Site icon ETHIO12.COM

ኢኮኖሚውን በኮንትሮባንድ እየወጉ ያሉ [ሌባ ሃብታሞች] ተለዩ

ኢትዮጵያና ሱዳን የደረሱበትን የሰላምና የደህንነት ውል ተከትሎ አስደንጋጭ ዜና እየተሰማ ነው። ሱዳን ለከተመ የቅባት ዕህል ገዢ ድርጅት በኮንትሮባንድ የሚያቀርቡት “ሌባ” የተባሉ የሚታወቁ ባለሃብቶች መለየታቸው ነው አስደንጋጭ የሆነው።

ሱዳን በክልሏ ኢትዮጵያ ላይ መሳሪያ አንስተው የሚዋጉ ሃይሎችን አሳልፋ እንደምትሰጥ ፈርማ ወደ ተግባር መግባቷን ተከትሎ ቀጣዩን የኢኮኖሚ አጀንዳ ተግባራዊ ለማድረግ በተደረገ ስምምነት መሰረት በጋራ ድንበር ተሻግሮ የሚወጣ ኮንትሮባንድ ለመቆጣጠርም የያዙትን ዕቅድ ሊተገብሩ መሆኑንን ጉዳዩን የሚያውቁ ለኢትዮ12 አስታውቀዋል። ኮንትሮባንዱን በማምከን ረገድ ሱዳን ጥቅም እንደምታገኝም ታውቋል። ይሁን እንጂ ዝርዝሩ አልተጠቆመም።

የኢትዮጵያ የቅባት ዕህልም ሆነ ሌሎች ሰብሎች ከፍተኛ የምርት ዕድገት ቢያሳዩም የውጭ ምንዛሬ ገቢው ብዙም አለማደጉ የኮንትሮባንድ ንግዱ ጣጣ እንደሆነ በጥናት ቀርቧል። ለኢሲኤክስ Ethiopia Commodity Exchange ቅርብ የሆኑ እንዳሉት የሚታወቁ ነጋዴዎች የቅባት ዕህል በሚፈለገው ደረጃ እያቀረቡ አይደለም። ይህም የሚሆነው በኢሲ ኤክስ በኩል የተለያዩ ባለሃብቶች ገዝተው አስፈላጊውን ሂደት አከናውነው ወደ ውጭ በመላክ እንዳይጠቀሙ፣ በኮንትሮባንድ በማሻገር ገንዘቡን በውጭ ባንክ ለመደበቅና ኢኮኖሚውን ለመጉዳት እንደሆነ አመልክተዋል። ስራውም የሚሰራው በዚሁ ትሥር እንደሆነ ገልጸዋል።

እነዚህ ሃይሎች የጎጥና የጎበዝ አለቃ እንደሚያደራጁ፣ በውጭ አገርና በአገር ውስጥ ሚድያ እየቀለቡ ሽብርን እንደሚያሰራጩ፣ የሰላምና የመረጋጋት ዜናን የሚቃወሙ ሃይሎች ያላቸው፣ በየቦታው በመዘዋወር ለበቀል የሚያነሳሳ ሃይል የሚያሰማሩ ወረበሎች እንደሆኑ ዜናውን የጠቆሙ አመልክተዋል።

መንግስት ጦርነት ላይ ስለነበር፣ ይህንኑ ተገን በማድረግ እስካሁን ባለው መረጃ በገፍ የተመረተ ሰሊጥ ወደ ሱዳን መኪና በማስለፍ የሚያግዙበት ከነተባባሪያቸው መለየታቸው ተሰምቷል። የሰላም ስምምነቱን በማንጋደድ ሌላ ሁከትና ረብሻ እንዲነሳ እየሰበኩ ያሉት የእነዚሁ ዱርዬ ህባታም ተከፋዮች እንደሆኑ፣ ሌሎችም ሳይገባቸው ይህንኑ ፈጠራ እያራቡ እንደሆነ ነው የተመለከተው።

ሱዳን የኮንትሮባንዱን መስመር ለመዝጋት በወሰነችው መሰረት መከላከያ በሙሉ ስልጣንና ሃላፊነት በኮንትሮባንድ የሚወጣውን ሰሊጥና ሌሎች የቅባት ዕህሎች ማገድ እንደሚጀምር፣ በዚህ ስራ ውስጥ የተሳተፉና እየተሳተፉ ያሉ ለህግ እንደሚቀርቡ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ይህንኑ ተከትሎ በሌብነት ላይ የሚወሰደውን እርምጃ የብሄር ታፔላ ለመስጠት መተርተር ቢጀመርም መንግስት እንደማይራራ መረጃውን የሰጡ አመልክተዋል። ሰሞኑንን በዳቦ ቤት ምረቃ ላይ ” በሌብነት ላይ የተጀመረው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል” ሲሉ አብይ አህመድ መናገራቸው ይታወሳል።

