ETHIO12.COM

ኢትዮጵያ ፈረንሳይና ጀርመን መከሩ፤ ኸርማንክሆን ትህነግ መሟሟት አለበት አሉ

ሰሞኑንን ኢትዮጵያ ላይ አድመው የነበሩ አገራት ወደ አገር ቤት ከፍተኛ ባለስልጣኖቻቸውን እየላኩ ነው። በጦርነቱ ወቅት ኢትዮጵያ በውጭ ሃይሎች ተወጥራ በነበረበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ” እንግባ ብለው ይለምናሉ” ብለው ሲናገሩ እንደነበረው የሆነ ይመስል። ትህነግንና ሻእቢያን አንድ ላይ ያነገሱት ኸርማንክሆንም እንግዶቹ በነካ እጃቸው ትህነግን እንዲያሟሙ የሚጠይቅ ጥሪ አቅርበዋል።

“ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፈረንሳይና ጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ” የሚለውን ዜና የመንግስት ሚዲያዎች በስፋት ቢዘግቡትም፣ ከሰዎቹ መምጣት በላይ ዜናውን የጎነው አመጣጣቸው ቀድሞ የተያዘ ዕቅድ ቢሆንም የቻይናውን ጠቅላይ ሚኒስትር ተከትለው መሆኑን ዜናውን የሚከታተሉ እየገለጹ ነው። ከቻይና ጋር ለጊዜው ያለተመለሱ “ስልታዊ” ስምምነቶች መደረጋቸውም በተሰማ ዋዜማ እንደሆነም እየተሰማ ነው።

የሰላም ስምምነቱ ” ትህነግ አሸናነፌን አሳምሩልኝ” ብሎ በተማጸነው መሰረት ከተከናወነ በሁዋላ ጆ ባይደን ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ደብዳቤ ጽፈው መጋበዛቸውን ተከትሎ መሆኑ ደግሞ በዲፕሎማሲውም መንገድ ድል እየተመዘገበ እንደሆነ አመላካች ሆኗል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ የአውሮፓ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካትሪን ኮሎንና እና ከጀርመን የፌደራል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌና ባየርቦክ ጋር መወያየታቸውን ” Today I have met with Catherine Collonna, France’s Minister for Europe & Foreign Affairs and Annalena Baerbock, Germany’s Federal Minister of Foreign Affairs. Our in-depth & fruitful discussions are reflective of the strong relations Ethiopia holds with both France and Germany.” ውጤታማ፣ ጥልቅ ውይይት ማድረጋቸውን፣ ይህም የሁለቱን አገራት ጠንካራ ወዳጅነት የሚያሳይ እንደሆነ ገልጸዋል። “ጥልቅና ፍሪያማ” ያሉትን ጉዳይ ባያብራሩም አውሮፓ ህብረት የዘጋጋቸውን መስኮቶች ለመክፈት ከዳር መደረሱን አመላካች ጉዳይ እንደሆነ ገልጸዋል።

የጀርመንና ፈረንሳይ ሚኒስትሮችም ለውጡን ለማስቀጠል አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ፣ ቀደም ሲል ሲያደርጉት የነበረውን እገዛ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ማረጋገጣቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

በሌላ ተመጋጋቢ ዜና ዲፕሎማቶችና አምባሳደሮች አዲስ አበባን ለቀው እንዲወጡ ሲወተውቱና በቀጠሯቸው የሚዲያ ሰራተኞቻቸው ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጩ የነበሩት የጀርመንና ፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውን ተከትሎ ኽርማንኮሆን “እግረ መንገዳችሁን ትህይነግን አሟሙት” ሲሉ በቲወተር ገጻቸው አስፍረዋል።

እርጅና የተጫናቸው የቀድሞ የትህነግ አንጋሽ ኸርማንኮሆን ሚኒስትሮቹ ወደ አዲስ አበባ የመሄዳቸውን ዜና አስቀድመው፣ ለሰላም ለማጠናከር ወይም ቋሚ ለማድረግ ሲባል ትህነግ እንዲሟሟ ወይም እንዲፈርስ እንዲያመቻቹ ጠይቀዋል። በተጨማሪም ከዚሁ ከትህነግ መክሰም ረገድም ኤርትራን እንዲጎበኙ መክረዋል።

ሰውየው ቢያረጁም ከመሬት ተነስተው እንደማያወሩ የሚገልጹ ” አብይ አህመድ መሾም አለበት” ብለው ቀድመው መናገራቸውን በማስታወስ ቀጣይ ዜናዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ አስታውቀዋል።

Exit mobile version