ETHIO12.COM

እንደ ዝናሽ ታያቸው አዜብ መስፍንም “ቀዳማዊት”

“አዜብ መስፍንም ቀዳማዊ እመቤት ነበሩ” ይላል ሳህሌ ወልደ ሃና። አዜብ ለሁለት አስርት ዓመታት በኖሩበት ሰፈር መኖር የጀመሩት ዝናሽ ታያቸውንም ሳህሌ እኩል እንደ አዜብ “ቀዳማዊት እመቤት” በሆናቸውን ሲያነሳ ” እውነትም ቀዳማዊት” በማለት ነው።

መለስ “ትንታግ ” ሲሉ እንደሚፈሩዋት ጠቅሰው የገለጿት አዜብ የአማኑኤል ሆስፒታል የቦርድ ሊቀመንበር ነበረች። ለአዕምሮ ህመምተኞች አገልግሎት ከሚሰጡ ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው ሳህሌ ” አዜብ ተቋሙን፣ ችግሩን፣ በጥቅሉ ታማሚዎቹ የሚያዙበትን አግባብ አያውቁም። ለማወቅም አይሞክሩም። በአማኑኤል ሆስፒታል ‘ታንከኛው’ ስለሚባል ቱሃን የሚባል ተባይ ሰምተው አይውቁም” ሲሉ መረጃ ያጣቅሳል።

ዛሬ ዝናሽ ታያቸው በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የሚኖሩ አቅመ ደካማ የስጋ ደዌ ተጠቂ ዜጎችን መኖሪየ ቤት እድሳት ማስጀመራቸውን የሚጠቅሰውን ዜና አካቶ በላከው አጭር ጽሁፍ ሳህሌ ” ከቤተመንግስት በመውጣት እንዲህ ያለ ቤት ውስጥ ገብቶ ቆሻሻ መናድ መባረክ እንደሆነ አመልክቷል።

አዲስ ከሚሰሩት ቤቶች መካከል አንዱ

ለአዜብ መስፍን ቅርበት ያላቸው ሚዲያዎች ወይም ሰዎች “ዛሬ ላይ ዝናሽን ታያቸውን ሲመለከቱ አዜብ ምን እንደሚሰማቸው ጠይቁና አሰሙን። ፖለቲካውን ድሮም ሳያውቁ ሲያቦኩት የኖሩት ስለሚበቃ እንደው ከራሳቸው ጋር ታርቀው እንደሆነ ለብዙዎች ትምህርት ይሆናሉና …”

ከለውጡ በሁዋላ ድሮ ኢህአዴግ እያሉ ትዝ የማይላቸውን ዛሬ ደሃ ቤት መግባት የጀመሩ፣ የደሃ ቤት መተገን የጀመሩ፣ ሰው ሰው መሽተት የጀመሩ፣ ሆስፒታል ሄደው የሚጎበኙ፣ በትምህርት ገበታቸው ላይ ጠኔ የሚጥላቸውን የሚያበሉ፣ የትምህርት መሳሪያና መለያ ልብስ የሚያለብሱ … መታየታቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ከትችት ውጪ ማመስገን ባህል ባለመሆኑ ተቀበረ እንጂ የሚዲያዎች ” መልካም ዜና” በሆነ ነበር። እንዳ ሳህሌ ገለጻ ” ዛሬ የጠቅላይ ሚኒስርት አብይ የትዳር አጋር የገቡበትን ቤት ስለሚያውቀው እዛ ሰፈር ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች በመታሰባቸው አጅግ መደሰቱን ጠቅሶ ” አመስግኑልኝ” ብሏል።

በርግጠኛነት ግንባታው ሲያልቅ ” ሰዎቹ እያነቡ ምስጋና ሲያቀርቡ እናያለን” ሲሉ ሃሳቡን ያጠቃለለው ሳህሌ ” ቤቶቹ መኖሪያ ሊባሉ የማይችሉ፣ በክረምት ምንም አይነት ውሃ የመከላከል አቅም የሌላቸው ሳይጣል ከኖረ ፍራሽ ክምር ተለይተው የማይታዩ ናቸው። እዚህ ውስጥ ገብቶ ስራ ማስጀመር የህሊና ምግብ ነው። አዜብ መስፍንን ባየንበት ዝናሽን አየን” ብሏል።

