Site icon ETHIO12.COM

ከባድ የግድያ ወንጀል የፈፀመው ሁሉም መብቶቹ ለዘወትር እንዲሻር በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነ

ከባድ የሰው ግድያ ወንጀል የፈፀመው ሙሉነህ አሰፋ በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነ

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ህግ ከባድ የሰው ግድያ ወንጀል በፈጸመው ሙሉነህ አሰፋ የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲፈረድበት አደረገ፡፡

የዐቃቤ ህግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ሙሉነህ አሰፋ በ4 ክሶች የተከሰሰ ሲሆን ታህሳስ 4 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 10፡40 ሰዓት ሲሆን በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ልዩ ቦታው የካ ተራራ ትምህርት ቤት አካባቢ የቤት ቦታን አስመልክቶ ከሟች አበበ ለብሶን ጋር በነበረ ፀብ ተከሳሹ እገልሃለው ብሎ ሲዝትበት ሟች ፖሊስ ጣቢያ አመልክቶ ሲመለስ አስቀድሞ በመዘጋጀት በሽጉጥ ተኩሶ ትከሻውን በመምታት ሲገድለው በስፍራው የነበሩ አልማዝ አሰፋ እና አዲስ አሰፋን ተኩሶ ጉዳት ያደረሰባቸው በመሆኑ በፈፀመው ከባድ የሰው ግድያ እና የመግደል ሙከራ ወንጀል 3 ተደራራቢ ክሶች ቀርበውበት ክርክር ሲያደርግ ቆይቷል።

እንዲሁም ተከሳሽ ወንጀሉን የፈጸመበት ሽጉጥ የፀና ፈቃድ ያልነበረው በመሆኑ የጸና ፈቃድ ሳይኖር የጦር መሳሪያ መያዝ እና መገልገል ወንጀል ሌላ ተጨማሪ ክስ የቀረበበት በመሆኑ በአጠቃላይ በ4 የወንጀል ክስ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ 1ኛ ሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት ቀርቦ ክርክር ሲያደርግ ቢቆይም ዐቃቤ ህግ ክሱን በማስረጃ በበቂ ሁኔታ ያስረዳ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ህዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሹ ዐቃቤ ህግ ባቀረባቸው 4 ክሶች ጥፋተኛ እንደሆነ ተረጋግጦ በቅጣት አወሳሰን መመሪያ 2/2006 እርከን 38 ስር መነሻ ቅጣት በመያዝ የቤተሰብ አስተዳዳሪ በመሆኑ 1 ማቅለያ ተይዞለት በእርከን 37 ስር በማሳረፍ ተከሳሽን ያርማል ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችን ያስተምራል ያለውን በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተከሳሽ በሁሉም መብቶቹ ለዘወትር እንዲሻር ሲል ወስኖበታል፡፡

Exit mobile version