በርካታ ጥቆማ በሰሊጥ ዘርፊያና ኮንትሮባንድ ዘርፍ መቅረቡ፣ ምርት በገፍ የመመረቱን ያህል ለኢ ሲ ኤክስ አለመቅረቡ ተዳምሮ መንግስት ታጋሽነቱ በመሟጠጡ ወደ እርምጃ ለመግባት መገደዱ ነው የተሰማው።

በተመሳሳይ በኦሮሚያ “ቡና ለኢ ሲ ኤክስ አናቀርብም” በሚል በፉክክር ደባ የጀመሩ እንዳሉ ታውቋል። ” በህጋዊ መነገድ ሰሊጥ ኢ ሲ ኤክስ ቀርቦ ካልገዛን እኛም ቡና ለኢ ሲ ኤክስ አናቀርብም” በሚል ኢኮኖሚው ላይ በዕንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሊሆኑበት እያስፈራሩ ያሉ መኖራቸውን ኢትዮ12 ሰምታለች። የአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ከድርጅቱ መረጃ ለማግኘት ቢሞክርም አልተሳካም። ኢ ሲ ኤክስ የሚየገባየው ምርት ቢጨምርም በአገሪቱ ከጨመረው የምርት ብዛትና አይነት አንጻር የውጭ ምንዛሬ ገቢው በሚጠበቀው ደረጃ ከፍ እለማለቱ የጓሮ ንግዱ መጧጧፉን አምለካች እንደሆነ ማሳያ ሆኗል።

በወልቃይት ሁመራ ከፈተኛ የሰሊጥና የጥጥ ምረት መመረቱን ተከትሎ ገበያው እንዳይረክስ ሲወተውቱ የነበሩ መኖራቸው ይታወሳል። ይህ ችግር ነጋዴዎችን ወደ ኮንትሮባንድ ወስዷቸው ስለመሆኑ መረጃው ባይኖርም፣ የቅባት ዕህል ወደ ሱዳን እንደሚጋዝ ግን በቂ ማስረጃና መረጃ አለ።

ቀደም ሲል የመጀመሪያው ወረራ ተጀምሮ ክተት ሲጠራ ከፈተኛ መጠን ያለው ሰሊጥ መጋዘን እየሰበሩ ሲዘርፉና ወደ ጎጃም ሲያጋግዙ የነበሩ ዱርዬ ሃብታሞችና ሹመኞች በገሃድ ስማቸው ተጠቅሶ ሲዘገብ ነበር።

ኢትዮጵያ ውስጥ ለዘይት ማምረቻ መንግስት በከፍተኛ ወጪ የሚጨመቀውን ድፍድፍ እያስገባላቸው፣ በኮንትሮባንድ እየተሳተፉ ሃብት የሚያሸሹ፣ የጎበዝ አለቃ በሚያደራጁና ሽብርን በተዘዋዋሪ ስፖንሰር የሚያደርጉ ከነ ሙሉ ትሥሥራቸው ለህግ የማቅረቡ ስራ መጠናቀቁን የገለጹ እንዳሉት፣ የሰላም ስምምነቱ ለዚህ እርምጃ መፋጠን ወሳኝ እንደሆነ ገልጸዋል።

በተመሳሳይ የሌብነት ዜና ወርቅ፣ የቁም ከብት፣ እንዲሁም ቡናና የከበሩ ማዕድናትን በሞያሌና በሶማሌ በኩል የሚያስወጡ ላይ በተመሳሳይ የተጠናከረ እርምጃ ለመውሰድ፣ ከነዚሁ ወገኖች ጋር በቁርኝት የሚሰሩ የመንግስት ሰዎችንም የመልቀም ስራ አብሮ እየተሰራ መሆኑ ታውቋል።

በርካታ ኢትዮጵያን በስራ አጥነት፣ በተስፋ መቁረጥና ራስን ለመቻል በሚል በባህርና በየብስ ወደ ሌሎች አገራት ሲጓዙ ህይወታቸው ማለፉ፣ የወጡትም የገሃነብ ኑሮ እየኖሩ መሆኑ እየተሰማና በሺህ የሚቆጠሩ ወገኖች ወደ አገራቸው እየተጋዙ ባለበት ሁኔታ አገራቸውን በሚዘርፉ ወረበሎች ላይ መንግስት እርምጃ እንዲወስድ የሚቀርበው ጥቆማ ከፍተኛ መሆኑን የፍትህ ሚኒስቴር ማስታወቁ አይዘነጋም።

Exit mobile version