ETHIO12.COM

የግንባር የሳምንቱ መረጃዎችና የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ

በወልደያ ግንባር በስጋት አካባቢያቸውን ለቀው የተንቀሳቀሱ ወደ ቀድሞ ቤታቸውና ሰፈራቸው አየተመለሱ ነው። ተቋርጦ የነበረው የወልዲያ ከተማ መብራት ተጠግኖ ተመልሷል።ዳግም በወርቄ በኩል ሃይል ኣሰባስቦ የመጣው የትህነግ ሃይል ወርቄወች፣ ከመከላከያ ጋር በመሆን በጥምረት ድል አንደመቱ ምስክሮች ተናግረዋል። ከትህነግ ወገን የተባለ ነገር የለም።

በግዳን አቅጥጫ የትህነግ ኃይል ቁጥጥር ስር ሥር ህነው የቆዩ ኣካባቢዎች በሙሉ በሚባል ደረጃ በጥምር ጦሩ እጅ ቁጥጥር ስር መሆናቸውን ምስክሮች ኣመልክተዋል።

▪️በሱዳን በኩል ከውጭ ሀይሎች ጋር በጥምረት የተከፈተብንን የወራሪው ኃይል ጥቃት ለመመከት የዳንሻ ሰው ነቅሎ ዘምቷል። እኔ ልቅደም እኔ ልቅደም እያለ ነው።

▪️ወራሪው ኃይል ሲዘጋጅበት የነበረውን ወረራ በሁሉም ግምባር ቢከፍትም ክንደ ብርቱ ኃይሎቻችን ጥቃቱን በመመከት በመልሶ ማጥቃት አሳሩን እያሳዩት ነው።

ሁመራ ግንባር

የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጥምር ጦሩ ሁሉንም ምሽጎች ሰባብሮ አካባቢውን ተቆጣጥሯል። ሸረሪማ ግዴማ ዙሪያ አዛዛ ነጭ ድንጋይ ሽብርተኛ ቡድኑ ይንቀሳቀስባቸው የነበሩ አካባቢዎች ናቸው:: አሁን በጥምር ጦሩ ቁጥጥር ስር ገብተዋል።

ሰቆጣ

ጀግናዉ መከላከያ ሰራዊታችን በፀመራ ግንባር በጁንታዉና ዉታፍ ነቃዮቹ ላይ እያሳረፈ ያለዉን ጡጫ በአካል ተገኝቼ አየሁ… ጠላት እግሬ አዉጭኝ እያለ ላለፉት ወርሃት ምናልባትም ለአንድ አመትና ከዚያ በላይ ይዟቸዉ የቆየዉን ገዥ መሬቶችና ምሽጎች ጥሎ ሲፍረጥጥ እድለኛ ሆኜ አየሁ። አበርገሌ ትናፍቀናለችኮ አይደል

ዋግ ኽምራ

በዋግ ኽምራ ዞን በዝቋላ ወረዳ ስር የነበረና ጁንታው ይተማመንበት የነበረው የቅዳሚት ማዕከል ምሽግ በጥምር ሃይሉ ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል:: በዚህም ምክንያት ጁንታው ወደ አብርገሌ ከተማ እየሸሸ ነው አብርገሌ ማለት ለሰቆጣ 65 ኪሎ ሜትር ይርቃል ለመቀሌ ደግሞ 45 ኪሎ ሜትር ይርቃል።

በአበርገሌ ግምባር የትህነግ ሃይል ከፍተኛ ማጥቃት ሰንዘሮ ነበር። ጥቃቱ ተደጋጋሚና ሰፊ ሃይል የተሳተፈበት ቢሆንም የጥምር ጦሩ ከመከላከል ወደ ማጥቃት ተሸጋገሮ በርካታ ቦታዎችንን በስፋት የተዘረጉ ምጽጎጽን መንጠቁ ታውቋል።በአበርገሌ በኩል የገፋው ሃይል ቀጣይ ከተማው መሆኒ መሆኗና መሆኒ ለመቀለ ቅርብና የመጨረሻዋ መዳረሻ ከተማ በመሆኗ “ምን ታስቧል” የሚል ጥያቄ ከየኣቅጣጫው አየተነሳ ነው።

በቆቦ አላማጣና ማይጨው መካከል ያለው የትህነግ ሃይል በትክክል በምን ሁኔታ አንደሚገኝ ባይታወቅም ከአፋር አባላ አቅጣጫ ያለው ሃይል ከተንቀሳቀሰ በምን መልኩ ራሱን ማዳን አንደሚችል ወደፊት የሚታይ ከመሆኑ ውጭ አሁን ላይይህ ነው ለማለት አንደማይቻል ለዘመቻው ቅርብ የሆኑ አየተናገሩ ነው።

