Site icon ETHIO12.COM

ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር መርማሪ ኮሚሽኑ ሊያወጣ ያዘጋጀው ሪፖርት ዓላማ ፖለቲካዊ ነው

በጭና እና ቆቦ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ በተመለከተ ቡድኑ ገና ከመነሻው ለአሸባሪው ቡድን ጥፋተኝነትን ለመከላከል የሄደበት መንገድ ትዝብት ላይ የሚጥለው መሆኑም ተመላክቷል:: በጭና ጭፍጨፋ የተፈፀመው መንግስት በወቅቱ ኅብረተሰቡ ታጥቆ የአሸባሪው ትህነግን ታጣቂ ኃይሎች እንዲዋጋ በማዘዙ የሽብር ቡድኑ አባላት ሲቪልና ተዋጊ የሆኑትን መለየት ባለመቻላቸው የተፈጠረ እንደሆነ አድርጎ አቅርቧል:: እንዲህ ዓይነት ለአንድ ወገን ያደላ ሪፖርት የፖለቲካ ሰነድ ከመባል ውጪ ሌላ ሰም ሊሰጠው እንደማይችል ተጠቁሟል::

በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተፈጽመዋል ይህንኑም አጣራለሁ በሚል የተሰየመው ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ስራውን ሳያከናውን ፖለቲካዊ አላማ አንግቦ ከመደምደሚያ ለመድረስ እየሰራ መሆኑን የኢፕድ ምንጮች አረጋገጡ፡፡ የኢትዮጵያን መከላከያ ለማጠልሸትና በአገሪቱ ላይ ጫና ለማሳደር መነሻ የሚሆን ፖለቲካዊ ድምዳሜ ላይ መድረሱም ታውቋል፡፡

 ኮሚሽኑ ጥቂት ግለሰቦችን ከኢንቴቤ/ኡጋንዳ በስልክ አነጋገርኩ በማለትና በመሰል ተጨባጭነት በሌላቸው አሉባልታዎች ላይ በመመስረት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተፈጽመዋል የሚል ድምዳሜ ላይ ለመድረስ መስራቱም ተጠቁሟል፡፡

ቡድኑ ራሱ ለተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ካውንስል ባቀረበው ሪፖርት፣ በግብአት እጥረትና መሰል ምክንያቶች የተጣለበትን ጥልቅ ምርመራ ማካሄድ እንደማይችል ማስታወቁ እየታወቀ፣ አገሪቱ ላይ የዲፕሎማሲያዊ ጫና ለማሳደር የታለመ ኢፍትሃዊና ሀቅ ላይ ያልተመሰረተ ድምዳሜ ላይ መድረሱ ተጠቁሟል፡፡

ምንጮች እንደጠቆሙት ኮሚሽኑ የተጠቀመው የጥናት ዘዴ፣ ከጥናቱ ወሰንና ከዳሰሳው ስፋት፣ ከመረጃ አሰባሰብም ሆነ ከአተናተኑ ሂደት አንጻር የተከተለው አካሄድ ሳይንሳዊ መንገድን ያልተከተለና ከዓለምአቀፍ ድንጋጌዎች ጋር የተቃረነ እና የተሳሳተ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

ኢፕድ ያገኘው መረጃ እንዳመለከተው፤ የጥናት ቡድኑ ላለፈው አንድ ዓመት ሲሰራ የቆየውን ሰነድ ይፋ ለማድረግ  በዝግጅት ላይ ይገኛል:: ሆኖም ቡድኑ ስራውን ሙሉ ለሙሉ እንዳላከናወነና ተጨማሪ በጀትና የሰው ሃይል እንዲፈቀድለትም ጠይቆ እንደነበር ምንጮቻችን ጨምረው ገልጸዋል:: በዚህ ሂደት ውስጥም ሆኖ ቡድኑ የሄደበትን ውጤት ሰሞኑን ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል::

