Site icon ETHIO12.COM

605 በወንጀል የተጠረጠሩ የባንክ ሂሳቦች በፋይናንስ ደህንነት ታገዱ

በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ በህገወጥ የተገኘን ሃብት ህጋዊ ለማድረግ፣ በውጭ አገር የገንዘብ ማስተላለፍና ሊሎች ከፋይናንስ ህገወጥ አሰራር ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ 605 የሂሳብ ሂሳቦች መታገዳቸው ተገለጸ።

ከፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ ሙሉ ቃል ሙሉ በሙሉ ከስር ያለው ነው ቀርቧል።

የኢፌዲሪ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ከህገ-ወጥ የውጭ አገራት ገንዘብ ማስተላሇፍ ወንጀሎች ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የተጠረጠሩ 665 (ስድስት መቶ ስልሳ አምስት) የባንክ ሂሳቦች እንዳይንቀሳቀሱ አገደ።

በአገልግሎቱ የታገዱት የባንክ ሂሳቦቹ ህጋዊ የውጭ አገራት ገንዘብ ማስተላሇፍ ፈቃድ ሳይኖራቸው በህገ-ወጥ መንገድ በአገር ውስጥ እና በውጭ አገራት ከለ አካላት ጋር ትስስር በመፍጠር በህገ-ወጥ መንገድ የገንዘብ ማስተላለፍ ተግባር ላይ ተሰማርተው የተገኙ ሲሆኑ በወንጀል ድርጊቶቹ ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ተሳትፎ የነበራቸውን አካላት በህግ ተጠያቂ ሇማድረግ የተጠናከረ ሥራ በመከናወን ላይ ይገኛል።

የተለያዩ የወንጀል ድርጊቶችን በመፈፀም የተገኘን ሃብት ከህጋዊ ምንጭና በህጋዊ መንገድ የተገኘ በማስመሰል የመጠቀም ወንጀሎች አፈፃፀም በየጊዜው እየተቀያየረ ያለ ወንጀል ከመሆኑም ባሻገር ከወንጀል ድርጊቶቹ የተገኘው ሃብት ሽብርተኝነትን በገንዘብ ለመርዳት ወንጀል መፈፀሚያ ጭምር የሚውል በመሆኑ የመከላከልና መቆጣጠር ስራው በተጠናከረ አግባብ በመከናወን ላይ ይገኛል።

ስለሆነም የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እነዚህን ወንጀሎች ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚያደርገው ሂደት ህብረተሰቡ መረጃና ጥቆማ በመስጠት የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል በዚህ አጋጣሚ ጥሪ ያቀርባል።

የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት

Exit mobile version