Site icon ETHIO12.COM

የበጀት ጉዳይ እይነጋገረ ነው፣ የ281 ቢሊየን ብር የበጀት ጉድለት

የቀጣዩ ዓመት በጀት ከወዲሁ በርካታ ክርክርና ስጋትን እያስተናገደ ቢሆንም ውሳኔውን ትክክል ነው ያሉ አሉ። መቼውንም የራሷን ዓመታዊ በጀት ችላ የማታውቀው ኢትዮጵያ አውሮፓና አሜሪካ ማነቆ ካደረጉባት ጊዜ አንስቶ እያደር ችግር እየገጠማት እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። ከዚሁ ችግር ጋር ተዳምሮ በገሪቱ በቅብብሎሽ የሚፈጸመው አሻጥርና ራሱ ጦርነቱ ያሳደረው ተጸዕኖ ከባድ ነው።

የሰሜኑ ጦርነት ከተጀመረ አንስቶ ሚዛን በጎደለው ውሳኔ መደበኛ እርዳታና ብድር ተዘግቶባት የከረመችው ኢትዮጵያ፣ ሰላሳ በመቶ የሚሆነውን ዓመታዊ በጀቷን በድጎማ ስታስኬደው እንደነበር የሚታወስ ነው። ከሰላም ስምምነቱ በሁዋላ የዓውሮፓ ህብረት እንደሚለቅ ያስታወቀውን ቋሚ የበጀት ድጋፍና እርዳታ በተባለውና በተለመደው መልኩ እስካሁን አልለቀቀም። አሜሪካም ሆነ የዓለም ባንክ በተመሳሳይ መንግስትን በስልት እያሹት እንደሆነ የሚታወቅ ነው።

በዚህ መነሻ ዓመታዊ በጀትን በራስ ለመሸፈን መንግስት ቁጠባን መሰረት ያደረገ በጀት ይፋ እንዳደረገ ተገልጿል። ለ2016 በጀት ዓመት ጠቅላላ ገቢ የውጭ እርዳታን ጨምሮ 520.6 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ የታቀደ ቢሆንም የ281.05 ቢሊየን ብር የበጀት ጉድለት እንዳጋጠመው ተገልጿል፡፡ ይህንን ጉድለትም በብድር ለመሸፈን ታቅዷል ነው የተባለው፡፡ ብድሩም በግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭና በሌሎች የአገር ውስጥ የብድር ግብአቶች እንደሚከናወን ነው የተገለጸው።

የዘንድሮው ዓመት በሚኒስትሮች ምክር ቤት የጸደቀው የ801 ቢሊየን ብር ካለፉት ዓመታት በጀት አንፃር የልማት ፍላጎቶችን ለማሟላት በቂ አለመሆኑ አቶ አህመድ ሸዴ በይፋ ተናግረዋል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ዛሬ የበጀት መግለጫውን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያቀርቡ እንዳሉት መንግሥት ከሀገር ውስጥ ገቢ እና ከውጪ አገር ርዳታ ምንጮች 520 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ማቀዱን ሚኒስትሩ አመልክተዋል ። በታቀደው ገቢ እና ወጪ መካከል ግን የ281 ቢሊየን ብር የበጀት ጉድለት መኖሩንም ሳይሸሽጉ ይፋ አድረገዋል። ይህ ጉድለትም ከውጭ ሀገር 39 ቢሊዮን ብር ቀሪው ደግሞ ከሀገር ውስጥ በብድር እንዲሸፈን መታቀዱን አመልክተዋል። ጉድለቱን ለመሸፈን ከታቀደው ብድር ደግሞ 53 ቢሊዮን የሚጠጋው ብሩ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ዋና እዳ ክፍያየሚውል ይፋ አድርገዋል።

በጀት ዓመቱ ከቀረበው 801.65 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ የፌዴራል መንግሥት በጀት ለአገር መከላከያ ሚኒስቴር 50 ቢሊዮን ብር ሲመደብ ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የወደሙ ተቋማትና አገልግሎቶችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ ደግሞ 20 ቢሊዮን ብር ተበጅቷል።

