Site icon ETHIO12.COM

“በጅግጅጋ ከተማ ረብሻ እና ግጭት ተከስቷል በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ ነው”

በጅግጅጋ ከተማ ረብሻ እና ግጭት ተከስቷል በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ ነው:- ኮሚሽነር መሀመድ አሊ ሀሰን

በጅግጅጋ ከተማ ረብሻ እና ግጭት ተከስቷል በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መሀመድ አሊ ሀሰን ገለጹ።

ኮሚሽነሩ እንዳሉት በዛሬው እለት በጅግግጋ ከተማ ቀበሌ 04 አየር ደጋ በተሰኘው አከባቢ የጋራ የመንገድ ላይ ኢፍጣር ፕሮግራም እንደነበር ገልጸው ከፕሮግራሙ መጠናቀቅ በኋላ ህዝቡ ወደየመኖሪያ አከባቢው ሲመለስ ተቀላቅለው የገቡ አንዳንድ አካላት ረብሻ የማስነሳት ሙከራ ለማድረግ ቢሞክሩም በሰላም ወዳዱ ህዝብ እና በጸጥታ አካላት ሙከራቸው እንደተኮላሸና የተወሰኑትም በቁጥጥር ስር የዋሉ እንዳሉ ጠቁመው በቀሪዎቹ ላይ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ይህን ተከትሎ የረብሻ እና የግጭት ጠማቂዎች በተለያዩ የማህበራዊ ድረገጾች በጅግጅጋ ቤተ እምነት ላይ ጉዳት ደረሰ፣ ተቃጠለ የሚሉ ዘገባዎች እየተሰራጩ መሆኑን የጠቆሙት ኃላፊው ይህ ፍጹም ሀሰት እና ክል ሰላም እንዳይሆን የሚፈልጉ አካላት ሴራ ነው ያሉ ሲሆን ይህንን እውነትም ማንኛውም ሰው ወደ ጅግጅጋ በመደወል ጭምር ማረጋገጥ የሚችለው ሃቅ ነው ብለዋል፡፡

ኮሚሽነሩ የክልሉን ሰላም እና መረጋጋት ለማወክ እንዲሁም ሁከትና ግርግር በመፍጥር ለዝርፊያ እና ለውንብድና የሚንቀሳቀስ የትኛውንም አካል መንግስት እና የፀጥታ መዋቅሩ የሚታገሱት ጉዳይ አይደለም ያሉት ሃላፊው ህዝቡ ከሀሰተኛ መረጃዎች ራሱን እንዲጠብቅ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ ENA

Exit mobile version