ኮሚሽኑ ከሰው ኃይል ጀምሮ በአካባቢው የተፈፀመውን ችግር ለማጣራት በቂ አቅምና ዝግጁነት ያልነበረው እንደሆነ የኢትዮጵያ መንግስት ከመጀመሪያውም በማረጋገጡ ከመነሻው ቅሬታውን ቢያቀርብም ቡድኑ ሁለት ባለሙያዎችና ሶስት ኮሚሽነሮችን በመያዝ ብቻ ወደ ስራ መግባቱም ተጠቁሟል::

ቡድኑ ምንም አዲስ ነገር ለመስራት የሚያስችል አቅም የሌለውና እውነተኛ ስራ ለመስራት ፍላጎት ያልነበረው ስለመሆኑም ከሂደቱ ማረጋገጥ እንደሚቻል ነው ምንጮቻችን ያረጋገጡት:: የቡድኑ አባላት ገና ሲመጡ ጀምሮ ወደስፍራው ሄደው የተከሰተውን ችግር ለማየት የሚያስችል ዝግጅት የሌላቸው በመሆናቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በጋራ ያካሄዱትን ጥናት ጥሬ መረጃ በመውሰድ ዳግም ለመተንተን ጥያቄ ማቅረባቸው ታውቋል:: ሆኖም የጥምር አጣሪ ቡድኑ ባካሄደው ትንተና ላይ ዳግም ትንተና ማካሄድ ጥምር የምርመራ ቡድኑንም እውቅና ጭምር የሚክድ እና ተዓማኒነቱን የሚያሳጣ በመሆኑ የተባበሩት መንግስታት ሰብአዊ መብት አጣሪ ኮሚሽን ጭምር ጥያቄውን ሳይቀበል እንደቀረ ታውቋል::

የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ካውንስልና የኢትዮጰያ አቻው ባካሄዱት የጥናት ግብአት ላይ ተመስርቶ ወደ ሚፈለገው ፖለቲካዊ ድምዳሜ ለመድረስ ቢሞክርም ይህንኑ ግብአት ከመንግስታቱ ድርጅት ከተወከለበት ጥምር ቡድን ጭምር ማግኘት አለመቻሉ የኢትዮጵያ መንግስት ብቻ ሳይሆን ሌሎች የሰብአዊ መብት አጣሪ ኮሚሽኖች ጭምር በቡድኑ ላይ እምነት እንዳልተጣለበት እንደሚያሳይ የኢፕድ ምንጮቹ አስረድተዋል:: ቡድኑ ችግሩ ወደተከሰተበት ስፍራ ሳይሄድ ስራውን ከውጭ ሆኖ በስልክ ሲሰራ መቆየቱን ያስታወቀው ይህ መረጃ፤ በዚህ መልኩ የሚደረግ ጥናት ተዓማኒነትና ተቀባይነት የሌለው ነው ተብሏል::

ቡድኑ ያተኮረው ተከስተውባቸዋል ከተባሉ ስፍራዎች ውስጥ በመቀሌ ፣ በቆቦና ጭና እንዲሁም በደደቢት ላይ ብቻ መሆኑ ጥናቱን ጎዶሎ የሚያደርገው ሲሆን፤ ቡድኑ የሄደበት የጥናት አካሄድም ሙሉ ለሙሉ የጥናት መስፈርቶችን ያላሟላ እንደሆነም በማስረጃዎች ተጠቅሷል:: ከዚህ አንጻር ሪፖርቱ ለአንድ ወገን የሚያዳላና የፖለቲካ ይዘት ያለው እንደሆነ ተጠቁሟል:: ለአብነትም ገና ከመነሻው ጦርነቱን ማን ጀመረው በሚለው ላይ እውነታውን ክዶ የሚነሳ እንደሆነ ነው የታወቀው::

ከዚህ አንጻር መላው የዓለም ህዝብ ጦርነቱን አሸባሪው ትህነግ እንደጀመረው እየታወቀና ራሱ የሽብር ቡድኑ በተለያዩ አጋጣሚዎች ምስክርነቱን ሰጥቶ እያለ ሰነዱ “የፌዴራል መንግስት እና የትግራይ ክልል አንዱ በሌላው ላይ በማሳበብ” በሚል የጦርነቱን መነሻ ለመሸፈን ያደረገው ጥረት የቡድኑን አይን ያወጣ ወገንተኝነት ያሳያል ተብሏል::

