Site icon ETHIO12.COM

የ “ነጻ አውጭ ” ፖለቲካ የህግ ክልከላ አንዲደረግበት አብን ጠየቀ

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ ፓርቲዉ በመግለጫዉ ካነሳቸዉ ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል፡-

፩. በሰላም ሥምምነቱ በተቀመጠው አግባብ የሽብር ቡድኑ ትጥቁን እንዲፈታ መንግስት በሙሉ አቅሙ እና ትኩረት እንዲሰራ፤

፪. የ “ነጻ አውጭ ግንባሮች” ፖለቲካዊ ኅልውና ሕጋዊ እውቅና በሚያገኝበት ሀገር ፣ የሀገር ሉዐላዊነት ፣ የግዛት አንድነት እና ሀገራዊ አንድነት ማረጋገጥ የማይቻል በመሆኑ ፤ መንግስት ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጭ እያለ የሚጠራው ቡድን እና መሰል “ነጻ አውጭ” ቡድኖች የፖለቲካ ኅልውናቸው እንዲከስም እንዲሰራ እና የሕግ ክልከላ ስራ ላይ እንዲያውል፤

፫. የአማራ ሕዝብ ክፋይ የሆኑት እና ከ30 ዓመት በላይ በአማራዊ ማንነታቸው ምክንያት የዘር ማጥፋት ወንጀል የተፈጸመባቸው የወልቃይት እና የራያ አካባቢዎች አሁን ባሉበት አማራ ክልል ሥር ሕጋዊ እውቅና እንዲያገኙ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና የፌዴራሉ መንግስት በአፋጣኝ የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ፣ እና

፬. በአሸባሪው ትሕነግ ጀማሪነት በሶስት ተከታታይ ዙር በተካሄደው የወራራ ጦርነት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን የአማራ፣ አፋር እና ትግራይ አካባቢዎች መልሶ የመገንባት እና የማቋቋም ሥራ የፌደራል መንግሥቱ በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት እንዲመራና እንዲያስተባብር፣ መላው ኢትዮጵያውያንም ለመልሶ ግንባታው እና መቋቋሙ ሥራ ድጋፍ እንዲያደርጉ ንቅናቄዉ ጠይቋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

Exit mobile version