ETHIO12.COM

አገር ሳይጠቅሱ “ኢትዮጲያዊ ያልሆናችሁ እጃችሁን ሰብሰቡ” ሲሉ አብይ አሕመድ አስጠነቀቁ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ” ኢትዮጵያዊ ያልሆናችሁ እጃቸውን እንዲሰበሰቡ እጠይቃለሁ” ሲሉ አስጠነቀቁ። የገበታ ለሀገር ኮይሻ ፕሮጀክት አካል የሆነው ሀላላ ኬላ ሪዞርት የተለያዩ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮችና የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ሲመረቅ ጠቅላይ ሚኒስትርይ የአገር ስም ሳይጠቅሱ ያስተላለፉት ማስጠንቀቂያ ለበርካቶች ግልጽ ነው።

“ኮሽ ባለ ቁጥር አሉ” ጠቅላይ ሚኒስይትሩ፣ ” ኮሽ ባለ ቁጥር በኢዮጵያ ጉዳይ ለመትፈት የምትፈለጉ ሃይሎች ከድርጊታችሁ እንድተቆጠቡ ወይም እንድትሰበሰቡ አሳስባለሁ” ሲሉ የኢትኦጵያን ጉዳይ ለኢትዮጵያ ብቻ እንዲተው ተማጽነዋል።

ኢትዮጵያዊያንን በማበጣበጥና በማባላት የሚገኝ የፖለቲካ ትርፍ እንደሌለ ያወሱት አብይ አህመድ፣ ” የእኛን ጉዳይ ለእኛ ተውት” ብለዋል። በራሳቸው ምድር ወይም አገር ላይ ለራሳቸው ህዝብ ያልሰሩት በርካታ ጉዳይ ስላለ ያንኑ ትኩረት ሰጥተው ቢሰሩ እንደሚሻልም አመልክተዋል። ደጋግመው “የእኛን ጉዳይ ለእኛ ቢተው እንደሚሻል ማሳሰብ እፈልጋለሁ” ብለዋል።

የፕሬዚዳንት ኢሳያስ መንግስት በግልጽ በትግራይ ሰላም እንዲሰፍን የተደረገውን ስምምነት ማጣጣሉ፣ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተፈጥሮ የነበረውን የቀኖና ጥሰት ተንተራሰው ጉዳዩ ዓለም አቀፍ ይዘት እንዲኖረው ካይሮ ድረስ በመዝለቅ የዘመቻው አስተባባሪና መሪ መሆናቸው፣ በውጭ አገር ያሉ ሚዲያዎችን በመደጎምና አጅንዳ በመስጠት ረገድ በስፋት እየሰሩ መሆናቸው፣ ከዚህም በላይ ኢመደበኛ ናቸው ከሚባሉ ታጣቂዎች ጋር ግንኙነት በመፍጠርና ከህገወጥ ንግድ ጋር በስፋት ስማቸው አገራቸውን በሚወዱ ዘንድ እየተነሳ በመሆኑ መልዕቱ ለማን ነው? የሚል ጥያቄ አጭሯል።

ኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ተፈጥሮ የነበርውን ሰላም ተከትሎ ምንም የተደረገ የንግድ ስምምነት ሳይኖር በከፍተኛ ደረጃ ለውጭ ዜጎች ባልተፈቀደ፣ እንዲሁም በህገወጥ ንግድ ጉዳይ ብዙ ቅሬታ እየቀረበ ባለበት ሰዓት ይህ መገለጹ፣ ነገሩን እያጠራው ነው የሚል አስተያየት አስነስቷል።

ኢትዮጵያ ሕግ ማስከበር እንደምትችል ማሳየቷን ያነሱት አብይ አህመድ አሁንም ህግን ለማስከበር ቁርጠኛ አቋም መያዙን ሲያስታውቁ ” ኢትዮጵያ ውስጥ አሳብን በሰላም መግለጽና መሸጥ ስለሚቻል መገዳደል አይስፈልግም፣ በመገዳደል የሚገኝ ነገር የለም” ብለዋል። ችግር እያየነከረ የሚሄድ እንጂ ሸብረክ የሚያደርግ ባለመሆኑ በተሳሳተ መንገድ ከመጓዝ ወጣቶች ራሳቸውን እንዲጠብቁ መክረዋል። እንዳለፈው የቀይ ሽብርና ነጭ ሽብ ጠባሳ አሳልፎ መጓዝ እንደማይጠቅም አሳስበው ” ኢትዮጵያዊ ያልሆናችሁ እጃችሁን ሰብስቡ” ብለዋል።

የሰሜን ክፍሉ ጦርነት ከቆመ በሁዋላ ፕረኢዚዳንት ኢሳያስ ኢትዮጵያ የገነባቸው ሃይልና ከአሜሪካና አውሮፓ ጋር እየመሰረተች ያለችው አዲስ ወዳጅነት እንዳልተመቻቸው አዋቂዎች ሲያስታውቁ ቆይተዋል። ከዚህም በላይ ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ላይ ጫና ፈጣሪ አገር ለመሆን እያኮበኮበች መሆኑና እጅግ የዘመነ የጦር መርከቦች ባለቤት የሆነ የባህር ሃይል ማዘጋጀቷ ” የኢትዮጵያ ቀጣይ አጀንዳ አሰብ ነው” በሚል አስተያየት እየተሰጠበት ነው።

“መሳይ መኮንን የትግራይ ሰላም ለኤርትራ ስጋት አይሆንም ወይ” በሚል በአሜሪካ የኤርትራ ዳያስፖራ ሰብሳቢ ባነጋገረበት ወቅት ስጋቱ እንዳለባቸው ማረጋገጣቸው አይዘነጋም።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኤርትራ ምድ ላይ የነበሩና ለውጡን ተከትሎ በነጻነት ሲንቀሳቀሱና ወረራውን በማምከን ረገድ የጀግንነት ስራ ሲያከናውኑ የነበሩ የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ቅሬታ እያሳዩ መሆኑ ይታወሳል። በአማራ ክልል በግልጽ ያለውን እቅስቃሴ እየመሩት ያሉት አዛውንት ሻለቃ ዳዊትም በተደጋጋሚ ኤርትራ መመላለሳቸውና ” ንቃት አልቋል አሁን ጊዜው የትግባር እርምጃ ነው” ሲሉ አውስትራሊያ ንግግር ማድረጋቸው ይታወሳል።

Exit mobile version