Site icon ETHIO12.COM

ኢትዮጵያና ሶማሊላንድ የበርበራ ወደብን አልምቶ የመጠቀም ስምምነታቸውን አጸኑ

ኢትዮጵያ ቀደም ሲል የነበረውን በበርበራ ወደብ አልምቶ የመጠቀም መብቷ እንደማይነካባት በሶማሊላንድ ፕሬዚደንት በኩል ይፋ ሆኗል ሲል የምሥራብ የሬድዮ መጽሔት ማስታወቁ ተመለከተ።

ይህ የተሰማው የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን ወደ ሶማሊላንድ ከተማ ሐርጌሳ ማቅናቱን ተከትሎ ነው። የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ እንዲሁም በአምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የተመራ የልዑካን ቡድን ከሶማሊላንድ ፕሬዚደንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ጋር መነጋገሩን የሶማሊላንድ ብሔራዊ ጣቢያ አመልክቷል።

ኢትዮጵያ የበርበራን ወደብ ለማልማት ከሶማሊላንድና ከዲፒ ወርልድ ኩባንያ ጋር የጋራ ስምምነት ፈጽማ እንደነበር ይታወሳል። በዚህ ስምምነት አስራዘጠኝ በመቶ የወደቡና ድርሻ እንዳላት ይታወቃል። ባለፈው ወር ከክፍያ ጋር በተያያዘ ድርሻዋ መነጠቁን የሶማሊላንድ የገንዘብ ሚኒስቴር መናገራቸውም ተናገረው ነበር።

እኚሁ ሚኒስትር በተገኙበት ፕሬዚደንታዊ የእራት ግብዣ የተደረገለት የኢትዮጵያ ልዑክ ስምምነቱ ባለበት ደረጃ አንደሚቀጥል ማስተማመኛ እንዳገኘ ቲክቨሃ አመልክቷል። ኢትዮጵያ የአስራ ዘጠኝ በመቶ ድርሻ ባለቤት የሆነችበት የበርበራ ወደብ በሙሉ አቅሙ ስራ ሲጀምር ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው። ለጅቡቲ በየወሩ የምትከፍለው ወጪም ይቀንሳል።

Exit mobile version