Site icon ETHIO12.COM

ትህነግ ኢትዮጵያንና ኤርትራን ማጣላት ቀዳሚ አጀንዳው አድርጓል

በደቡብ ሱዳን የተከናወነውን የሰላም ስምምነት ቀደም ብሎ ትህነግ ከእማራ ጋር ምንም ዓይነት ጸብ እንደሌለው፣ የኢርትራ ህዝብም ወዳጁ እንደሆነ በተደጋጋሚ በመግለጽ የትግል ስልት ለመቀየሩ ምልክት አሳይቶ ነበር። ይህንኑ የአቅጣጫ ለውጥ ተከትሎ ትጥቅ ለመፍታት ቀነ ገደብ ቆጥሮ የፈረመው ትህነግ መንግስት የኤርትራን ሰራዊት ከትግራይ ክልል እንዲወጣ እንዲያደርገልት ለዓለም ማህበረሰብ ባሰራጨው አቤቱታ ላይ ጠይቋል።

“ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በተጨማሪ የኢትዮጵያ መንግሥትም የኤርትራ ጦር በትግራይ ሕዝብ ላይ እየፈጸመ ነው ያለውን ግፍ እና በደል በአስቸኳይ እንዲያስቆም” ሲል ማመልከቻውን ቀድሞ ለዓለም፣ ቀጥሎ ለኢትዮጵያ መንግስት ያሰማው ትህነግ፣ ከሰላም ስምምነቱ በሁዋላ የኤርትራ መንግስት ላይ ተደጋጋሚ መግለጫና ብሶት እያሰማ ነው። መንግት ይህን አስመልክቶ እስካሁን ምንም ምላሽ አልሰጠም። የኮሙኒኬሽን ሚኒስትሩ ግን በግል የማህበራዊ ገጽ አውዳቸው ላይ “ምንም ወዲያ ወዲህ ማለት የለም ስምምነቱን ተገባራዊ አድርግ” ሲሉ አሁን ላይ ያለውን ምድራዊ እውነታ በማስታወስ ምላሽ ቢጤ አመልክተዋል።

በኤርትራ የመንግስት ለውጥ ማድረግ እንዳልቻሉ የገለጹበትን የነጮቹ መረጃ በስፋት እየወጣ ባለበት በአሁን ሰዓት፣ ትህነግ ኤርትራ ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ መጀመሩ፣ ኢትዮጵያም ኤርትራ ላይ አቋም እንድትወሰድ መተየቁ፣ ይህንንም ዓለም በጫና ተግባራዊ እንዲያደርገው መወትወቱ ኢትዮጵያና ኤርትራን ለማጋጨት ያለመ እንደሆነ ከየአቅጣጫው እየተገለጸ ነው።

ሟቹ የትህነግና ኢህአዴግ ሊቀመንበር፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት አቶ መለስ ዜናዊ የፈረሙትን ይግባኝ የሌለውን የአልጀርስን ስምምነት ሲፈርሙ የባድሜና ካባቢው ጥያቄና የፈሰሰው የንጹሃን ደም ከንቱ እንደገባ ያስታወሱ እንደሚሉት፣ ትህነግ ባድመና አካባቢውን አስመልክቶ ጥያቄ የማንሳት ሞራል የለውም። ጉዳዩ የኢትዮጵያ ህዝብ ተዋሽቶ በህግ የተዘጋ የትም ይግባኝ የማይባልበት በመሆኑ የሚያዋጣው በዲፕሎማሲ አግባብ መሄድ እንደሆነም በተመሳሳይ የድንበር ውዝግብ ልምድ ያላቸው በይፋ ደጋገመው ገልጸውታል። ከለውጡ በፊት ራሱ ትህነግ በበላይነት በሚመራው መንግስት የአልጀርሱ ስምምነት ያለአንዳች ገደብና መሸራረፍ ተግባራዊ እንዲሆን መወሰኑም ይታወሳል።

ይህን የውሰነውና ያስወሰነው፣ ቀደም ሲል አዋቂዎች ትህነግን ለሙግት አልጀርስ ያቀረበው ማስረጃ ትክክል እንዳልሆነ ሲነገረው ” አያገባችሁም” ብሎ ክርከሩን በሽንፈት ከቋቸ በሁዋላ ዛሬ ላይ ያለውን መንግስት በባድመ ጉዳይ ከኤርትራ ጋር ውጊያ ግባ ብሎ መጠየቅ ነውር እንደሆን የሚገልጹ፣ ” ለሁለት አስርት ዓመታት ድንበር ሲጠብቅ የኖረውን የኢትዮጵያን መከላከያ አርደው ሲያበቁ፣ እርቃኑን ሲያሰድዱት በታደገው የኤርትራ መንግስት ላይ አሁን መሳሪያ አንሳ ብሎ መጠየቅ ትህነግ አሁን ላይ ደጋፊዎቹ እንደሚሉት ካርቶን ራስ መሆኑንን ከማሳየት አያልፍም”

