Site icon ETHIO12.COM

“በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የዘር ፍጅት ለማስነሳት የትህነግ ተላላኪዎች ሃሰተኛ መረጃ አሰራጭተዋል” የጋራ ግብረሃይል አስጠነቀቀ

በመሆኑም የዩኒቨርሲቲዎቹ ተማሪዎችና ማህበረሰብ የተከሰተውን ችግር ምክንያት በማድረግ ሆን ብለው ግጭት ለማነሳሳት እየተንቀሳቀሱ ያሉ የአሸባሪው ህዋሓት ጁንታ ቡድን ተላላኪዎችና ቅጥረኞች መኖራቸውን ተገንዝባችሁ ከነዚህ አሸባሪዎች ራሳችሁን በመጠበቅ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደርጉ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ያሳስባል። ሆኖም ይሄንን ማሳሰቢያ ተላልፈው ከድርጊታቸው የማይቆጠቡ አካላትን የማይታገስና ጥብቅ ህጋዊ እርምጃም ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን ያስታውቃል።

‘’ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል እንዲሉ’’ እነዚህ ሚዲያዎች ሰሞኑን እንደለመዱት ግጭት ለመቀስቀስ በዩኒቨርሲቲዎች ላይ ያነጣጠረ ግጭት ለማስነሳት «በአማራ ክልል ዩኒቨርስቲዎች የሚማሩ የኦሮሞ እና የሌሎች ብሄር ተማሪዎችን ለማጥቃት የተደራጀ የደህንነት ቡድን ወደ አማራ ክልል ተልኳል» የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።

በቅርቡ የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ)፣ የጉሙዝ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅንቄ (ጉህዴን) እና የኦነግ-ሸኔ አሸባሪዎች ተደራጅተውና ተቀናጅተው በጋምቤላ ክልል በጋምቤላ ከተማና አካባቢው እንዲሁም በጊምቢና ደምቢ ዶሎ ከተማ ጥቃት ለመፈፀም ሙከራ አድርገው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር በመቀናጀት በወሰዱት እርምጃ የሽብር ቡድኖቹ በከፍተኛ ደረጃ እየተደመሰሱና ተፈጥሮ የነበረውም ችግር ተወግዶ አካባቢው ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲመለስ ተደርጓል።

ይሁን እንጂ የሽብር ቡድኖቹ በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊንቢ ከተማ አካባቢ የሚገኝ ቶሌ ቀበሌ ላይ ሰላማዊ በሆኑና ምንም በማያውቁ ንፁሃን ህፃናትና ሲቪሊያን ላይ ጉዳት ማድረሳቸውና በርካቶችንም መግደላቸው ይታወሳል።

ወያኔ ሀገር የማፍረስ እኩይ ዓላማውን በጦርነት ማሳካት ስላልቻለ በየቦታው ባደራጃቸውና ባስታጠቃቸው ተላላኪ ቡድኖች አማካኝነት የጅምላ ግዲያ በተልዕኮ እየፈፀመና እያስፈፀመ ይገኛል።የዚህ ድርጊት ዋና ዓላማም ህዝብ በመንግስት ላይ ተስፋ ቆርጦ እንዲነሳና ሰላም እንዲደፈርስ ለማድረግ ነው።

የሽብር ኃይሎችን በሁሉም አካባቢ የመቆጣጠር እና ህግ ማስከበር ስራ እየተሰራ ባለበት በዚህ ወቅት አንድ መሆንና አሸባሪዎችን በጋራ መፋለም ሲገባን በተለያየ ውዥንብርና ከፋፋይ ሂደት ውስጥ መግባት በፍፁም አይኖርብንም።

በተለይ በአሸባሪው ህዋሓት ጁንታ ቡድን ፋይናንስ የተደረጉ ሚዲያዎችን በመጠቀምና እኩይ ዓላማቸውን ለማስፈፀም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ለማደናቀፍ ተማሪዎችን በብሄርና በሀይማኖት በመከፋፈል ግጭት እንዲፈጠር ለማነሳሳት ሌት ተቀን አሸባሪዎች እየሰሩ መሆናቸውን የጋራ ግብረ ኃይሉ ደርሶበታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የጠላትን ሴራና አካሄድ ጠንቅቀን ካልተረዳንና እነርሱ በከፈቱልን ቦይና ወጥመድ ውስጥ የምንገባ ከሆነ ለውስጥና ለውጭ ጠላቶቻችንን እኩይ ሴራ በራችንን እንደከፈትን ይቆጠራል።

እነዚህ በዶላር የተገዙ ሚዲያዎች ከዚህ ቀደም በጎንደር ችግር ከመፈፀሙ አስቀድመው ህዝቡን በሀይማኖት ለመከፋፈል አጀንዳ ቀርፀው ሰላም ለማደፍረስና ግጭት ለማቀጣጠል ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡
የተፈጠረውን ግጭት በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች እንዲዳረስና የእምነቱን ተከታዮች ወደ ለየለት ሁከትና ብጥብጥ ለማስገባት ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበረም።

ሆኖም የጥፋት ተልዕኳቸው በህዝባችን የመቻቻል ባህል፣ አርቆ አስተዋይነት፣ ትዕግስት እና በፀጥታ ኃይሎቻችን ከፍተኛ ርብርብ መክሸፉ ይታወቃል።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ ከራሱ በፊት ለህዝብና ለሀገር ህይወቱን እየሰዋ የህዝብን ሰላምና ደህንነት የሚጠብቅ ኃይል መሆኑ የሚታወቅ ሆኖ ሳለ የተፈጠረውን ክስተት ምክንያት በማድረግ በሽብርተኞች ላይ የተጀመረው ዘመቻ ተጠናክሮ እንዳይቀጥል የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ይገኛሉ።

‘’ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል እንዲሉ’’ እነዚህ ሚዲያዎች ሰሞኑን እንደለመዱት ግጭት ለመቀስቀስ በዩኒቨርሲቲዎች ላይ ያነጣጠረ ግጭት ለማስነሳት «በአማራ ክልል ዩኒቨርስቲዎች የሚማሩ የኦሮሞ እና የሌሎች ብሄር ተማሪዎችን ለማጥቃት የተደራጀ የደህንነት ቡድን ወደ አማራ ክልል ተልኳል» የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመሆኑም የዩኒቨርሲቲዎቹ ተማሪዎችና ማህበረሰብ የተከሰተውን ችግር ምክንያት በማድረግ ሆን ብለው ግጭት ለማነሳሳት እየተንቀሳቀሱ ያሉ የአሸባሪው ህዋሓት ጁንታ ቡድን ተላላኪዎችና ቅጥረኞች መኖራቸውን ተገንዝባችሁ ከነዚህ አሸባሪዎች ራሳችሁን በመጠበቅ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደርጉ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ያሳስባል። ሆኖም ይሄንን ማሳሰቢያ ተላልፈው ከድርጊታቸው የማይቆጠቡ አካላትን የማይታገስና ጥብቅ ህጋዊ እርምጃም ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን ያስታውቃል።

ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም. አዲስ አበባ

Exit mobile version