ETHIO12.COM

አሸባሪው ህወሃት ህጻናትን በጦርነት በማሰለፍ የሚያከናውነውን ጭካኔ የተሞላበት ተግባር የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እያወገዘው አይደለም

አሸባሪው ህወሃት ህጻናትን አስገድዶ በጦርነት በማሰለፍ የሚያከናውነውን ጭካኔ የተሞላበት ተግባር የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በተገቢው መልኩ እያወገዘው አለመሆኑን አንድሪው ኮሪብኮ ተናገሩ፡፡

አንድሪው ኮሪብኮ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ አሸባሪው ህወሃት ህጻናትን አስገድዶ በጦርነት በማሰለፍ ለሰው ማእበል የጦርነት ስልት እየተጠቀመባቸው ቢሆንም የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለጉዳዩ የሚጠበቅበትን ምላሽ እየሰጠ አለመሆኑን ተናግረዋል።

ዲሲፕሊን ያለው ወታደር ህጻናትን ተኩሶ እንደማይገድል የገለጹት የፖለቲካ ተንታኙ፤ የሽብር ቡድኑ ማፊያዎች ይህን ከግንዛቤ በማስገባት ህጻናትን በጦርነት በማሰለፍ ለሽብር ተግባራቸው እውን መሆን እየሰሩ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል፡፡

በተጨማሪም የሽብር ቡድኑ ህጻናትን በጦርነት የሚያሰልፈው በወታደሩ ዘንድ “ራስን በመከላከልና ህጻናትን ተኩሶ አለመግደል” በሚለው የሞራል እሳቤ ላይ ውዥንብር እንዲፈጠር በማድረግ አለማውን ለማሳካት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የሽብር ቡድኑ ጦርነት ቁሞ ችግሮች በሰላም እንዲፈታ ከማድረግ ይልቅ አሁንም በሽብር ተግባሩ መቀጠሉ ደግሞ እጅግ አሳዛኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሃብቷን በመጠቀም ለመልማት የምታደርገውን ጥረትና በዓለም አቀፉ መድረክ ያላትን ሚዛኑን የጠበቀ አካሄድን የማይፈልጉ የውጭ አካላት በኢትዮጵያ የተጀመረው ጦርነት እንዲባባስ እየሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

የፌደራል መንግስቱ ችግሩ በሰላም እንዲፈታ ረዥም ርቀቶችን ቢጓዝም በተቃራኒው የሽብር ቡድኑ ምላሽ ግን ጥቃትን በመፈጸም ችግሮች እንዲባባሱ ማድረግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሽብር ቡድኑ ከዚህ አካሄድ የተቀየረ ማንነት ሊኖረው እንደማይችልም ነው ያብራሩት፡፡

የፌዴራል መንግስቱ ሰለማዊ ዜጎች እንዳይጎዱ ከፍተኛ ጥንቃቄ እያደረገ ቢሆንም አሸባሪው ህወሃት ግን ህዝብን እንደ ምሽግ በመጠቀምና የህዝባዊ ማእበል የጦርነት ስልትን እየተከተለ ስለመሆኑ አንስተዋል፡፡

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይህን የሽብር ቡድኑን አካሄድ በግልጽ እያወገዘው አለመሆኑ ደግሞ እጅግ አሳዛኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ መድረክ የአፍሪካ ድምጽ እንዲሰማ እንዲሁም በዓለም ጂኦ ፖለቲካ ባለው የምስራቅና ምእራብ መሳሳብ ውስጥ ሚዛኗንና ነጻነቷን ጠብቃ በመንቀሳቀሷ በአንዳንድ ምእራባዊያን አገራት ጥርስ እንደተነከሰባትም ነው ያብራሩት፡፡

ኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ ነጻነቷን ጠብቃ በአፍሪካ ተጽእኖ እየፈጠረች መምጣቷን ጠቅሰው፤ እንዳንድ የምእራባዊያን አገራት ይህን አካሄድ እንዳልወደዱት ያነሳሉ፡፡

የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖምን ጨምሮ መሰል የቡድኑ ደጋፊዎች የዓለም አቀፍ ተቋማትን ሚና በመጥለፍ የግል ፍላጎታቸውን እያራመዱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዚህም የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በተቋሙ ያለውን ስልጣን በመጠቀም የአሸባሪው ህወሃት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ቁንጮ መሪ ሆኖ እያገለገለ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡

OBN

Exit mobile version