በሌላ በኩል የመቀሌው የሰብአዊ መብት ጥሰትን በተመለከተ ቀደም ሲል የተባበሩት መንግስታት እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት የጋራ ኮሚቴ ማጣራት አድርጎ እያለ ድጋሚ ለማጥናት መነሳቱ ጥናት በተካሄደበት ስፍራ በድጋሚ ጥናት መካሄድ የለበትም የሚለውን የጋራ ስምምነት የጣሰ እንደሆነም ተጠቁሟል:: የጥናቱ ዘዴን በተመለከተ በርካታ እርስ በርስ የሚጣረሱ መረጃዎች የታጨቁበት እና ወደ እውነታው ለመንደርደር የማያስችሉ፣ የመረጃ አሰባሰብ ሂደቱም ወደእውነታ ለመድረስ የሚያስችሉ እንዳልሆኑ ሰነዱን የውሸት ለመሆኑ ምስክሮች ናቸው::

ለአብነትም መግደል፤ መድፈር፣ መጨፍጨፍ፤ ወዘተ የሚሉ ቃላትን በሪፖርቱ ውስጥ ቢያካትትም ነገር ግን ቡድኑ መረጃዎችን ያጣራው በስልክ ከመሆኑ አንጻር ይህንን ለማወቅ የሚከብደው እንደሆነ ተጠቁሟል:: ለምሳሌ በመቀሌ ሴቶች መደፈራቸውን ከጠቀሰ በኋላ ማስረጃ ያደረገው አንድ ሃኪም ምስክር መሆኑ ምንም ዓይነት የጥናት መልክ የሌለው ሰነድ እንደሆነ ያመላክታል ተብሏል::

ቡድኑ በመቀሌ ማረሚያ ቤት ዘረፋ እንደተፈፀመ ይገልጻል:: ነገር ግን የአሸባሪው ትህነግ ኃይሎች በመከላከያ ኃይል ተመትተው ሲወጡ አስር ሺህ የሚሆኑ ታራሚዎችን ፈትተው በመሄዳቸው እነዚህ ሰዎች ማስረጃ እንዳይገኝባቸው ዘርፈው እንደሄዱ ይታወቃል:: ይህ እየታወቀ እንዲህ ዓይነት ያፈጠጡ እውነቶችን በመካድ ችግሩን የፈፀመው የመንግስት ኃይል እንደሆነ ለማሳየት መሞከሩ የሰነዱን ተአማኒነት ያሳጣል::

በጭና እና ቆቦ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ በተመለከተ ቡድኑ ገና ከመነሻው ለአሸባሪው ቡድን ጥፋተኝነትን ለመከላከል የሄደበት መንገድ ትዝብት ላይ የሚጥለው መሆኑም ተመላክቷል:: በጭና ጭፍጨፋ የተፈፀመው መንግስት በወቅቱ ኅብረተሰቡ ታጥቆ የአሸባሪው ትህነግን ታጣቂ ኃይሎች እንዲዋጋ በማዘዙ የሽብር ቡድኑ አባላት ሲቪልና ተዋጊ የሆኑትን መለየት ባለመቻላቸው የተፈጠረ እንደሆነ አድርጎ አቅርቧል:: እንዲህ ዓይነት ለአንድ ወገን ያደላ ሪፖርት የፖለቲካ ሰነድ ከመባል ውጪ ሌላ ሰም ሊሰጠው እንደማይችል ተጠቁሟል::

በአጠቃላይ የቡድኑ የመጨረሻ ግብ መንግስት ሰብአዊ ርዳታን እንደ ጦር መሳሪያ ተጠቅሟል በሚል የሀሰት ክስ የኢትዮጵያን የመከላከያ ሰራዊት እና የመንግስትን ስም ማጠልሸት መሆኑን ምንጮቻችን ጠቁመዋል::

በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ ዘመን መስከረም 8/2015

Exit mobile version