌ መግባታቸውን ተከትሎ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው እንዳሉት ተጨማሪ የነፍስ አድን ሰብአዊ ርዳታ ወደ ትግራይ ክልል መድረሱን አሜሪካ በበጎ የምትመለከተው እርምጃ ነው። ለዚህም የኢትዮጵያ መንግስት፣ የትህነግ አመራሮች፣ የአፋር ክልል ባለስልጣናት እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ግብረሰናይ ድርጅቶች ለተቸገሩ ሁሉ እርዳታ ለመስጠት የሚያደርጉትን ጥረት አገራቸው እንደምታደንቅ አስታውቀዋል።

አፋር ሰላማዊ ዜጎች ተወረው በጅምላ ግፍ እየተፈጸመባቸው መሆኑንን አንስተው በዝርዝርና በሚፈለገው መጠን የአገራቸውን አቋም ያላስታወቁት ብሊንከን፣ እንደ ትግራይ ክልል ሁሉ የአፋር ክልል ሕዝብና በስቃይ ላይ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታና በማይስተጓጎል መልኩ ሰብአዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ጠቁመዋል።



በቀጣይም የትህነግ ኃይሎች ከያዟቸው የአፋር ክልል አካባቢዎች ቢወጡ መልካም እንደሆነ ያመለከቱት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣ በድርድርና በዘላቂነት ግጭቶችን ለማስወገድ ሁሉም ወገኖች የጀመሩትን እርምጃ አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ገልጸዋል።

“… በትግራይ ክልል አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ እንዲሁም የኢትዮጵያውያን ብልጽግናና ደህንነት ለማረጋገጥ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሂደት አስፈላጊና መሰረታዊ ነው” ያሉት ብሊንከን ፖለቲካዊ መፍትሄ ሲሉ ያነሱት ሃሳብ አልተብራራም።

በሌላ በኩል አሜሪካ ከ1 ሺህ 700 ሜትሪክ ቶን በላይ ሕይወት አድን የሰብአዊ ድጋፍ የያዙ እርዳታ ጫኝ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ክልል መድረሳቸው በበጎ ጎኑ እንደምታየው አንቶኒ ብሊንከን ገልጸዋል።

“ወደ ትግራይ ክልል ያልተገደበ እርዳታ መድረስ መቀጠል አለበት፤አፋርን ጨምሮ በችግር ላይ የወደቁ ሁሉም ዜጎች ሰብአዊ ድጋፍን ተደራሽ ማድረግ ይገባል” ሲሉም ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የገለጹት።

በትግራይ ክልል የኤሌትሪክ ኃይል፣የባንክና የቴሌኮምዩኒኬሽን ጨምሮ ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች ዳግም መጀመር አስፈላጊ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ትህነግ በአፋር ክልል ከያዛቸው አካባቢዎች ለቆ እንዲወጣና በዚህ ረገድም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም በቡድኑ ላይ ጫናና ግፊት እንዲያደርግ በመግለጽ ላይ ይገኛል።

በሌላ በኩል ወደ ትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ ጭነው የተጓዙ 50 እርዳታ ጫኝ ተሽከርካሪዎች መቀሌ መግባታቸውን የዓለም የምግብ ፕሮግራም መግለጹ የሚታወስ ነው። ከጫኑት እርዳታ ውስጥ ስንዴ፣የቅባት እህልና ነዳጅ እንደሚገኝበት ጠቁሟል።

Exit mobile version