ETHIO12.COM

ሸኔ እየተበታተነ ንጽሃንን በድጋሚ መጨፍጨፉን መንግስት ይፋ አደረገ

“ጥቃቱ የተፈፀመው በቄለም ወለጋ ዞን፣ ሐዋ ገላን ወረዳ ውስጥ በሚገኝ መንደር ሃያ ተብሎ የሚጠራ አካባቢ መሆኑንና ቢያንስ ሰባ ሰው ሳይገደል እንዳልቀረ ከተገደሉት መካከል ቤተሰቦቼ ይገኙባቸዋል” ሲሉ የምዕራብ ወለጋ ነዋሪ ለቪኦኤ ምስክርነታቸውን አኑረዋል። ይህን ጭፍጨፋ የፈጸመው ራሱን “የኦሮሞ ነጻነት ጦር” የሚለው፣ ከትህነግ ግራ በጣምራ የሚሰራውና በአሸባሪነት የተፈረጀው ሸኔ እንደሆነም ምስክሩ ገልጸዋል። ይህ ሪፖርት እስከቀረበ ድረስ ሸኔ የሰጠው ማስተባበያም ሆነ ማረጋገጫ የለም።

የጸጥታ አካላት ከሚያደርሱበት ዱላ የፈረጠጠው የሸኔ ቡድን በምዕራብ ወለጋ በዜጎች ላይ አደጋ እያደረሰ በመሸሽ ላይ ነው። በኦሮሚያ ክልል፣ ቄለም ወለጋ ዞን ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ጭፍጨፋ ተፈጽሞባቸዋል። በዜጎቻችን ላይ በደረሰው መከራ እያዘንን ይሄንን አሸባሪ ቡድን እስከመጨረሻው ተከታትለን ከህዝባችን ጋር እናስወግደዋለን። ጠ/ሚ አብይ አሕመድ በማህበራዊ ገጽ

በቅርቡ በምዕራብ ወለጋ በማንነታቸው ተለይተው በጅምላ መጨፍጭፋቸው ከተሰማ በሁዋላ፣ መከላከያ በስፋትና በጥልቀት እርምጃ መውሰድ መጀመሩ በተለያዩ አግባቦችና ሃላፊዎች ሲገለጽ ቆይቷል። ሕዝብ በየዕለቱ፣ ፓርላማውም ዘግየት ብሎ መንግስት የጀመረውን የማጽዳት እርምጃ እንዲቀጥልበት፣ በመንግስት መዋቅር ውስጥ ሆነው ከጭፍጨፋው ጋር ተባባሪ የሆኑትን አጣርቶ ለህግ የማቅረቡን ተግባርም እንዲገፋበት መጠየቃቸው ይታወሳል።

ባለፈው ሳምንት የህጻናት መማሪያ ትምህርት ቤትን የወታደር ካምፕ ባደረገው የሸኔ ሃይል ላይ ጥቃት ሰንዝሮ አርባ አምስት መግደሉንና ሁለት መማረኩን መንግስት በገሃድ ካስታውቀ በሁዋላ እየወጡ ያሉ መረጃዎች ሸኔ በውስጥም በውጭም አደጋ ላይ መውደቁን አመልካቾች እንደሆኑ እየተነገረ ነው።

አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ የአማራ ተወላጆችን መጨፍጨፉን ከጥቃቱ የተረፉ ተጎጂዎች ተናገሩ።
አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በኦሮሚያ ክልል በቄለም ወለጋ የአማራ ተወላጆች ላይ በፈጸመው ጭፍጨፋ ህፃናት እና ሴቶችን ጨምሮ የበርካታ ንጹኀን ህይወት ማለፉን ከጥቃቱ የተረፋ ተጎጅዎች ተናግረዋል።
ተጎጂዎቹ ለአሚኮ እንደተናገሩት በአማራ ተወላጆች ላይ ጥቃቱ የተፈጸመው በኦሮምያ ክልል በቄለም ወለጋ በሮቢት ገበያ ወረዳ መንደር 20 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው። አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በዚህ አካባቢ በከባድ መሳሪያ በመታገዝ በርካታ አማራዎችን መጨፍጨፋን ነው ቤተሰቦቻቸውን ያጡ ተጎጂዎች የተናገሩት።
ከጥቃቱ የተረፈው ሕዝብም ወደ ከተማ በመግባት የመጠለያና የዕለት ምግብ ችግር እንዳጋጠመውና ችግሩን መንግሥት መፍትሔ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።
አሁን ላይ በአካባቢው የሀገር መከላከያ ሠራዊት መድረሱን ገልጸዋል። ጥቃት አድራሾችም ለጊዜው መሸሻቸውን የተናገሩት ተጎጅዎቹ በንጹኀን ላይ እየተፈጸመ ያለውን ጭፍጨፋ መንግሥት እንዲያስቆም ጠይቀዎል። ሲል ኢሚኮ ምስክሮችን ጠቅሶ ዘግቧል

“የሸኔ ታጣቂ ቡድነ ላይ እየተወሰደ በሚገኘው እርምጃ ቡድኑ ላይ የተፈጠሩ ተጽዕኖዎች ሰፊ ናቸው” ሲሉ የሚናገሩ እንዳስረዱት ሸኔ ሃይሉ እየተበተነ ነው። የዕዝ ሰንሰለቱ እየፈረሰ ሲሆን፣ ተራ ዝርፊያና ንጽሃንን ኢላማ በማድረግ እየጨፈጨፈ መሆኑን ያስረዳሉ። ይህን መረጃ ካገኘን በሁዋላ መንግስት ጭፍጨፋ መፈጸሙን አረጋግጧል።