ሰቆጣ‼️

የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚመራው ጥምር ጦር በሰቆጣ ትህነግ የገነባውን ኣምስት ምሽግ ሰብሮ ወደፊት እየሄደ አንደሆነ በስፍራው ዘመቻ ላይ ያሉ ወገኖች ተናገረዋል። ከሰቆጣ መያዝ ጋር በኣልበርጌ አየገፋ የሄደው ሰራዊት በምን ደረጃ ላይ አንደሚገኝ መንግስት የተነፈሰው ነገር የለም።

ወልቃይት ሁመራ

በወልቃይት ኣቅጣጫ ትህነግ ጦርነት መጀመሩ ሲሰማ ወይም መንግስት በኣምስት ኣቅጣጫ ትህነግ ጦርነት ከፍቶብናል ካለ በሁዋላ ወዲያውኑ የአካባቢው ሕዝብ “እኔ ልቅደም” በሚል ስሜት ወደ ግንባር ሲተም የሚያሳይ ምስል ይፋ ሆኗል። ደጀኑም አየፎከረ ስንቅ ሲያዘጋጅና ታይቷል። ፋኖውና ሚሊጻው ልዩ ሃይልና መከላከያን ለማገዝ ሲተም አቶ ጌታቸው ” ከኣማራ ጋር ጦርነት ኣልከፈትንም” ሲሉ መግለጫ ሰጥተዋል።

ኣቶ ጌታቸው ወልቃይት ጠገዴን በሃይል ሰብረው የመያዝ አቅም አንዳላቸው ላለፉት ሶስት አመታት በተደጋጋሚ ሲናገሩ አንደነበር ይታወሳል። የቀድሞ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደም ጦርነቱ ኣማራውን አንደማይመለከት ኣቶ ጌታቸውን ተከትለው ተናግረው ነበር። የታደሰ ወረደን ልዩ የሚያደርገው ከኦነግ ሸኔ ጋር በኦሮሚያ በኩል ኣብረው እንደሚመጡ ገልጸው አማራውን የመንካት ፍላጎት አንዳላቸው መግጻቸው አንደሆነ ንግግራቸውን የሰሙ ወዲያው ተችተዋል። ” ከሸኔ ጋር ሆነው ኣማራውን አያሳረዱ ጦርነቱ አማራውን አይመለከትም ማለት ምን ማለት ነው” ሲሉ የጠየቁ አንዳሉት አማራ ትህነግን የሚሰማበት ጆሮ የለውም ብለዋል። ኣንዳንድ ባንዳዎች በስውር በአማራ ስም የሚያደርጉትን የባንዳነት ተግባር አንዲያቆሙ ጠይቀዋል።

በማይጠብሪ በኩል ትህነግ በድርብ ምሽግ ያጠራቸውና ሲቆጣጠራቸው ከነበረበት ቦታ ተመቶ መውጣቱን የኣካባቢውን ውጊያ የሚከታተሉ አያስታወቁ ነው። በሁሉም ኣቅጣጫ የትህነግ ሃይል ውጊያ ቢጀምርም በውጊያው የት ድረስ ድል አንዳገኘ አንደወትሮው ይፋ አላደረገም። መንግስትም ቦታና ቀበሌ ጠቅሶ ስላገኘው ድል አስካሁን ይፋ ያደረገው ነገር የለም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ነው የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ የተጠራው። የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ አንዲጠራ የጠየቁት አሜሪካ፣ ፈረንሳይ፣አየርላንድ፣ ኖርዌይ፣ አልባንያ መሆናቸው ታውቋል። ለመጪው ማክሰኞ የተጠራው ስብሰባ የትህነግ ሃይል አንደታሰበው መግፋት ባለማቻሉ አንደሆነ ቅሬታ የተሰማቸው ገልሸዋል። በራስዋ ትራንስፖርት፣ ነዳጅ፣ መድሃኒት፣ ቀለብና አበል አየተወጋች ያለቸው ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር የሚጠራው ይህ ስብሰባ ምን አንደሚወስን ባይታወቅም፣ ትህነግ በደደቢት ኣቅጣጫ ሊቋቋመው ያልቻለው ጥቃት አንደተሰነዘረበት በተገለጸ ማግስት መሆኑ ከስብሰባው ጀርባ የተለመደው የተንኮል ድግስ ሰለመኖሩ በርጃቶች ከወዲሁ አያስታወቁ ነው። ከስብሰባው ቀድሞ አሜሪካ መልእክተኛዋን ወደ ኣዲስ ኣበባ እንደምትልክ ኣስታውቃለች።

ማሳሰቢያ – በሪፖርቱ ኣካባቢዎችና የጦርነቱ ዝርዝርና ምስል ያልታተመው መንግስት በሰጠውን መመሪያ መሰረት ነው

Exit mobile version