Site icon ETHIO12.COM

በ”ገዳዩ” የትህነግ የትምህርት ፖሊሲ “ትውልድ ላሽቋል”፤ ብርሃኑ ነጋ ታዩ

በጦርነት እንዳይሆን ሆኖ ከተቀጠቀጠ በሁዋላ ትዕቢቱን በውርደትና ተዘርዝሮ በማይጠቃለል ኪሳራ ዘግቶ የፍርድ ቀኑንን የሚጠብቀው ትህነግ፣ ዛሬ በድጋሚ ድል መደረጉ ይፋ ሆኗል። “ኢትዮጵያ ትህነግን በገሃድ ድል አደረች። ልጆቿንም ከመንጋጋው ነጠቀች” ሲሉ የገለጹ ” ለምን ድንጋይ ወርዋሪና በመንጋ የሚነዳ ትውልድ እንድተፈጠረ አሁን ገባን” ሲሉም ተደምጠዋል።

የአስራ ሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች የፈተና ውጤት ይፋ ሲሆን ሶስት ነጥብ ሶስት ከመቶ የሚሆኑት ብቻ ማለፋቸውን ወይም ከሃምሳ በላይ ውጤት ማምጣት እንደቻሉ መገለጹን ተከትሎ ነው ከላይ የተገለጹት አስተያየቶች የተሰሙት። በማህበራዊ ሚዲያ አውታሮች የተሰራጩት። ” የትህነግ ገዳይ የትምህርት ፖሊሲ ትውልድ አምክኖ በኪሳራ ተዘጋ” ሲሉ የጻፉም አሉ።

“የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ50 በመቶ በላይ ያመጡት ተፈታኞች 3 ነጥብ 3 በመቶ ናቸው” መባሉን ተከትሎ ” አሁን ምን ይባላል? ምንስ መፍትሄ ይኖራል?” ሲሉ የጠየቁ በርካታ ቢሆኑም ” ይህ ዳግም ድል ነው። ትህነግ ዳግም ድል ተመታ። ትውልድ እንደቀበረ ተቀበረ …. እንኳንም ውጤቱን አየነው። ትውልድ ራሱን አይቶ እንዲያስብ ይረዳዋል” ሲሉ የቁጭት አስተያየት የሰጡ ጥቂት አይደሉም።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ50 በመቶ በላይ ያመጡት ተፈታኞች 3 ነጥብ 3 በመቶ ብቻ መሆናቸው ለትህነግ፣ ለትህነግ አገልጋዮችና በዚህ አውድ ተንከባለው ለመጡ ሁሉ ሃፍረት እንደሆነም እየተገለጸ ነው።

ለመጀመሪያ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ በጥብቅ ቁጥጥርና ስልት ከኩረጃ ነጻ እንዲሆን ባደረጉት ፈተና ላይ ከውጭና ከውስጥ ጫጫታው በርትቶ እንደነበር ይታወሳል። በደቦ መስራት የለመዱ ” ፈተና አንፈተንም” እስከማለት ደርሰው ሁከት ለማስነሳት እንደ አቶ ክስርስቲያን ታደለ ሳይቀሩ እጃቸውን አስገብተውም ነበር። ነጋ ቦንገር ” ዞር በሉ” በሚል የጸና አቋማቸው፣ መንግስትም ነጻነት አጎናጽፏቸውና የጠየቁትን በጀት ፈቅዶ፣ በመጨረሻ የተገኘው ውጤት እንደ አገር ትንሳኤ ሊሆን እንደቻለ እየተገለጸ ነው።

ዩሪ ቢስሜኖቭ በቀደመችው ሶቪየት ህብረት ኬጂቢን ሲያገለግል የነበረ፣ በጋዜጠኛናት የሰራ ሰው ነው። አሱ አንደሚለው አንድን አገር አንበርክኮ ለመግዛት ትውልድን ማላሸቅ፣ ትውልዱን አላሽቆ አውነትን እንዳይቀበል ማድረግ፣ በተቋማት ውስጥ የላሸቁትን በመመደብ ማንኮታኮት መበተን፣ ኢኮኖሚውን ማናጋት፣ ቀውስ መፍጠር፣ በቀውስ ወስጥ ማህበራዊ እረፍት መንሳት፣ ይህ ሁሉ ከሆነ በሁዋላ ኖርማላይዜሽን ወይም አረጋጊ መስሎ ወደ ቤተመንግስት መሮጥ። ሊንኩን ተጭነው ሙሉውን ያንብቡ

የተማሪዎቹን ውጤት በተመለከተ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ መግለጫ ሲሰጡ እንዳሉት፤ ፈተናውን ከወሰዱት 896 ሺህ 520 ተማሪዎች መካከል ከ50 በመቶ በላይ ያመጡት ተማሪዎች ቁጥር 29 ሺህ 909 ብቻ ናቸው። ይህ አስደንጋጭ፣ ግን ከገዳዩ የትምህርት ፖሊሲ መገላገል ግድ መሆኑንን አመላካች ዜና የኪጂቢው ሰላይ የተናገረውን የሚያስታውስ ሆኗል። እንደ ዩሪ አባባል ትውልድ እንዲገሽብና እንዲደነቁር የሚደረገው በሂሳብ ነው።

