Site icon ETHIO12.COM

“በቀጣይ ዋናው የቤት ስራችን እንደመሪ ፓርቲ ነፃነትን በአግባቡ መጠቀምና ማስተዳደር ላይ መስራት ነው”

“ድሎችን ማፅናትና ፈተናዎችን መሻገር” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው ወቅታዊና ታሪካዊ የአመራር ተልእኮ መድረክ በሀገራዊ የሰላም ፣ የጸጥታ እና የልማት ጉዳዮች ላይ ለሦስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው ውይይት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቋል፡፡

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚደንትና የዋናው ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ከተሳታፊ አመራሮች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የኑሮ ውድነትን፣ የስራ እድል ፈጠራን፣ መንግስታዊ አገልግሎት አሰጣጥና እንዲሁም የሰላምና ደህንነት ጉዳዮችን በሚመለከት ብልጽግና ፓርቲ በትኩረት እንደሚሰራ አበክረው ገልፀዋል።

ብልፅግና ፓርቲ አስቀድሞ የጀመራቸውን መርህን መሰረት ያደረጉ ተቋማዊ አሰራሮችን አጠናክሮ በማስቀጠል የፓርቲውን ህዝባዊ ቅቡልነት ማሳደግና ጠንካራ መንግስታዊ አቅም መፍጠር እንደሚገባም ጠቅሰዋል፡፡

ይህንንም ለማጠናከር አመራሩ የአመለካከት እና የተግባር አንድነቱን በማጠናከር በህብረ ብሔራዊ አንድነት በተሰናሰለ ወጥ ሀገራዊ እሳቤ አቅም መሆን እንደሚገባው አንስተዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ፖለቲካዊ እሳቤዎች ኢትዮጵያዊ መሰረት ያላቸውና የሀገራችንን እና የህዝባችንን ችግር ፈቺዎች እንዲሆኑ ማድረግ፣ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ማሳደግና የህዝቡን ፖለቲካዊ ሞጋችነትና የልማት ተሳትፎ እንዲሁም ተጠቃሚነት በማሳደግ ቅቡልነትና ማሳገድ እንደሚገባም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በአጠቃላይ ብልጽግና ፓርቲ መላ መዋቅራዊ አቅሙን ፈትሾ የሚታዩ የአመራር የአቅም ጉድለቶችን አርሞ፣ ውስጣዊ ብልሽቶችን አክሞና መርህን መሰረት ባደረገ አግባብ ተግባራት በማሳለጥ የተጀመረውን ሀገራዊ ለውጥና እድገት በማስቀጠል ህዝባዊ ቅቡልነትን ማሳደግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞ እንደሀገር የመጣውን ነፃነት ከመጠቀም ጋር ሰፊ ክፍተት እንዳለና ነፃነትን ማክበርና ማስከበር በሚመለከት ብልፅግና ፓርቲ የሚደራደርበት ጉዳይ እንዳልሆነ አሳስበዋል፡፡

እንደመሪ ፓርቲ ነፃነትን በአግባቡ መጠቀምና ማስተዳደር ላይ መስራት እንደሚገባም አክለው ገልፀዋል፡፡
በተመሳሳይ ነፃነትን በፓርቲው ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባና የፓርቲው አመራርና አባል ተገቢ ነፃነት ተጎናፅፎ ሃሳቡን ያለተፅዕኖ እያራመደ መቀጠል እንዳለበት በአፅንኦት አስቀምጠዋል።

እንደሀገር የዴሞክራሲ፣ የፍትህና የዳኝነት ተቋማት በነፃነትና በገለልተኝነት ስራቸውን አጠናክረው መስራት እንደሚገባቸውም ለተሳታፊ አመራሮች ማንሳታቸውን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

Credit ENA

Exit mobile version