Site icon ETHIO12.COM

«አስቸኳይ መልእክት በትግራይ ለምትኖሩ ወገኖቻችን» መንግሥት

በትግራይ የምትኖሩ ወገኖቻችን በተለይም የጁንታው ወታደራዊ መሣሪያዎች እና ማሠልጠኛዎች ካሉባቸው አካባቢዎች ራሳችሁን እንድታርቁ ይመከራል።

መንግሥት እስከ አሁን ድረስ ለሰላም በሩን ክፍት አድርጎ ቢጠባበቅም ጁንታው ጥቃቱን ቀጥሎበታል።

በመሆኑም የፌዴራል መንግሥት ያለ ቅድመ ሁኔታ ለመነጋገር የገለጸው ዝግጁነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለጁንታው ፀረ ሰላም ዕብሪት ምንጭ የሆኑ ወታደራዊ ዐቅሞችን ዒላማ ያደረገ ርምጃ ይወስዳል።

የመንግሥት ኮምንኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ

ያለ ጦርነት መኖር የማይችለው አሸባሪው ሕወሐት ለሰላም የተከፈቱትን በሮች ሁሉ እየዘጋቸው ነው፤ የመከላከያ ኃይላችን ይዞ በቆየባቸው ቦታዎች ላይ አሁንም ጥቃት እፈጸመ ይገኛል።

የመከላከያ ኃይላችን የመንግሥትን የሰላም አማራጭ በመያዝ በጥንቃቄ በመከላከል ላይ ነው።

እስካሁን የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰላም ያደረጋቸው ጥረቶችና የከፈላቸው ዋጋዎች ይታወቃሉ፤ መንግሥት በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል የተፈጠረውን ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል ።

በዚህ ውሳኔው ሠረት የተናጠል የተኩስ አቁም አድርጓል። ለርዳታ የሚገቡ መኪኖችና ለርዳታ የሚገቡ ቁሳቁሶች ላልተገባ ተግባር መዋላቸውን እያወቀ እንኳን፣ ለሕዝቡ ሲባል፣ ወደ ትግራይ ክልል ሰብአዊ ርዳታ ያለ ችግር እንዲገባ ሁሉንም ነገር አመቻችቷል ።

የድርድር ዕቅዱንና ተደራዳሪዎቹን ይፋ አድርጓል። በማናቸውም ጊዜ፣ በማንኛውም ቦታ፣ በማናቸውም ጉዳዮች ለመነጋገር ዝግጁ መሆኑንም አሳውቋል።

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አሁን በግልጽ እንደታየው ሕወሐት ነዳጅ ዘራፊ ብቻ ሰይሆን ጠብ ጫሪ መሆኑን ዐውቆ ማውገዝ አለበት።

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ፣ “ሁለቱ ወገኖች’ ከሚል ፍርደ ገምድል ጥሪ ተላቆ መንግሥት ወደ ያዘው የሰላም አማራጭ ሕወሐት እንዲመጣ ግፊት እንዲያደርግ አሁንም መንግሥት ጥሪ ያደርጋል።

ይህ ካልሆነና ሕወሐት ጥቃቱን የሚቀጥል ከሆነ፣ መንግሥት በሕግ የተጣለበትን ግዴታ ለመወጣት ሲል ማንኛውንም ርምጃ ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን ያሳውቃል።

ነሃሴ 20 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ

Exit mobile version