ETHIO12.COM

ኢትዮጵያና ኤርትራ ምሽግ ተቀያየሩ፤ ጌታቸው ረዳ አሁንም [እየፈሰሱ] ነው

Ethiopie, juni 2000 Grensconflict, oorlog tussen Ethiopie en Eritrea. Photo: Petterik Wiggers/Hollandse Hoogte Ethiopia, june 2000 War between Ethiopia and Eritrea. Near Zalambessa, recaptured by Ethiopian Forces. The Ethiopians are retreating due to a shaky peace agreement. The army has enough trucks for transportation while in the Ogaden desert people are starving. Captured Eritrean tanks by the Ethiopian army. War between Ethiopia and Eritrea. Near Zalambessa, recaptured by Ethiopian Forces.

ወደ ትግራይ ክልል ዘልቆ የነበረው የኤርትራ ጦር ምሽጉን ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በማስረከበ እይየወጣ ነው። ይህ የሆነው ኢትዮጵያና ኤርትራ ቀደም ብለው በደረሱት ስምምነት መሰረት ነው። የትግራይ ቲቪ አቶ ጌታቸውን ጠቅሶ ስህተት አሰራጭቷል። የመንግስት ኮሙኒኬሽን ተመሳሳይ ግድፈቶችን ሳይወል ሳያድር እንዲስተካከል ማድርግ እንዳለበት አስተያየት ተሰጥቷል።

በችግሩና በክህደቱ ወቅት የኢትዮያን መከላከያ ሰራዊት እጁን ዘርግቶ እንደተቀበለ የተመሰከረለት የኤርትራ መንግስት ጦሩን ያስወጣው ከአድዋ ፣አክሱም፣ ሽሬ፣ ሸራሮና፣ሰለክለካ እንዲሁም በአካባቢው ካሉ ትናንሽ መነደሮች ነው።

የሶስተኛ ጊዜው ወረራ ሙከራ ከመደረጉ በፊት በኢትዮጵያ መንግስት የጸጥታና ደህንነት ግምገማ “ትህነግ ካሁን በሁዋላ በአካባቢው ካለው ሃይል በላይ ተጨማሪ ሃይል አያስፈልገውም። ስጋትም አይደለም” ተብሎ እንደነበር፣ ወደ ቆቦ ዳግም ከመጣም በሁዋላ በሁሉም ግንባር በቅንጅት በተደረገ ማጥቃት ወቀለ ዙሪያ ሲቀረው በወዳጆቹ ጩኸት የተጠየቀውን ሁሉ “አደርጋለሁ” በሚል ፈርሞ አመራሩ ከመከላከያ ጡንቻ መትረፉም ገሃድ የታየ ሃቅ ነው።

ዜናውን የነገሩን እንዳሉት ኤርትራ ካሁን በሁዋላ ትህነግ ስጋት እንደማይሆንባት አረግግጣለች። የኤርትራን ሰራዊት እግር ተክቶ ምሽጉን የተረከበው የኢትዮጵያ ጦር ላይም ሙሉ መተማመን አሳድራለች። ሁለቱ አገራት የወታደራዊና የደህንነት ውላቸውን ጠብቀው እንደሚሰሩም ታውቋል። ዝምታቸውም ከዚሁ የመነጨ እንደሆነ ተመልክቷል። መከላከያ የኤርትራ ሰራዊት ባለባቸው አካባቢዎች ሲገባ ሰላምታ እየተቀያየሩና በጋለ የወዳጅነት ስሜት እንደነበርም ለማረጋገጥ ተችሏል።

በአሁኑ ሰዓት ትህነግ ከየትኛውም የኢትዮጵያ ክልሎች በላይ የውጊያ አቅምና ሃይል እንደሌለው፣ ዳግም ጦርነትን ማሰብ እንዳይችል ተደርጎ መመታቱና “ቅድመ ሁኔታ ይሟላ፣ አለበለዚያ አፍንጫችሁን ይዤ የምፈልገውን አደርጋለሁ። ሳይመሽ እጃችሁን ስጡ” እያለ ማስታወቂያ ሲያሰራጭ የነበረው ትህነግ ዛሬ ላይ ልክ እንደ አንድ ክልል ህግ አክብሮ ለመኖር መስማማቱ ብዙ ትርጉም እንዳለው በርካቶች እየገለጹ ነው።

ዘጠና በመቶ የሚሆነውንና በትህነግ ተያዞ የነበረውን የትግራይ ክልል አጽድቶ፣ መቀለን ለመቆጣጠር ጫፍ ላይ ባለበት ወቅት መከላከያ ” ቆይ” መባሉንና ትህነግ ” አስቸኳይ ተኩስ ማቆም ይደረግ” ሲል ለተመድ፣ አሜሪካ፣ አውሮፓና ለሚያውቃቸው ሁሉ ደብዳቤ በማሰራጨት ነበሱን ማትረፉን በመርሳት የትግራይ ቲቪ “የመከላከያ ባታሊዮን ጦር ወደ ትግራይ ገብቷል” በሚል አቶ ጌታቸውን ጠቅሶ ዘግቧል። ዘገባው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ልክ ዛሬ ትግራይን እንደተቆጣጠረ አድርጎ የሚያስት ዜና መስራቱን ያዩ ” አቶ ጌታቸው አሁንም አፋቸው እያፈሰሰ ነው። ባስቸኳይ እንዲያስተካክሉ ሊነገራቸው ይገባል” እያሉ በማህበራዊ ሚዲያ መንግስትን እያነቁ ነው።

በጦርነቱ ወቅት አስገራሚ የካድሬ ወሬ ሲያወሩና በየቀኑ አስደንጋጭ መረጃ ሲያሰራጩ የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ ” ማፍሰሱ” ለምዶባቸው ስለሆነ እስኪድኑ ዝምታን እንዲመርጡ መመከር እንዳለባቸው ያሳሰቡ ጥቂት አይደሉም። መንግስትም የሰላም ስምምነቱን ” ሰርግና ምላሽ ባያድርገውና ረጋ ብሎ በስከነ መንፈስ ቢያስኬደው መልካም እንደሆነ፣ በተለይም በካድሬ ደረጃ ሳይሆን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ ላይ ትኩረት ቢያደርግ” የሚሉም አሉ።

ይህ በንዲህ እንዳለ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግሥት መሠረት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት የሚተዳደሩ ተቋማትን ለመጠበቅ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በዛሬው ዕለት ትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ገብቶ ሥራ መጀመሩን ይፋ ሆኗል።

መንግስትና ትህነግ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የደረሱባቸውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በትግራይ ክልል የሚገኙ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት የሚተዳደሩ አየር ማረፊያዎች፣ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ የቴሌኮም አገልግሎት፣ የባንክና ሌሎች ለህብረተሰቡ አገልግሎት ለሚሰጡ የፌደራል ተቋማት አስተማማኝ ጥበቃ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ቀደም ብሎም በትግራይ ክልል አካባቢዎች በመግባት ህብረተሰቡን በማረጋጋት ወደ ቀየአቸው እንዲመለሱ በማድረግ የፀጥታና ደህንነት የማስከበር ስራዎችን እየሰራ መቆየቱ ይታወቃል።

ኢትዮ 12ን በቲውተር በቴሌግራምበፌስቡክ ይከተሉ

Exit mobile version