በመከላከያ ሰራዊት መሪነት ጥምር ጦሩ ክፉኛ ጉዳት ያደረሰበት ትህነግ፣ በአንዳንድ ቦታዎች አገግሞ ጥቃት ለመክፈት ዝግጅት እያደረገ መሆኑ እየተገለጸ ባለበት ወቅት መንግስት ለሰላም ሂደቱ በሚበጀው አግባብ ላይ ማተኮሩ ስጋት የገባቸው ” የጥንቃቄ ያለህ” እያሉ ነው። እነዚህ ወገኖች ትህነግ በኤርትራና ኢትዮጵያ መካከል ጸብ አስነስቶ ይህንኑ የአራተኛ ጊዜ ጦርነት ለማስነሳት ዕቅድ እንዳለው ይገልጻሉ።

ስለግንባር ዝግጅት መረጃ ያላቸው እንደሚሉት የኢትዮጵያ ጥምር ሃይሎች ሰላም ቢወርድም በየቀኑ ልምምድ ማድረጋቸውን፣ በየተናውም ሰዓት መመሪያ ከደረሳቸው የሚያደርጉትን ጠንቀቀው በመረዳት በተጠንቀቅ ላይ መሆናቸውን ይገልጻሉ። እነዚህ ወገኖች እንደሚሉት የኢትዮጵያ ጦር እንደቀድሞ በቁጥር፣ በመሳሪያ፣ በሞራልም ሆነ በደጀንነት ብልጫ የሚወሰድበት እንዳልሆነ፣ ቀደም ሲል ከሆነባቸው ሁሉ በቂት ትምህርት የወሰዱ መሆናቸውንም ይናገራሉ። አጨዳም ሆነ ማናቸውንም ተግባራት ሲያከናውኑ ትህነግ የሚያጠምደውን ማናቸውንም ወጥመድ በመከታተል እንደሆነ አክለው ያስረዳሉ።

ለምንግስት ቅርብ የሆኑ እንደሚሉት ከኤርትራ ጋር አንዳችም ጸብ ውስጥ የሚከት ነገር ሊከናውን ቀርቶ እንደማይታሰብ አመልክተዋል። ትህነግ መንግስትና የአማራውን ማህበረሰብ ለማጣላት ” ፋኖ ወዳጄ፣ አማራ ወዳጄ” የሚል አዲስ አካሄድ ቢጀመርም፣ ሰሞኑንን ይፋ በሆነ ቪዲዮ ኤርትራ ሰላም ከፈለገች ከአማራና ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያላትን ግንኙነት አቁማ ከትግራይ ጋር ማደርግ ብቻ አማራጯ እንደሆነ የትህነግ አክቲቪስቶች ሲናገሩ የሚያሳይ ቪዲዮ እየተሰራጨ ነው።

ቴዎድሮስ የሚባለው የርዕዮት የዩቲዩብ ሚዲያ ባለቤትና የትህነግ ቀዳሚ ወዳጅ በቅርቡ በመረረ የስድብና የወቀሳ ውርጅብኝ ” ትህነግ የሚያደርገውን አያውቅም፣ የሚያደርገውን ያውቃል ብላችሁ ያልሰሙ አትጥሩት” ሲል ባሰራጨው ቪዲዮ ” 1.5 የሚሆን የትግራይ ህዝብ ተበትኖ በሚኖርበት የኢትዮጵያ ክፍል በነሳነት እንዳይኖር መታወቂያ ላይ ብሄር ይጽፍ ነበር” ሲል የስጋቱን ግዝፈት በማሳየት “ካርቶን ራሶች” ሲል አሳይቷል። አያይዞም አሰብን ያስረክብ ነበር ሲልም ግርምቱን ዘርዝራል። የትህነግን ቅል ራስነት ለማሳየት በርካታ ጉዳዮችን በዘለፍ ቃላት አጅቦ ያቀርበው ቴዎድሮስ ” ትህነግ ወደ መቀለ መሸሹን ድንቁርና” ብሎታል። ቴዎድሮስ ከካርቶን ውጭ ወጥቶ የማያስብና ካርቶን ራስ እንደሆነ በይፋ የሰደበው ትህነግ ” ተተኪ ፖለቲከኞች አላዘጋጀም” ሲል ከታች እስከ ላይ ያሉትን ጠርጓቸዋል።

