Site icon ETHIO12.COM

“ስምምነቱን የጣሰ ማዕቀብ ይጠብቀዋል” አሜሪካ

የኢትዮጵያ ፈደራዊ መንግስትና ህወሓት በቅርቡ የተፈራረሙትን ስምምነትን የሚያዉኩ ወገኖችን በማዕቀብ እንደምትቀጣ አንድ የአሜሪካ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ከፍተኛ ባለስልጣን አስጠነቀቁ።

የአሜሪካ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ከፍተኛ ባለስልጣን» ከሚለዉ ማዕረግ ሌላ መደበኛ ስምና ማዕረጋቸዉ በሚስጥር የተያዘዉ ባለስልጣን እንዳሉት፣ በአፍሪቃ ሕብረት ሸምጋይነት የተደረገዉን የሁለቱን ወገኖች ድርድር አሜሪካ በቅርብ ስትረዳና ስትተባበር ነበር።

ባለስልጣኑ ስለስምምነቱ ማባራሪያ በሰጡበት መግለጫዉ እንዳሉት ሁለቱ ወገኖች እንዲስማሙ ከዋይት ሐዉስ እስከ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር፣ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ በየሐገሩ እስከሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲዎች ባለስልጣናት፣ዲፕሎማቶችና ሰራተኞች ከፍተኛ እገዛ ማድረጋቸዉን ጠቅሰዋል።

እንደ ዶቸቨለ ዘገባ ባለስልጣኑ ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላ ተፈራራሚ ወገኖች የሚሉትና የሚያደርጉት እንቅስቃሴም አበረታች ነዉ ብለዋል፡፡

ባለስልጣኑ «ዩናይትድ ስቴትስ ማዕቀብ መጣልን ሁል ጊዜ የመርሕዋ መሳሪያ አድርጋ ትጠቀምበታለች።በሰብአዊ መብት ረገጣ የሚጠየቁ ተዋኞችን (ወገኖችን) ተጠያቂ ለማድረግ ወይም ይሕ ስምምነት እንዲከበርና በትክክል ገቢር እንዲሆን አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ማዕቀብ ለመጣል አሜሪካ አታመነታም» ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዓብይ አሕመድ መንግስታቸዉ ስምምነቱን «በታማኝነት» ገቢር እንደሚያደርግ ማስታወቃቸዉ ይታወሳል።
የዓለም ቀይ መስቀል ኮሚቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የላከዉ መድሐኒትና የሕክምና ቁሳቁስ ትናንት መቀሌ መደረሱ መገለጹ አይዘነጋም።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

Exit mobile version