“ለራሳቸው ልጆች ልዩ ትምህርት ቤት አዘጋጅተው ሌላውን በድንቁርና ምች በመምታት፣ አደንቁረው እንዳሻቸው ሊነዱት አስበው የዳከሩት የትህነግ ቁልፍ ቁማርተኞች ግብራቸው ሳይሆን አሳባቸው ዛሬ ላይነሳ ተቀበረ” ሲሉ አቶ ሳህሌ ደበበ በጽሁፍ ገልጸዋል። አያይዘውም ” ስለምን ድንጋይ ወርዋሪና አስወርዋሪ፣ አቅም የሌላቸው አመራሮችና አገርን በቁም የሚቀብሩ ሌቦች እንደተፈጠሩ ዛሬ ካልገባን እስከወዲያኛው አይገባንም” ብለዋል።

ከ50 በመቶ በታች ካመጡ ተማሪዎች መካከል በዩኒቨርሲቲዎች የመቀበል አቅም እየታየ ካመጡት ውጤት በመነሳት የማብቂያ ትምህርት እየተሰጣቸው ፈተና እንዲወስዱ ይደረግና ካለፉ በቀጣዩ ዓመት ትምህርት እንዲቀጥሉ ሁኔታዎች መመቻቸቱን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ይህ አካሄድ ራስን ከድንጋይ ወርዋሪነት፣ ከአልባሌ ሱሶች፣ ከመንጋ እሳቤ በማረቅ ማጥናት ብቻ መፍትሄ እንደሆነ ትውልድ እንዲረዳ መልካም አጋጣሚ መሆኑንን አስተያየት የሰጡ ተናግረዋል። በዳግም ፈተናውም ቢሆን እድል የሚያገኙ እስከ 100 ሺህ የሚደርሱ ተማሪዎች በመሆናቸው፣ ከወዲሁ ዕድሉን የሚያገኙ ውገባቸውን ጠብቅ እንዲያደርጉ የመከሩም አሉ።

“ትህነግ እሱን መሳይ እንዳመረተ ሁሉ፣ በአመክኖ የሚያምን ጠያቂ ትውልድ በማምረት በኢዮጵያ የአሳብ ልዕልና የበላይነት እንዲያገኝ ፕሮፌሰር ብርሃኑ መሰረት ጥለዋል” ሲሉ የመድሃኔዓለም መመህር መሆናቸውን የጠቀሱ ገልጸዋል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ በምርጫ 97 ወቅት የትህነግን የትምህርት ፖሊሲ “ገዳይ” በማለት ትውልድን የሚጨርስ እንደሆነ አደባባይ ሲከራከሩ እንደነበር አይዘነጋም። ከሁለት አስርት ዓመት በሁዋላ ትንቢታቸውን ሚኒስትር ሆነው አይተዋል። በቀጣይም ትውልድ የሚድንበትን የትምህርት ፖሊሲ በማስረጽ ታሪካዊና ሙያዊ አደራቸውን እንደሚወጡ ይጠበቃል።

በምርጫ 97 ” ቦዘኔ ለውጥ አያመጣም” በሚል አቶ በረከት ድርጅታቸው ባመረታቸው ታዳጊዎች ላይ ሲቀልዱ፣ በርካቶች እደ ዩሪ ትንታኔ አልገባቸውም ነበር። ዛሬ ትውልድ መገሸቡ አደባባይ ሆኗል። አገሪቱ በግዢና በፖለቲካ ውሳኔ በሚሰጥ ዲግሪ መጥለቅለቋ ያሳሰባቸው ፕሮፌሰር ብርሃኑ ‹‹የትምህርት ሥርዓቱ ክፉኛ ወድቋል፡፡ እንስማማ፣ እንደ አገር እንስማማ፤ለዚህም ይረዳ ዘንድ ፖለቲካንና ትምህርትን እንለይ፡፡ ትምህርትን ከአካባቢ ፉክክር እንለይ፡፡ በ30.7 ሚሊዮን ተማሪዎች ሕይወት ላይ አንፍረድ፤›› ሲሉ ቀደም ሲል በፓርላማ ፊት ቀርበው ማስጠንቀቂያ አዘል ጥያቄ ማቅረባቸው አይዘነጋም።

አቶ መለስ የትምህርት ሚኒስትር ያደረጓቸው ወ/ሮ ገነት ዘውዴ ምሁራንን ከዩኒቨርስቲ ጠራርጎ በማስወጣት በታሪክ የሚጠቀሱ እንስት ሲሆኑ፣ በዚሁ ተግባራቸው “የዘመኑ ዮዲት ጉዲት” ተብለውም ነበር። ከአርባ በላይ ከፍተኛ ምሁራንን አባሮ ኦና የሆነው የአገሪቱ ዩኒዘርስቲ ከዛ ስብራቱ በሁዋላ በወጉ እንዳላገገመ ዛሬ ድረስ ይጠቀሳል።

Exit mobile version