ባለፉት ዓመታት የተከሰቱ ተደራራቢ ቀውሶች የኢኮኖሚ እድገት ላይ ከፍተኛ ጫና ማሳደራቸውን ያስታወቁት የገንዘብ ሚኒስትሩ እንዲያም ሆኖ ግን ኢኮኖሚው በ6.1 በመቶ ማደጉንና በ2016 ደግሞ በ7.5 በመቶ ያድጋል ተብሎ እንደሚገመት ገልፀዋል። ሚኒስትሩ አክለውም በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት የወደሙ ንብረቶች እና አገልግሎት መስጫ ተቋማትን መልሶ ለመገንባትና ዜጎችን ለማቋቋም ከመንግሥት ግምጃ ቤት 20 ቢሊዮን ብር መመደቡን አብራርተዋል። ያነጋገርናቸው አንድ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ደግሞ መንግሥት ለዓመቱ የያዘው በጀት ከዋጋ ግሽበት አንፃር ካለፈው ዓመት ዝቅ ያል ነው ብለዋል። ከአምናው በጀት በ1.9 በመቶ ብቻ ሳይሆን ይህንን ግሽበት ለማካካስ እስከ 40 በመቶ የበጀት ጭማሪ ማድረግ ይጠበቅበትም እንደናበርም ገልፀዋል።

የ2016 በጀት ዓመት ካቀረበው 801.65 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት ውስጥ ለመደበኛ ወጪዎች 370.1 ቢሊዮን ብር ፣ ለካፒታል ወጪዎች 203.4 ቢሊዮን ብር፣ ለክልሎች የሚሰጥ የበጀት ድጋፍ 214 ቢሊዮን ብር፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ 14 ቢሊዮን ብር ሆኖ ቀርቧል

801.65 ሆኖ የቀረበው በጀት “የሀገር ደህንነትን ከማስጠበቅ፣ በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጐችን ከመርዳት፣ የወደሙ መሰረተ ልማቶች መልሶ ከማቋቋም፣ በቀጣይ ሊኖሩ የሚችሉን የማህበራዊና የኢኮኖሚ ለውጥ ዓላማዎችን ከማሳካት አንፃር የተቃኘ” ነው ተብሎለታ። የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ዛሬ ለተወካዮች ምክር ቤት ዝርዝሩን ሲያቀርቡ እንዳሉት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በቀውስ ተፈትኗል። በዋናነት በሀገር ውስጥ ገቢ ይሸፈናል የተባለው በጀት ለሀገር መከላከያ የሚመደበው ካለፈው አመት አንፃር መጠኑ ዝቅ እንደሚል፣ በጀቱ ካለፈው ዓመት ሲተያይ የልማት ፍላጎቶችን ለማሟላት በቂ እንደማይሆን በዚህም ምክንያት መንግሥት አዳዲስ ቅጥር እንደማይፈጽም አብራርተዋል። በጀቱ የ 281.05 ቢሊዮን ብር ጉድለት እንደሚኖረውም ገልፀዋል።

ለፌደራል መንግስት መደበኛ ወጪዎች 369.6 ቢሊየን ብር ፣ ለካፒታል ወጪዎች 203.9 ቢሊየን ብር ፣ ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ 214.07 ቢሊየን ብር እንዲሁም ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ 14 ቢሊየን በጠቅላላው 801.65 ቢሊየን ሆኖ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ በጀቱ የዋጋ ንረትን ለሚያረጋጉ ጉዳዮችም ትኩረት የተሰጠው ነው ተብሏል። ያነጋገርናቸው የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ግን መንግሥት ይህንን ግሽበት ለማካካስ እስከ 40 በመቶ የበጀት ጭማሪ ማድረግሲጠበቅበት ካምናው አንፃር የ 1.9 በመቶ ብቻ ጭማሪ ማድረገጉን ተችተዋል። 

መንግሥት በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት የወደሙ ንብረቶች እና አገልግሎት መስጫ ተቋማትን መልሶ ለመገንባትና ዜጎችን ለማቋቋም ከመንግሥት ግምጃ ቤት 20 ቢሊዮን ብር መድቧል። የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዶክተር ደግዬ ዓለሙ እንደሚሉት ግን ከደረሰው ውድመት አንፃግ ይህ ዝቅተኛ ነው። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በበጀቱ ላይ በርከት ያሉ ጥያቄዎችን አንስተዋል። ምክር ቤቱ በጀቱ ላይ ለአንድ ወር ከተወያየበት በኋላ የሪፐብሊኩ ጠቅላይ ሚኒስትር በተገኙበት እንደሚጸድቅ ዲደብሊው ካቀርበው ሪፖርት መረዳት ተችሏል።

