Site icon ETHIO12.COM

ኢትዮጵያ የ24 ስዓት መረጃ

🇪🇹 መረጃ 1 ከኢፕድ የተገኘ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን የጋራ መክፈቻ ሥነ-ስርዓት ተካሂዷል።

የሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች 2014 ዓ.ም መንግስት የሰሜኑ ጦርነት በሰላም እንዲቋጭ በርካታ ጥረቶች ያደረገበት ዓመት ነበር።

መንግስት የአገሪቱን ጥቅም ባስከበረና ዘላቂነት ባለው መልኩ ከህወሓት ጋር ድርድር እንዲደረግ የተቻለውን ጥረት ማድረግ ይገፋበታል። ይህንን የሰላም አማራጭ በመርገጥ ለሚደረግ ማንኛውም ትንኮሳ አስፈላጊው የማስተገሻ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ሊሰመርበት ይገባል ብለዋል።

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=412109224445872&id=100069403920568
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=412099241113537&id=100069403920568

🇪🇹 መረጃ 2 ከኢፕድ የተገኘ

የሁለቱ ምክር ቤቶች አባላት የሳይንስ ሙዚየም እና ፓን አፍሪኮን ኤ.አይ 2022 ዐውደ ርዕይን ጎበኙ

የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶቸ አባላት የሳይንስ ሙዚየም እና ፓን አፍሪኮን ኤ.አይ 2022 ዐውደ ርዕይን ጎብኝተዋል።

ሀገራዊ ችግሮችን በዚህ መልኩ ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት በእጅጉ እንደሚያበረታቱ ጎብኚዎቹ ገልጸዋል።
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=412195084437286&id=100069403920568

🇪🇹 መረጃ 3 ከኢፕድ የተገኘ

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች መሰጠት ተጀምሯል

የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የመጀመሪያው ዙር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መሰጠት ተጀምሯል።
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=411929681130493&id=100069403920568

🇪🇹 መረጃ 4 ከኢዜአ የተገኘ

በስንዴ ልማት የተመዘገበው የላቀ ውጤት በሌሎችም መስኮች ከቀጠለ ፈጣን እድገትና የዳበረ ኢኮኖሚ መገንባት ያስችላል

ኢትዮጵያ በስንዴ ልማት ያስመዘገበችው የላቀ ውጤት በሌሎች ልማቶች ከቀጠለ በፈጣን እድገት አስተማማኝ ኢኮኖሚ መገንባት የሚያስችል መሆኑን የምጣኔ ሃብት ምሁራን ገለጹ።

በ2015 ዓ.ም በአገር አቀፍ ደረጃ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በመስኖ በማልማት 52 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ለማምረት እቅድ ተይዟል።

ኢትዮጵያ ባለፉት አራት ዓመታት በአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ትኩረት ሰጥታ እያከናወነቻቸው ካሉ ተግባራትና ስኬት ከተመዘገበባቸው መካከል የስንዴ ልማት ይጠቀሳል።

🇪🇹 መረጃ 5 ከኢፕድ የተገኘ

የአሸባሪው ትህነግ መሪዎች ሥልጣናቸውን ለማስመለስ ሲሉ የትግራይን ወጣት እያስጨረሱ ነው

ጥቂት የአሸባሪው ትህነግ መሪዎች ሥልጣናቸውን ለማስመለስ ሲሉ የትግራይ ህፃናትና ወጣቶችን በጦርነት በመማገድ እያስጨረሱ ይገኛሉ ሲሉ የትግራይ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ትዴፓ) መስራችና አማካሪ አቶ መኮንን ዘለለው ገለጹ፡፡ https://www.press.et/?p=83185

🇪🇹 መረጃ 6 ከኢፕድ የተገኘ

የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ከወንጀል ተግባር ጋር ግንኙነት ያላቸው የባንክ ሂሳቦችን አገደ

የኢፌዲሪ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ከህገ-ወጥ የውጭ አገራት ገንዘብ ማስተላሇፍ ወንጀሎች ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የተጠረጠሩ 665 የባንክ ሂሳቦች እንዳይንቀሳቀሱ አገደ።
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=412138164442978&id=100069403920568

🇪🇹 መረጃ 7 ከኢዜአ የተገኘ

ከ560 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በመውሰድ ላይ ናቸው – ትምህርት ሚኒስቴር

በ130 ማዕከላት ከ560 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በተረጋጋና በሰላም እየወሰዱ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንዲሁም ሚኒስትር ዴኤታዎች የፈተናውን አጀማመርና አጠቃላይ ሂደት በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።

🇪🇹 መረጃ 8 ከኢፕድ የተገኘ

በግብዓት እጥረት ምክንያት ስጋት ላይ ወድቄያለሁ ሲል ቱ ብራዘርስ ፉድ ኮምፕሌክስ ገለፀ

የቱ ብራዘርስ ፉድ ኮምፕሌክስ ፋብሪካ በማምረቻ መሳሪያ እና ጥሬ እቃዎች ችግር ምክንያት ስጋት ላይ መሆኑን አስታወቀ።

ከውጭ ምንዛሬ ፍላጎት ጋር ተያይዞ ቅድሚያ ኤክስፖርት ለሚያደርጉት ቅድሚያ ለመስጠት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት መደረጉንና ለተግባራዊነቱም አቅጣጫ እስኪሰጥ እየተጠበቀ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል።https://www.press.et/?p=83193

🇪🇹 መረጃ 9 ከኢፕድ የተገኘ

72 ተቋማት የኤሌክትሮኒክስ የመንግሥት ግዥ ሥርዓትን መጠቀም ጀመሩ

በ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት 72 የሚደርሱ መስሪያ ቤቶች የኤሌክትሮኒክስ የመንግሥት ግዥ ሲስተምን መጠቀም መጀመራቸውን በመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን የኤሌክትሮኒክስ የመንግሥት ግዥ ሲስተም ፕሮጀክት ማናጀር አስታወቁ፡፡ https://www.press.et/?p=83184

🇪🇹 መረጃ ከኢዜአ የተገኘ

በአፍሪካ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከምንጊዜውም በላይ ዓለም አቀፍ ትብብር ያስፈልጋል

አፍሪካ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ለምታደርገው ጥረት ከምንጊዜውም በላይ ዓለም አቀፍ ትብብር እንደሚያስፈልጋት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትርና የአፍሪካ አረንጓዴ አብዮት ጥምረት (አግራ) የቦርድ ሊቀመንበር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ገለጹ ።

የአፍሪካ ህብረት በአህጉሪቷ አንገብጋቢ የሆነውን የምግብ ዋስትናን እና የተመጣጠነ ምግብ ተደራሽነትን በተመለከተ ዛሬ በአዲስ አበባ ጉባኤ አካሄሂዷል።

Via ዛሬ በኢፕድ ዐይን

Exit mobile version