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የሚኖሩ አቅመ ደካማ የስጋ ደዌ ተጠቂ ዜጎችን መኖሪየ ቤት እድሳት ዛሬ ማስጀመራቸውን ጽህፈት ቤታቸው በፌስ ቡክ ገጹ አስታውቋል። ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ዛሬ ያስጀመሩት የስድስት አባወራ ቤቶቸን ሲሆን፤ እድሳቱ በቅርብ ቀናት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተመልክቷል።

ከወር በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በተመሳሳይ የፈራረሱ የአቅመ ደካማ መኖሪያዎችን የመገንባት ስራ ማስጀመራቸው፣ ለአዲስ አበባ ባለስልታኖችና ለሚኒስትሮች ተከፋፍለው ተመሳሳይ ተግባር እንዲያከናውኑ መመሪያ ምስተታቸውን ተከትሎ በውጭ አገር ባሉ የሚታወቁ የዩቲዩብ አውዶች መወገዛቸው ይታወሳል።

አብይ አህመድ ወደ ስልታን ከመጡ በሁዋላ የክረምት የበጎ ተግባር መርሃ ግብርን ማስጀመራቸውና ተማሪዎች በእረፍታቸው ለአገራቸውና ለማህበረሰባቸው ቅዱስ ተግባር ሲያከናውኑ ማየት አሁን አሁን እየተለመደ መምጣቱን በርካቶች የወደፊቱን ፍሬ በማሰብ አድንቆት እየቸሩት ይገኛሉ።

First Lady Zenash Tayachew visited & donated 15 wheelchairs to Mekodonia, home for elderly & disabled.

ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ በርካታ ተምህርት ቤቶችን ማስገንባታቸው፣ የአዕምሮ ህመምተኞችንና አካለ የጎደለባቸው ወገኖች እመጠለያቸው ድረስ በመሄድ የሚረዱ፣ የሚጎበኙ፣ በቤተመንግስት አረጋዊያንና አቅመ ደካሞችን ማዕድ በማጋራት ይታወቃሉ። ጽህፈት ቤታቸው ግንባታ ማስጀመር ብቻ ሳይሆን በተባለበት ወቅት በማተናቀቅ በማስረከብ ይታወቃል። ዝናሽ አሳዳጊ ላጡ ሕሳናት ጉስቋም አካባቢ ማረፊያ ማዕከል ማስገንባታቸና ሜቆዶኒያን በተደጋጋሚ የሚጎበኙ ትሁት ሰው ናቸው። በንግግራቸው ፖለቲካ የማያውቁና እንደ መሪ ሚስት ልታይ ልታይ የማይሉ ቁጥብ ሴት መሆናቸውን በቅርብ የሚያውቋቸው ይመስከራሉ።

በተቃራኒው አዜብ በከፍተኛ ሙስና፣ ስልጣንን ተገን በማድረግ፣ የፖለቲካ ስልጣናቸውን የሚወዱ፣ ያለ ችሎታቸውና አቅማቸው ትላላቅ የፓርቲ ተቋማትን ሲመሩ የኖሩ፣ በባለቤታቸው ትከሻ ላይ ሆነ በርካታ ያልተገባ ተግባር ሲፈጽሙ የኖሩና ቤተ መንግስትን ለቆ ለተረኛው ለማስረከብ ፈቃደኛ ባለመሆን የሚታወቁ፣ በሃያ አመት የስልጣን ዘመናቸው አንድ የሚያፈስ ቆርቆሮ ያላስጠገኑ፣ አንድ የራበው ሕጻን አቅፈው ያላጎረሱ፣ አረጋዊያንና አቅመ ደካሞችን ማእድ ስለማጋራት አስበው የማያዉቁና በተለያዩ በጎ አገልግሎቶች ሲሳተፉ ያልታዩ መሆናቸውን ሳህሌ አመልክቷል።

ዝግጅት ክፍሉ – ማረሚያ ወይም ሊስተካከል የሚገባ መረጃ ካለ ለማከል ዝግጁ ነን።


Exit mobile version