“የጸጥታ አካላት ከሚያደርሱበት ዱላ የፈረጠጠው የሸኔ ቡድን በምዕራብ ወለጋ በዜጎች ላይ አደጋ እያደረሰ በመሸሽ ላይ ነው። በኦሮሚያ ክልል፣ ቄለም ወለጋ ዞን ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ጭፍጨፋ ተፈጽሞባቸዋል። በዜጎቻችን ላይ በደረሰው መከራ እያዘንን ይሄንን አሸባሪ ቡድን እስከመጨረሻው ተከታትለን ከህዝባችን ጋር እናስወግደዋለን” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በማህበራዊ ገጻቸው አስታውቀዋል። የጭፍጨፋውን መጠን ግን አላስታወቁም።

“የኦሮምኖ ነጻ አውጪ ሰራዊት ነኝ” ሲል ራሱን የሚጠራው ይህ ታጣቂ ቡድን በቢቢሲ በኩል ከወለጋው ጭፍጨፋ ነጻ ያደረገው ሸኔ፣ በወቅቱ “ጭፍጨፋው በነጻ አካል እንዲጣራ እጠይቃለሁ” ከማለቱ ውጭ የአገር መከላከያ ሰራዊት ወሰድኩ በሚል ስላሰራጨው ዜና ምንም አላለም። ይዟቸው የነበረውን አካባቢዎች አስረክቧል መባሉንም በተመሳሳይ አላስተባበለም።

ጉዳዩን የሚከታተሉና ውስጥ ያሚያውቁ ተማኝ ምንጮች ሸኔ ኃይሉ እየተበታተነ ወደ ጫካና ዋሻዎች እየሸሸ መሆኑን አስታውቀዋል። ይህም የሆነው ሃይሉ በበርካታ እቅጣጫዎች በስፋት የተከፈተበትን ጥቃት መቋቋም ስለተሳነው ነው። ይህ ሃይል በፀጥታ አካላት የሚወሰዱ ጥቃት መክቶ መዋጋት ባለመቻሉ ለመሸሽ መገደዱና፣ ሲሸሽ ንጽሃንን እየጨፈጨፈ መሄዱ ተመልክቷል።

ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ብሎ ራሱን ለግምሽ ምዕተ ዓመት የሚጠራው ትህነግ ጃልመሮ ከሚመሩት ታጣቂ የሸኔ ቡድን ጋር በተመሳሳይ አጀንዳ አብረው ለመስራት መስማማታቸውን ይፋ ካደረጉ በሁዋላ ቡድኑ ሰፊ ቁጥር ያላቸውን ንጹሃንን ዘር ለይቶ ሲያጠቃ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። በሁለት ሳምንት ውስጥ የደረሰውን ጭፍጨፋ ትህነግም ሆነ ሌሎች ኦሮሚያ ላይ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች በይፋ አልተቃወሙም። ይሁን እንጂ ሸኔ ” የለህበትም” ሲል አስተባብሎ “ገለልተኛ” ሃይል እንዲያጣራ መጠየቁ ይታወሳል። ትህነግም አማራና አፋር ክልልን በወረርበት ወቅት ላደረሰው ጥፋት ሲጠየቅ ” በገለልተኛ ካል ይጣራ” ሲል በተመሳሳይ ሲያስተባብል እንደነበር ይታወሳል።

ከአካባቢው ወታደራዊ መረጃ ያላቸው እንዳሉት የደረሰበትን ጥቃት ተከትሎ የሸኔ የታችኛው ታጣቂ ሃይል አመራሮች ትዕዛዝ መቀበል ያቆሙበት፣ በተለያዩ አከባባዎች በተለያየ ደረጃ የሚገኝ የቡድኑ ታጣቂ ደግሞ ከቡድኑ መሪዎቻቸው የሚሰጡ መዋቅራዊ ትዕዛዞችን ወደሁዋላ የማለት ባህሪ እያሳዩ እንደሆነም አስታውቀዋል።
ታጣቂዎቹ አንድን አከባቢ ተቆጣጥረው ረጅም ጊዜ ይዞታቸውን አስተብቀው መቆየት እንደማይችሉ የተገነዘቡ በመሆኑ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ስፍራው ላይ ሳይደርሱ አስቀድመው ዝርፊያ በመፈጸም በፍጥነት አካባቢዎቹን ለቀው እነደሚወጡ ምንጮቹ ማስረጃ ጠቅሰው አመልክተዋል። አያይዘውም ንጹሃንን እየጨፈጨፈ መሆኑን ተናግረዋል።
“ቡድኑ በቀጥታ ከፀጥታ አካላት ጋር ፊት ለፊት ውጊያ ለማካሄድ የሚያስችል ቁመና የሌላው በመሆኑ የፀጥታ አካላት ባልደረሱበት ወይም በሳሱበት ቀጠና ሾልኮ በመግባት ሲቪሎችን ኢላማ ያደረግ ግደያ በመፈጸም የሚዲያ ትኩረት ለማግኘት ጥረት ሲያደርጉ ይስተዋላል” ሲሉ ወቅታዊ መረጃዎችን ያሰባሰቡት ወገኖች፣ ይህንኑ ተከትሎ “ሸኔ ተተኪ ታጣቂ ለማፍራት በተወሰነ ደረጃ ተቸግሯል” ብለዋል። አያይዘውም ” ባለፉት ጥቂት ቀናት በተካሄዱ ኦፕሬሽኖች ከ400 በላይ ታጣቂዎች ተገድለውበታል” ሲሉ ቡድኑ አዳዲስ ታጣቂዎችን ለመመልመል የተገደደበትን ምክንያት አመላክተዋል።

Exit mobile version