የደቡብ አፍሪካ ስምምነትን ትህነግ እንዳልፈረመ፣ የፈረመ የትግራይ መንግስት እንደሆነ መስማቱን ጠቅሶ ቴዎድሮስ ” አልገባኝም። የገባችሁ ጻፉልኝ ወይም አስረዱኝ” ሲል ግራ እንደተጋባ በዛው “ካርቶን” ካለው ጭንቅላት የወጣውን ማምታታት እንደ ምናምንቴ አቅርቦታል። ይህን እንደ ቅርብ ማሳያ የሚወስዱ “ትህነግ አራዳ አድርጎ ራሱን ያያል። ኢትዮጵያና ኤርትራን አጣልቶ ዳግም ሊያንሰራራ ይመኛል” ሲሉ ተናግረዋል። አሁን አሁን ትህነግ ኢትዮጵያ ውስጥ ማንንም ማታለል የማይችልበት ደረጃ መደረሱን የሚጠቅሱ፣ በለውጡ ማግስት ” ቆሞ ቀር” ሲሉ የሚገልጹትን ሰዎች ቃላት በመበደር ” ከቆሞ ቀርነቱ ተላቆ ለትግራይም ይሁን ለመላው የአገሪቱ ህዝብ ሰላም ቢመኝና ለዚሁ ቢሰራ” ሲሉ ደጋፊዎቹ እንዲነቁ ጠይቀዋል።

ትሀንግ ትግራይ ልክ እንደ ጋንቤላ፣ ቤኒሻንጉል፣ አፋር፣ ሲዳማ፣ … ክልል ነች። በፌደራል አደረጃጀት በህዝብ ቁጥር መሰረት ውክልናቸውን ወስደው፣ በመከላከያና ፖሊስ ውስጥ በልካቸው ተሳትፈው ለመኖር ማመን ያቃተውና የትግራይን ህዝብ ቴዎድሮስ እንዳለው “ወዳጅ አልባ. ጎረቤት አልባ” በማድረግ በጥይት የሚያስማግዱት ለምን እንደሆነ አሁን ላይ መልሱ መፈለግ እንዳለበት የትግራይ ተውላጆችም እየጠየቁ ነው።

ኢትዮጵያና ኤርትራ የድህነትና የጸጥታ ጉዳይ ላይ አብረው ለመስራት መስማማታቸውና መፈራረማቸው ይታወሳል። ከደቡብ አፍሪካው ስምምነት በሁዋላ መከላከያ ድንበር እንደሚጠብቅና የትግራይን ክልል ስለማ እንደሚያስከብር ቢገለጽም፣ ትህነግ ከሱ የሚጠበቀውን አድርጎ የቀረው ጉዳይ በዲፕሎማሲ እንዳይፈታ ልክ እንደ ቅድመ ሁኔታ የኤርትራ ወታደሮች እንዲወጡ መጠየቁ ብዙም እንደማያስኬደው ተመክቷል።

በጎንደር በኩል ሳየቀር ለትግራይ ህዝብ እርዳታ መግባት መጀመሩን ተከትሎ መሳሪያና ተተኳሽ እንዳይገባ ሁልተ ጣቢያዎች ላይ ብርበራ እንደሚደረግና በአየር በረራ ላይም በትግራይ አየር ማረፊያዎች ላይ ብርበራ እንደሚደረግ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ባንዲራ ያለበት ያልመከነ ንጹህ ስንዴ ወደ ትግራይ መላኩ ኢትዮጵያ በቂ ስንዴ እያመረተች መሆኗን ለሚያጣጥሉ ምላሽ ሆኗል። አሁን ላይ የተጀመረው ዕርዳታና የማህበራዊ አገልግሎቶች ዳግም መጀመረ የጸነሳውን ተስፋ ዳግም አውድሞ የትግራይንና የአጎራባች ነዋሪዎችን ወደ ስቃይ መውሰድ የሚታሰብ እንዳልሆነ ትህነግ ውስጥ ያመኑ መኖራቸው ትህነግ ከሴራው በፊት በልዩነት ታሪኳን እንዳታገባድድ የፈሩላትም አሉ። የሌተናል ጻድቃንና ጌታቸው መገለጫ የሚያሳየው ይህንኑ እንደሆነ የሚተቁም ስለመሆኑም እየተገለጸ ነው።

Exit mobile version