ETHIO12.COM

“ደብረ ኤሊያስ ገዳም የደረሰበት ጉዳት የለም” ወረዳው፤ መከላከያ ስራውን መጨረሱ ተሰማ

ከቤተ ክርስቲያኑ ግርጌ ተሰርቶ የነበረ ምሽግ

አካባባዊ በተለይም ገዳሙ ወታደራዊ ማስለጠኛ፣ የሚፈለጉ ሰዎች መመሸጊያ፣ ሃይማኖታዊ ዓላማውን የሳተ በመሆኑ በአባቶች፣ በሃይማኖት መሪዎች፣ በመንግስት ሃላፊዎችና ታውቃ ሰዎች ቢለመኑም ፈቃደኛ እንዳልሆኑ፣ በስተመጨረሻም ደብሩም ሆነ መኖኮሳቶች ምንም ሳይሆኑ መከላከያ ገብቶ ስራውን አከናውኖ መጨረሱ ተሰማ። በርካታ ታጣቂዎች ለመከላከያ እጃቸውን መስጠታቸውም ተገልጿል። ወረዳው መከላከያ ስራውን ጉዳት ሳያደርስ ማከናወኑን ይፋ ሲያደርግ እጅቻውን ስለሰጡና ስለተማረኩት ያለው ነገር የለም። ሻለቃ ዳዊት ወለደጊዮርጊስ የሚመራው የአማራ ህዝባዊ ግንባር ስለ ወታደራዊው ሽንፈትም ሆነ ድል ምንም ሳይል፣ የአማራ ህዝብ በህብረት እንዲነሳ ጥሪ አሰምቷል።

ይህ ከመሆኑ በፊትና ይህ ዜና ከወረዳው በይፋ ከመገለጹ በፊት ጎጃም የሚገኘው የደብረ ኤሊያስ ገዳም መቃተሉን፣ መከላከያ እንዳወደመው የሚያሳይ ምስል ነው ተብሎ የተሰርጨው መረጃ ሙሉ በሙሉ የሃስተ እንደሆነ መሳያ በማጣቀስ ጉዳዩን የሚከታተሉ ገልጸዋል። በሌላ በኩል መረጃ ቲሌቪቭን ደብረ “ኤሊያስ ግዳም በድሮን ሊደበደብ ነው” በሚል ዜና አቅርቧል። ታጣቂዎቹ ድል እንደቀናቸውም ሊንክ አድርጎ የሌላ ሚድያን ገጹ ላይ አኑሯል።

መረጃ በሚል ስያሜ የሚታወቀው የቲቪ( የዩቲዩብ) የተቃውሞ ማሰራጫ የደብረ “የአብይ አሕመድ አገዛዝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን እንደዚህ ነው በመድፍ ደብድቦ አያነደዳት ያለው” ሲል ነው የድሮ ፎቶ ልክ አሁን እንደተደረገ አድርጎ ያሰራጨው። መረጃ ይህን ዜና በቆየ ምስል አጅቦ አሁን እንድተደረገ በማስመሰል ማቅረቡን ተከትሎ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜናውን ሳያጣሩ አሰራጭተውለታል።

ዜናው ሃይማኖትን ለይቶ የማጥቃት፣ ጥቃቱን እያደረሰ ያለው ደግሞ የኦነግ መንግስት ሰራዊት ኦሮሞ እንደሆነ፣ ዓላማውም አማራ ክልልንና ኦርቶዶክስን የማጥፋት መሆኑንን፣ በዚህ ከቀጠለ የሁሉም ህልውና አደጋ ላይ እንደሚወድቅ፣ ሁሉም መረጃውን በፍጥነት አሰራጭቶ እንዲነሳሳ በማድረግ የበኩሉን እንዲወጣ ወዘተ ጥሪ በሚያስተላልፉ የታጀቡ ምስሎች በስፋት ሲሰራጩ መዋላቸው በርካቶችን አሳዝኖ ነበር። የምሬት ድምጽም ያሰሙ ነበሩ። ከሁሉም በላይ ሰዎች እንዲሰዉና እንዲጸድቁ ” የሰማዕትነት” ጥሪም ያስተጋቡ ጥቂት አልነበሩም።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን ” የኦነጉ ሰራዊት” በማለትና በማጠልሸት ላይ የተመሰረተው ይህ መረጃ በመረጃ ቲቪ አማካይነት በተበተነው ምስል አማካይነት ሁሉም የራሱን እያከል ሲቀባበለው ሊከሰት የሚችለውን አደጋና ዕልቂት የመረጃ ቲቪ ባለቤቶች ማስላት አለመቻላቸው አስገራሚ መሆኑንን መረጃ ቲቪን የሚያውቁ ገልጸዋል። የሃይማኖት ጉዳይ ጥንቃቄ የሚያሻው፣ በጥብቅ ጠርቶና ነጥሮ በትኩረት ቃላት ተመርጠው የሚሰራጭ ሆኖ ሳለ በዚህ ደረጃ የሃስተ ዜና በማሰራጨት ህዝብ እንዲጫረስ የተወሰነበት አግባብ በጥብቅ ሊመረመር እንደሚገባው እነዚሁ ወገኖች አመልክተዋል።

