Site icon ETHIO12.COM

ሰማኒያ በመቶ የሚሆኑት ሚኒስትሮች ይሰናበታሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የሚመሩት ካቢኔ ከሰማንያ መቶ በላይ ለውጥ እንደሚደረግበት ኢትዮ12 ሰምታለች። ለመረጃው እጅግ ቅርብ የሆኑ እንዳሉት ከተሰናባች ሚኒስትሮች መካከል እንደ ልምዳቸው በቢሮ ደረጃ ምክትል ሊሆኑ የሚችሉ እንዳለ ተመልክቷል።

መንግስት ካቢኔውን በዚህ ብዛት ለማሰናበትና በአዲስ ለመተካት ያሰበው ከአቅም ጋር በተያያዘ ሲሆን፣ ሰሞኑን የአዳዲስ አምባሳደሮች ሹመት ይፋ ሲሆን በአምባሳደርነት ሃላፊነታቸው የተመሰገነ ስራ በማከናወን የታወቁ ከሃላፊነታቸው መነሳታቸው አነጋጋሪ ሆኖ መሰነበቱ ይታወሳል። በግንባር ቀደም በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት አቶ ሄኖክ ተፈራ ናቸው።

ኢትዮ12 እንደሰማችው ከሆነ ከውጭ ጉዳይ ጀምሮ በሚደረግ የሚኒስትሮች ለውጥ በርካታ አዳዲ ሰዎች ወደ ፊት ይመጣሉ። መንግስት በዚሁ ዘርፍ እንዲያገለግሉ ሲያመቻቻቸው የነበሩ በሹመቱ ይካተታሉ።

“አንዳንድ ሚኒስትሮች ከሚታወቁበት የቀድሞ የሚዲያ ደጅ ጠፍተዋል” በሚል የሚናፈሰው ወሬ ከምን የመነጨ እንደሆነ የመረጃው ባለቤቶች ገልጸዋል። ምክንያቱ ወንበራቸውን እንደሚለቁ ማወቃቸውን ተከትሎ የተፈጠረ ስሜት ነው። ምንም ሆነ ምን በአጭር ቀናት ውስጥ ሹመቱ ይፋ እንደሚሆን ታውቋል። ከኦእነግ፣ ኢዜማና አብን የተሾሙት ሶስቱ ሚኒስትሮች ድርጅታቸው እስካልጠየቀ ድረስ በሚኒስትር ማዕረግ ስራቸውን እንደሚቀጥሉም ለመረዳት ተችሏል።

በሌላ ዜና አቶ ተሾመ ቶጋ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው መሾማቸው መንግስትን ለትችት ዳርጎታል። የፓርላማ አፈጉባኤ በነበሩበት ወቅት የተቀናቃኝ ፓርቲ ወኪሎችን በማራከስ፣ በመገደብ፣ ንግግራቸውን በማስቆም፣ ስልጣናቸውን ተገን አድረገው በማስፈራራት ሲፈጽሙ የነበረውን ተግባር ያስታወሱ ለውጡን ተከትሎ አራት ዓመታትን በአምባሳደርነት ለዚያውም ቻይና መስራታቸው ሳያንስ አሁንም ኮሚሽነር መሆናቸው አግባብ እንዳልሆነ ከየአቅጣጫው እየተገለጸ ነው። ለትህነግ ልዩ ታማኝ የነበሩት አቶ ተሾመ የስፖርት ሚኒስትር ሆነውም ለግለሰቦች ሲሉ ኢትዮጵያ በፊፋ እንድትታገድ ትልቅ ሚና መጫወታቸው በአገር ደራጃ ጥቁር ታሪካቸው እንደሆነ እነዚሁ ወገኖች ያስታውሳሉ።

“በተለይ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ፓርላማ በሚገኙበት ወቅት ነበር ለመምስለና ተላላኪነታቸውን ለማጽናት እየተንፈራገጡ የሚወስዱት እርምጃ አስነዋሪ፣ በዚሁ ተግባራቸው ህዝብ የሚጠላቸው ነበሩ” የሚሉ አሁን የተሾሙበት የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነርነት የቀድሞ አለቆቻቸውን በማቋቋም ስም ዳግም የሚያገኙበት መሆኑ ጉዳዩን ግጥምጥም አሰኝቶታል።

Exit mobile version