Site icon ETHIO12.COM

የትም ተጣለ የተባለው ጀግና “ሚዲያዎቹ የጁንታው ናቸው” ሲል ምስክርነቱን ሰጠ

“የጥፋት አንደበቶች” በሚል የቀረበው አጭር ዘገባ ” ዛሬስ ምን ይሉ ይሆን?” የሚል ጥያቄ የሃሰት ዜና ሲያሰራጩ በነበሩት ላይ አስነስቷል። የጦርነት መሐንዲሱ ብርጋድየር ጄኔራል ሻምበል በየነ ገጹ ላይ ጉዳት ደርሶበት በወደቀ ቅጽበት ጀምሮ በሄሊኮፕተር ተጭኖ፣ እሱ ህክማናው ሰፈር እስኪደርስ ባለሙያዎች ተሰባስበው እንደተበቁትና በልዩ እንክብካቤ ህክምና እንድተደረገለት ምስክርነቱን ሰጥቷል።

ጀግናው ” የጁንታው ተከፋይ ሚዲያዎች” ሲል ነው ሚዲያዎቹን የፈረጃቸው። አቅራቢውም ” ማፈሪያ” ሲል ነው በኢትዮጵያ መከላከያ ላይ ልተሰነዘረው ስም ማጥፋት ግብረ ምላሽ የሰጣቸው። “አገር እንወዳለን በሚል አገር ማፍረስ” ተብሎ በማስረጃ ለቀረበው ሪፖርት 360 እስካሁን ያለው ነገር የለም። በይፋም ይቅርታ አልጠየቀም። ከዚህ ቀደም “የአባይ ግድብ ተሸጧል” በሚል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ላይ መረጃ እንዳላቸው ደጋግመው መናገራቸው ይታወሳል። አባይ ተገድቦ ኤሌክትሪክ ማመንጨቱ እውን ሲሆን 360ን ጨምሮ ተሸጠ ያሉ ማስተባበያ አልሰሩም። የባለከዘራውን ምስክርነት ያድምጡ ያጋሩ።

Exit mobile version