“በቅዱስ ሚካኤል ሼር አድርጉና ለምትችሉት ሁሉ አድርሱት” በሚል የተሰራጨውን ምስል ቶማስ ጃጃው ያሰራጩትን ክፍሎችና በታዘዙት መሰረት ” ደመነብሳዊ መንጋ” ብሎ በመሰየም ” በዛሬው ዕለት በደብረ ኤሊያስ ገዳም በመከላከያ ጥቃት ተፈፀመ ብሎ ሲያራግበው ከዋለው ሌላኛው የቤተክርስቲያን ፎቶ መካከል ይህ ሁለተኛው ነው። የቤተክርስቲያኑ ፎቶ መገኛ ራያ ሲሆን ፌስቡክ ላይ የተለጠፈው ደግሞ 30 Nov 2022 ነበር” ብሏል። ማስረጃውንም ከስክሪን በማንሳት ለታሪክ ይመዘገብ ዘንዳ በቴሌግራም ገጹ ላይ አኑሮታል።

ይህ የመረጃ ቲቪና የሌሎች በስብስብ ምስሉ ውስጥ ያሉ አካላት ያሰራጩት የተሳሳተ ምስል መሆኑ በመረጃ ተደግፎ ይፋ ቢሆንም፣ እስክንድር ነጋ በይፋ መሪው ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ እንደሆነ የመሰከረለትና እሱም የትጥቁን ትግል መቀላቀሉን ይፋ ያደረገለት ድርጅት ” መላው የአማራ ህዝብ እንዲነሳ” ሲል ይህን መግለጫ አሰራጭቷል።

1 / 25

የአማራ ህዝባዊ ግንባር ግንቦት 23/2015 ዓ.ም

ደብረኤልያስ ወረዳ በሚገኘው የሥላሴ አንድነት ገዳም ላይ 3 ሞርተሮችን ጨምሮ በተለያዩ ከባድና የቡድን መሳሪያዎች ጥቃት እየፈፀመ የሚገኘው የፌደራል መንግስቱ መከላከያ ኃይል፤በገዳሙ ግቢ ውስጥ ከ200 በላይ መናኝ እናቶች የሚገኙበትን ግቢ በሞርተር በመምታት ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ መነኮሳት አልቀዋል፤ሌሎችም ከፍተኛ ጉዳት አስተናግደዋል።በዚህም ገዥው የኦህዴድ ብልፅግና ስርዓት ከባድ የጦር ወንጀል ፈፅሟል።

ይህ የጦር ወንጀል በገዳሙ መናኝ እናቶች ላይ የተፈፀመው በአካባቢው የመደበኛ ስልክ ጥሪም ሆነ የኢንተርኔት አገልግሎት በማቋረጥ ነው።

ይህ ድርጊት በአገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ህጎች ፍፁም የተከለከለ በመሆኑ፣ የዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍ/ቤት(ICC) ጨምሮ የዓለም አቀፍ ማህበር ጉዳዩን በአጣዳፊ እንዲመለከተው እንጠይቃለን።

በጎጃም ደብረ ኤልያስ ጭፍጨፋ ሲፈፅም የቆየው የኦህዴድ ብልጽግና መከላከያ ሠራዊት ዛሬ ሸበል በረንታ፣ ዲማ ጊዮርጊስ፣ የትኖራ ፣ወጀል ዓባይ ፣በመርጦ ለማሪያም፣ደብረዎርቅ እና እሁዲት-ኢናባራ አየሁ መከላከያ እንዲገባ ወስኖ ተጨማሪ የጦር ወንጀል እንዲፈፀም እያደረገ ነው።

በተመሳሳይ በሰሜን ሸዋ እንሳሮ፣ራሳ፣መርሃ ቤቴ እና ይፋት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሠራዊት በማሰማራት በአማራ ህዝብ ላይ ከፍተኛ የጦር ወንጀል በኦህዴድ/ብልፅግና የሚመራው ገዢ ስርዓት እየፈፀመ ነው። መላው የአማራ ህዝብ በሠራዊቱ እየተፈፀመበት ያለውን የጦር ወንጀል በጋራ በመሆን ሊመክት ይገባል።

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ፣ሚዲያዎች፣የሲቪክ ማህበራት፣የሰብዓዊ መብት ተቋማት እና ሌሎችን የንፁሃን ጭፍጨፋን በአፅኖት ሊመለከቱት ይገባል።

የአማራ ህዝባዊ ግንባር ፣ ግንቦት 23/2015 ዓ.ም

“ቤተክርስቲያኑ በመድፍ ነደደ፣ ወደመ፣ አመድ ሆነ፣ መነክሴዎቹ ተፈጁ ….” ተብሎ በተለያዩ አግባቦች የተሰራጩት ምስሎች በተንሸራታቹ የምስል ሳጥን ውስጥ እንዳለ ይመልከቱ። ይህ ሁሉ ዜና ሲሰራጭ ቆይቶ፣ የእነ እነ ሻለቃ ዳዊት ግንባርም ተደጋጋሚ ጥሪ ካሰማ በሁዋላ፣ የደብረ ኤሊያስ ወረዳ በድብሩ ላይ ምንም የተፈጠረ ጉዳት እንደሌለ፣ ገዳሙ ዓላማውን በሳተ መልኩ ምን ሲሰራበት እንደነበር፣ መከላከያ ጉዳት ሳያደርስ አካባቢውን ተቆጣጥሮ ኦፕሬሽኑንን መፈጸሙን ዘርዝሮ የሚከተለውን መግለጫ አውጥቷል።

የደብረ ኤልያስ ወረዳ መግለጫ

የደብረ ኤልያስ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት

Exit mobile version