ከዚሁ የበጀት ዜና ጋር በተያያዘ በሰፊው ቅብብሎሽ ያገኘው የገንዘብ ሚንስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የመንግስት ሠራተኛ ቅጥር እንደማይኖር ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ በጀት እንደሆነ መግለጻቸውን ተከትሎ ዋዜማ ” 2016 ዓ.ም በጀት አመት ምንም አይነት የመንግስት ሰራተኛ ቅጥር እንደማይፈጸም የገንዘብ ሚንስቴር አስታወቀ” ሲል ያሰፈረው ዘገባ ነው። ሚኒስርትሩ የስራ ፈጠራ በግል ዘርፉ እንደሚኖር የገለጹ ሲሆን ክልሎች ቅጥር እንዳያካሂዱ ስለመከልከሉ አልተገለጸም።

ከጥቂት ቀናት በፊት በሚንስትሮች ምክር ቤት ጸድቆ ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የተላከውን የ2016 ዓ.ም የመንግስት በጀት አስመልክተው ሰኔ 1 ቀን 2015 ዓም በፓርላማው ቀርበው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ሚንስትሩ የ2015 ዓም የኢኮኖሚ አፈጻጸምና የበጀት ረቂቁን በተመለከተ ባቀረቡት ማብራሪያ የ2016 የመደበኛ በጀት በየመ/ቤቱ ያለውን አዲሱን አደረጃጀት ታሳቢ በማድረግ፣ የበጀት አጠቃቀም በቁጠባና በውጤታማነት ላይ ያተኮረ እንደሚሆን ጠቅሰው በቀጣይ በጀት አመት አዳዲስ የመንግስት ሠራተኛ ቅጥር እንደማይኖር ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ በጀት መሆኑን ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡

መንግስት አዘጋጅቶ ባቀረበው የ2016 በጀት ዓመት ካቀረበው 801.65 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት ውስጥ ለመደበኛ ወጪዎች 370.1 ቢሊዮን ብር ፣ ለካፒታል ወጪዎች 203.4 ቢሊዮን ብር፣ ለክልሎች የሚሰጥ የበጀት ድጋፍ 214 ቢሊዮን ብር፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ 14 ቢሊዮን ብር ሆኖ ቀርቧል፡፡

የቀረበው በጀት የፊሲካል ሥርዓቱን ለማጠናከር የመንግስት ፋይናንስ አጠቃቀም ውጤታማነትን የሚያሻሽሉ፣ ግልጽነትና ተጠያቂነትን የሚያሰፍኑ ሥርዓቶችን በመዘርጋትና በውጤታማነት ሥራ ላይ በማዋል የሀብት ብክነትን ለማስወገድና በጀትን በቁጠባ ለመጠቀም የሚያስችሉ ተግባራት በተጠናከረ ሁኔታ ይተገበራል ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ የምክር ቤት አባላት ሚንስትሩ ባለፈው አመት የ2015 በጀት ለምክር ቤቱ ሲያቀርቡ በተመሳሳይ አዲስ ቅጥር እንደማይፈጸም መናገሩን አውስተው መንግስት ለአዳዲስ ምሩቃን የስራ እድል መፍጠር ካልቻለ የመንግስት ቅጥር ለሚፈልጉ ተመራቂዎች እጣ ፋንታ ምንድን ነው የሚል ቅሬታ አንስተዋል፡፡

