Site icon ETHIO12.COM

ጠቁሙ 25% ውሰዱ‼

ሀብት በማስመዝገብና በማሳወቅ ሂደት፤ አመራሮችንና ባለሙያዎች ሳያስመዘገቡ የቀሩትን ሀብት የጠቆመ ዜጋ ከተጠቆመው ሀብት ላይ 25 በመቶ እንዲያገኝ እንደሚደረግ የፌደራል ስነምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታውቋል።

ለዚህም ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ በፌደራል ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የሙስ እና መረጃ አስተዳደሥ መሪ ሥራ አስፈፃሚ ፈርዳ ገመዳ የገለጹ ሲሆን፤ ይህም በአዋጅ ቁጥር 668/2002 በግልፅ መስፈሩን ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ እስካሁን 763 የመንግስት አመራሮችን ቢለይም፤ እስካሁን ሀብታቸውን ያስመዘገቡት 20 በመቶው ብቻ መሆናቸው ተጠቅሷል። ከዚህ ውስጥ 107ቱ በማንዋል 42ቱ በኦንላይን ምዝገባ ስርዓት ያከናወኑ ናቸውም ተብሏል።

ኮሚሽኑ ከFM 97.1 ጋር በነበረው ቆይታ ሀብታቸውን ያላስመዘገቡ ሰዎች በህግ ፊት ተጠያቂ ከመሆናቸው በፊት ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ጥሪውን አቅርቧል። እስካሁንም 2 ሺሕ 272 የፌደራል ተቋማት መካከለኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ሀብታቸውን ማስመዝገብ ችለዋል።

በኦንላይን ምዝገባ ስርዓቱ ላይ አልፎ አልፎ የሲስተም ችግር እየገጠመኝ ነው ያለው ኮሚሽኑ፤ ችግሩን ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሰራሁ መሆኑንም አስታውቋል።

Via ኢቢሲ

Exit mobile version