Site icon ETHIO12.COM

ነዳጅ? ግሪክና ቱርክ አለመግባባታቸውን በሰላም እንዲፈቱ አሜሪካ ጥሪ አቀረበች

በሁለቱ ሀገራት መሀከል ያለው አለመግባባት ግሪክንም ቱርክንም ኔቶንም አይጠቅምም ብሎዋል በግሪክ የአሜሪካ አምባሳደር Ambassador Tsunis በሁለቱ ሀገራት መሀል ያለው አለመግባባት በዲፕሎማሲያዊ ውይይት ይፈታል የሚል ተስፋ አሜሪካ እንዳላት ገልፆዋል።

ቱርክ አሜሪካ ና የአውሮፓ ሀገራት ገለልተኛ አደሉም የግሪክ ደጋፊ ናቸው ትላለች።

ቱርክ ግሪክን ብታጠቃ አሜሪካ ምን ታደርጋለች ተብሎ የተጠየቀው አምባሳደሩ ጥንቃቄ የተሞላበት ምላሽ ሰጥቶዋል። ግሪክ እራሷን ትከላከላለች ብለን እናምናለን ነገር ግን ከዛ ሁሉ በፊት ሰላም ስለሚሻል ለሠላም እንሰራለን ብሎዋል።

Ambassador Tsunis አሜሪካዊ ቢሆንም ወላጆቹ ከግሪክ ወደ አሜሪካ ተሰደው የሄዱ ናቸው።

በቱርክና ግሪክ መሀል ባለው የ Aegean ደሴቶች ላይ በሁለቱ ሀገራት የድንበር ውዝግብ አለ።

ራሺያ በቱርክ በኩል ወደ አውሮፓ የነዳጅ ቧንቧ ልትሰራ መሆኗን ከገለፀች በኋላ ቧምቧው ያልፍበታል ተብሎ በሚታሰበው የ Black sea ቀጠና ቅርበት ባለው የግሪክ ባህር 6 የጦር ሰፈሮች ልታቋቁም እንደሆነ ገልፃለች። ግሪክም ስትራቴጂካዊ ቦታውን ለአሜሪካ ለመስጠት ፈርማለች።

ግሪክ በኦቶማን ቱርክ አስተዳደር ለ 600 አመት ስትገዛ ነበር። የኦቶማን ኢምፓየር ግዛት ህዝቦች በየቦታው የአመፅ ትግል ሲጀምሩ የባልካን ሀገራት የሚባሉት እነ ግሪክ ሰርቢያ አልባኒያ ክሮሺያ ሜቄዶንያ የአረብ ሀገራት ና ሌሎችም የቱርክ ግዛቶች አመፁ። በወቅቱ ቱርክ ከእንግሊዝ ራሺያ ፈረንሳይና ሌሎች በርካታ ሀገራት ያለማቋረጥ ለ 5 አመታት ያህል ስትዋጋ ነበር። ጦርነቱ ከአንደኛው የአለም ጦርነት የቀጠለ ነበር። በወቅቱ እንግሊዝ ፈረንሳይ ህንድ አውስትራሊያ ኒው ዚላንድ ና ሌሎችም ጦር ቱርክ ላይ በ Dardanelles በኩል ኢስታንቡልን ለመያዝ ከባድ ጥቃት ከፍተው ነበር። ለብዙ አመታት ከቱርክ ሰራዊት በብዛትም በቴክኖሎጂም በመሣርያም የማይመጣጠን ከፍተኛ ጦር ይዘው ቢዘምቱም በቱርክ ተመክተው ተመለሡ ዋና ከተማ ኢስንቡልን ለመቆጣጠር ቀርቶ ከድንበር ለማለፍም አልቻሉም።

በምስራቅ ግንባር ግሪክ ከሌሎች አጋሮቿ ጋር ሆን 300,000 ወታደር በርካታ መሣርያና ፕሮፌሽናል ሰራዊት ይዛ እስከ Izmir ደርሳ የነበረ ቢሆንም 80,000 የሠው ብዛትና እጅግ አነስተኛ ትጥቅ 5,000 ፈረሰኛ ብቻ በያዙ የተደራጁ የቱርክ ወጣቶች በተከፈተባት የመልሶ ማጥቃት በአሳፋሪ ሁኔታ ተሸንፋ ወታደሮቿ አብዛኞቹ አልቀው የቀሩት በሙሉ ከነ ትጥቃቸው ተማርከው ይዞታዋን መልሳ አስረክባ ለቃ ለመውጣት ተገደደች።

በነ ዊንስተን ቸርችል ይመራ የነበረው የእንግሊዝ ፈረንሳይ አየርላንድ አውስትራሊያ ኒውዚላንድና ሌሎችም ምእራብ ሀገራት ጥምር ጦር አንድም ቦታ መያዝ ሳይችል ብዙ ሰው ሰውቶ መሣርያ አስረክቦ ወደ ሰላማዊ ውይይት መጥቶ 1923 ላይ የሠላም ውይይት ከቱርክ ጋር ተፈራረመ። በጦርነቱ በኋላ ድል የተጎናፀፈችው ቱርክ ከስምምነቱ በኋላ ዛሬ ቱርክ ምትባለው ሀገር ሆና ተመስርታ አሁን ባለው ድንበሯ እውቅና አገኘች። ሆኖም ከግሪክ ድንበር በኩል ባለው የ Aegean sea ደሴቶች በኩል አንዳንድ አለመግባባቶች ነበሩ።

ያንን ስምምነት የድል አመት እያለች ቱርክ በየአመቱ ታከብረዋለች። ውሉ እስከ 100 አመት የሚዘልቅ ነው። በ 2023 ሊያበቃ 11 ወር ይቀረዋል። ውሉ ካበቃ በኋላ ቱርክ በስምምነቱ አልገደደም ትላለች።

ከዚህ ቀደም በተመሣሣይ የግሪክ ቆጵሮስ ከግሪክ ጋር በመሆን ቆጵሮስ ደሴት ላይ ከቱርክ ሰራዊት ጋር ተዋግተው ከቀናት ውግያ በኋላ ተሸንፈው ቱርክ 40% ያህል ቆጵሮስን ተቆጣጥራ የቱርክ ቆጵሮስ ብላ ሰይማው ነበር። አሜሪካ ና አውሮፓ እስከ አሁን እውቅና አልሰጡትም። ቱርክ ብቻ ናት እውቅና የሰጠችው።

በዛው የሜዲትራኒያን ቀጠና ነዳጅ መኖሩ ከታወቀ ጀምሮ በቱርክና ግሪክ መሀከል ያለው አለመግባባት ተባብሶ ይገኛል። ግሪክ ውስጥ የሚኖሩ 200,000 ያህል የቱርክ ቋንቋ ተናጋሪዎች መብትም አንዱ የውዝግባቸው ምንጭ ነው።

በቅርቡ የቱርኩ ኤርዶጋን የሆነ ቀን ማታ ላይ ግሪክ እንገባለን ማለቱ በግሪክ በኩል ከባድ ስጋት ሆኖ ይገኛል።

Daily Sabah

Exit mobile version