በየአመቱ አዳዲስ የስራ እድል አይፈጠርም በሚል የሚቀጥል ከሆነ ተመራቂዎችና ዜጎች ተስፋ በመቁረጥ ለአላስፈላጊ ስደት እንዳይዳረጉ ስጋት አለኝ ሲሉ አንድ የምክርት አባል ቅሬታ አሰምተዋል፡፡ የምክር ቤት አባሏ አክለውም ይህ አሰራር የመልካም አስተዳደር ችግር እንደሚሆን ጠቅሰው‹‹ ምስኪን አርሶ አደሮች ብዙ መስዋዕት ከፍለው ነው ልጆቻቸውን አስተምረው የሚያወጡት ፣ በመንግስት መስሪያ ቤት በየአመቱ ይቀጠሩ የሚል እምነት ባይኖረኝም በምን መልኩ ነው አሁን የተማሩ ምሁራንን ወደ ስራ ማስገባት እና ማሰማራት የምንችለው ›› ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

በተመሳሳይ የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ መምህርና የምክር ቤት አባሉ ዶ/ር ዘገየ ሙሉየ ሲናገሩ ለዜጎቹ ስራ መፍጠር አንዱ የመንግስት ሃለፊነት መሆኑን ጠቅሰው ስራ ባለመፍጠር የትም ሊደረስ አይችለም ብለዋል፡፡ ይህን በመዝጋት ዘላቂ የሆነ ስራ መስራት አይቻለም ስለዚህ መንግስት የገቢ አሰባሰቡን ስርዓት በማስተካከልና የመንግስትን ወጭ በተገቢው ቦታ በማዋል ጠበቅ ተደርጎ ካልተሄደ በቅርብ ጊዜ ከችግር ሊወጣ አይችለም ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ በመንግስትና በግል ዩንቨርሰቲዎችና ኮሌጆች በየአመቱ በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች እየተመረቁ ይወጣሉ፡፡ ይሁን እንጂ የስራ እድል የማግኘት ሁኔታው አስከፊ ከመሆን አልፎ መንግስት በአገር ውስጥ የሚመረቁ ተማሪዎችን ከውጭ አገራት መንግስታት ጋር በመነጋገር በተለያዩ የስራ መስኮች ወደ ውጭ አገራት ስራ ስምሪት ለመላክ ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚንስትሩን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በየመድረኩ ሲያነሱ ይደመጣል፡፡

በቅርቡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ የስምንት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ሲቀርቡ በስምንት ወራት ውስጥ ለ2.6 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ለሁለት ሚሊዮን ዜጎች መፍጠሩን ገልጸው፡ ነገር ግን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ከስድስት ሚሊዮን በላይ ስራ አጥ ዜጎች መመዝገባቸውን ተናግረው ነበር፡፡

ከጥቂት ወራት በፊት የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በፓርላማው ቀርበው ባደረጉት ንግግር በአገሪቱ ውስጥ ከሚገኙ ተመራቂ ተማሪዎች 42 በመቶ የሚሆኑት ስራ አጥ መሆናቸውን አስታውቀው ነበር፡፡

የገንዘብ ሚንስትሩ ከምክርቤቱ ለቀረበላቸው ጥያቄ ማብራሪያ ሲሰጡ የኢትዮጵያ የመንግስት ሰራተኛ ቁጥር እጂግ በጣም ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው በመላው አገሪቱ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሰራተኛ አንዳለ ጠቅሰዋል፡፡

ውጤታማነትና የቁጥር ጉዳይ አብሮ በንጽጽር መታየት አለበት ያሉት ሚንስትሩ በቅርቡ የተዘጋጀ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ፕሮግራም መኖሩንና፣ ሪፎርሙ እንደየ ክልሎችና እንደየተቋማት ሁኔታ እየተመነዘረ ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል ብለዋል፡፡

‹‹እንኳን አዳዲስ ሰራተኛ ለመቅጠር ቀርቶ ያሉትን ሰራተኞች ጭምር የመዋቅር ማስተካከያ አድርገናል›› ያሉት ሚንስትሩ የተለያዩ ተቋማት ያላቸውን ዲፓርትመንት መቀነሳቸውን ተናግረዋል፡፡ ስራ እድል መፈጠር አለበት የሚለው የሚያስማማ ቢሆንም ‹‹መንግስት የስራ እድል መፍጠሪያ ማሽነሪ አይደለም፣›› በተቻለ መጠን የግሉ ዘርፈን ኢንቨስትመንት በማሳደግ መሰራት አለበት ብለዋል ሲል ዋዜማ ሬዲዮ አስታውቋል።

Exit mobile version